ኦሪት ዘፀአት 25
25
ለቤተ እግዚአብሔር የሚቀርብ መባ
(ዘፀ. 35፥4-9)
1እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረው፦ 2“የእስራኤልን ልጆች በልባችሁ ያሰባችሁትን ከገንዘባችሁ መባ አምጡልኝ” በላቸው። 3ከእነርሱም የምትቀበሉት መባ ይህ ነው፤ ወርቅ፥ ብር፥ ናስም፥ 4ሰማያዊና ሐምራዊ፥ ቀይም ድርብ ግምጃ፥ ጥሩ በፍታም፥ 5የፍየልም ጠጕር፥ ቀይ የተለፋ የአውራ በግ ቍርበት፥ ሰማያዊ ቀለም የገባ ቍርበት፥#ዕብ. “የአቆስጣ ቍርበት” ይላል። የማይነቅዝ ዕንጨት፥#ዕብ. “የግራር ዕንጨት” ይላል 6የመብራትም ዘይት፥ ለቅብዐት ዘይትና ለጣፋጭ ዕጣን ቅመም፥ 7መረግድም፥ ለልብሰ እንግድዓና ለደረት ኪስ የሚደረግ ፈርጥ። 8መቅደስ ትሠራልኛለህ፤ በመካከላቸውም አድራለሁ። 9በተራራው እንዳሳየሁህ ሁሉ፥ እንደ ማደሪያው ምሳሌ፥ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ ለእኔ ትሠራለህ፤ እንዲሁ ትሠራለህ።
የቃል ኪዳኑ ታቦት
(ዘፀ. 37፥1-9)
10“ከማይነቅዝ ዕንጨትም የምስክሩን ታቦት ሥራ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን። 11በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በእርሱም ላይ በዙሪያው የወርቅ አክሊል አድርግለት። 12አራት የወርቅ ቀለበቶችም አድርግለት፤ እነርሱንም በአራቱ እግሮቹ ላይ አኑር፤ በአንድ ወገን ሁለት ቀለበቶች፥ በሌላ ወገን ሁለት ቀለበቶች ይሁኑ። 13መሎጊያዎችንም ከማይነቅዝ ዕንጨት ሥራ፤ በወርቅም ለብጣቸው። 14ለታቦቱ መሸከሚያ በታቦቱ ጎን ባሉት አራት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አግባ። 15መሎጊያዎቹም በታቦቱ ቀለበቶች ውስጥ ተዋድደው ይኑሩ፤ ከቶም አይውጡ። 16በታቦቱም ውስጥ እኔ የምሰጥህን ምስክር ታስቀምጣለህ። 17ከጥሩ ወርቅም ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ የስርየት መክደኛ ሥራ። 18ሁለት ኪሩቤል ከተቀጠቀጠ ወርቅ ሥራ፤ በስርየት መክደኛውም ላይ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ። 19ከስርየት መክደኛውም ጋር አንዱን ኪሩብ በአንድ ወገን፥ ሁለተኛውንም ኪሩብ በሌላው ወገን አድርገህ በአንድ ላይ ትሠራዋለህ፤ ሁለቱንም ኪሩቤል እንዲሁ በሁለት ወገን ታደርጋቸዋለህ። 20ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ወደ ላይ ይዘረጋሉ፤ የስርየት መክደኛውንም በክንፎቻቸው ይሸፍናሉ፤ ፊታቸውም እርስ በርሱ ይተያያል፤ የኪሩቤልም ፊቶቻቸው ወደ ስርየት መክደኛው ይሁን። 21የስርየት መክደኛውንም በታቦቱ ላይ ታደርገዋለህ፤ እኔም የምሰጥህን ምስክር በታቦቱ ውስጥ ታኖረዋለህ። 22በዚያም እገለጥልሃለሁ፤ ለእስራኤል ልጆች የማዝዝህን ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።
ኅብስተ ገጹ የሚቀመጥበት ገበታ
(ዘፀ. 37፥10-16)
23“ርዝመቱም ሁለት ክንድ፥ ወርዱም አንድ ክንድ፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል የሆነ ገበታ ከማይነቅዝ ዕንጨት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከንጹሕ ወርቅ” ይላል። ሥራ። 24በጥሩም ወርቅ ትለብጠዋለህ፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት፤ 25በዙሪያውም አንድ ጋት የሚያህል ክፈፍ አድርግለት፤ የወርቅም አክሊል በክፈፉ ዙሪያ አድርግለት። 26አራትም የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት፤ ቀለበቶቹንም አራት እግሮቹ ባሉበት በአራቱ ማዕዘኖች አድርግ። 27ቀለበቶቹም ገበታውን ለመሸከም መሎጊያዎቹ እንዲሰኩባቸው በክፈፉ አቅራቢያ ይሁኑ። 28መሎጊያዎቹንም ከማይነቅዝ ዕንጨት ሥራ፤ በንጹሕ ወርቅም ለብጣቸው፤ ገበታውም በእነርሱ ይነሣ። 29ለማፍሰሻም ይሆኑ ዘንድ ወጭቶችዋን፥ ጭልፋዎችዋንም፥ መቅጃዎችዋንም፥ ጽዋዎችዋንም አድርግ፤ እነርሱንም ከጥሩ ወርቅ አድርጋቸው። 30በገበታም ላይ ኅብስተ ገጹን ሁልጊዜ በፊቴ ታደርጋለህ።
የቤተ እግዚአብሔር መቅረዝ
(ዘፀ. 37፥17-24)
31“መቅረዝንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ፤ የመቅረዙም እግሩና ቅርንጫፎቹ የተቀጠቀጠ ሥራ ይሁን፤ ጽዋዎቹም፥ ጕብጕቦቹም፥ አበቦቹም አንድነት በእርሱ ይደረጉበት። 32በስተጐኑ ስድስት ቅርንጫፎች ይውጡለት፤ ሦስት የመቅረዙ ቅርንጫፎች በአንድ ወገን፥ ሦስትም የመቅረዙ ቅርንጫፎች በሌላ ወገን ይውጡ። 33በአንደኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፤ በሁለተኛውም ቅርንጫፍ ጕብጕብና አበባ፥ ሦስትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች፤ እንዲሁም ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስት ቅርንጫፎች አድርግ። 34በመቅረዙም ጕብጕቦቹንና አበቦቹን፥ አራትም የለውዝ አበባ የሚመስሉትን ጽዋዎች ከእርሱ አድርግ። 35ከመቅረዙ ለሚወጡ ለስድስቱ ቅርንጫፎች ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ከሁለቱም ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ፥ ደግሞ ከሁለት ቅርንጫፎች በታች አንድ ሆኖ የተሠራ አንድ ጕብጕብ ይሁን። 36ጕብጕቦቹና ቅርንጫፎቹ ሁሉ ከእርሱ ጋር አንድ ይሁኑ፤ ሁሉም አንድ ሆኖ ከተቀጠቀጠ ከጥሩ ወርቅ ይደረግ። 37ሰባቱንም መብራቶች ሥራ፤ በፊቱ ያበሩ ዘንድ መብራቶቹን ያቀጣጥሉአቸዋል። 38መኰስተሪያዎችዋን፥ የኵስታሪ ማድረጊያዎችዋንም ከጥሩ ወርቅ አድርግ። 39መቅረዙም፥ ዕቃውም ሁሉ ከአንድ መክሊት ጥሩ ወርቅ ይሠሩ። 40በተራራ ላይ እንዳሳየሁህ ምሳሌ እንድትሠራ ተጠንቀቅ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፀአት 25: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ