የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 30

30
የዕ​ጣን መሠ​ውያ
(ዘፀ. 37፥25-28)
1“የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ውን ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት ሥራ። 2ርዝ​መቱ አንድ ክንድ፥ ስፋ​ቱም አንድ ክንድ፥ አራት ማዕ​ዘን ይሁን፤ ቁመ​ቱም ሁለት ክንድ ይሆ​ናል፤ ቀን​ዶ​ቹም ከእ​ርሱ ይሠሩ። 3ወለ​ሉ​ንና የግ​ድ​ግ​ዳ​ው​ንም ዙሪያ፥ ቀን​ዶ​ቹ​ንም በጥሩ ወርቅ ትለ​ብ​ጠ​ዋ​ለህ፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም የጥሩ ወርቅ ክፈፍ ታደ​ር​ግ​ለ​ታ​ለህ። 4ከክ​ፈ​ፉም በታች ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አድ​ር​ግ​ለት። በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለቱ ጐን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱን ያነ​ሡ​ባ​ቸው ዘንድ የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎቹ መግ​ቢያ ይሁኑ። 5መሎ​ጊ​ያ​ዎ​ቹ​ንም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት አድ​ርግ፤ በወ​ር​ቅም ለብ​ጣ​ቸው። 6ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ባለው መጋ​ረጃ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ።#ዕብ. “ይህ​ንም አን​ተን በም​ገ​ና​ኝ​በት ከም​ስ​ክሩ በላይ ባለው በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ” ይላል። 7አሮ​ንም በጎ መዓዛ ያለው የደ​ቀቀ ዕጣን በው​ስጡ በየ​ማ​ለ​ዳው ይጠ​ን​በት፤ መብ​ራ​ቶ​ቹን ሲያ​ዘ​ጋጅ ይጠ​ነው።#ምዕ. 30 ቍ. 7 “መብ​ራ​ቶ​ችን ሲያ​ዘ​ጋጅ ይጠ​ነው” የሚ​ለው በግ​እዙ የለም። 8ይህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ወ​ትር ዕጣን ይሆን ዘንድ አሮን በማታ ጊዜ መብ​ራ​ቶ​ቹን ሲያ​በራ ያጥ​ነ​ዋል። 9ሌላም ዕጣን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አታ​ቀ​ር​ብ​በ​ትም፤ የመ​ጠ​ጥም ቍር​ባን አታ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም። 10አሮ​ንም በዓ​መት አንድ ጊዜ በቀ​ን​ዶቹ ላይ ማስ​ተ​ስ​ረያ ያደ​ር​ጋል፤ በዓ​መት አንድ ጊዜ ኀጢ​አ​ትን ከሚ​ያ​ነ​ጻው ደም ይወ​ስ​ዳል፤ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም እን​ዲ​ያ​ነጻ ያደ​ር​ጋል፤ ይህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።”
ቤዛ ነፍስ
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 12“አንተ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ቍጥር የወ​ሰ​ድህ እንደ ሆነ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ መቅ​ሠ​ፍት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ቸው፥ በቈ​ጠ​ር​ሃ​ቸው ጊዜ ከእ​ነ​ርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥ​ራ​ቸው መጠን የነ​ፍ​ሱን ቤዛ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይስጥ። 13ይቈ​ጠሩ ዘንድ የሚ​ያ​ል​ፉት ሁሉ የሚ​ሰ​ጡት ይህ ነው፤ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን የሰ​ቅል ግማሽ ይሰ​ጣል። ሰቅ​ሉም ሃያ አቦሊ ነው፤ የሰ​ቅ​ሉም ግማሽ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍር​ባን ነው። 14ይቈ​ጠር ዘንድ የሚ​ያ​ል​ፈው ሁሉ፥ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም ከፍ ያለ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦታ ይሰ​ጣል። 15ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስጦታ ስት​ሰጡ ባለ ጠጋው ከሰ​ቅል ግማሽ አይ​ጨ​ምር፤ ድሃ​ውም አያ​ጕ​ድል። 16የማ​ስ​ተ​ስ​ረ​ያ​ው​ንም ገን​ዘብ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወስ​ደህ ለም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ማገ​ል​ገያ ትሰ​ጠ​ዋ​ለህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ለነ​ፍ​ሳ​ችሁ ቤዛ እን​ዲ​ሆን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች መታ​ሰ​ቢያ ይሁን።”
የመ​ታ​ጠ​ቢያ ሰን
17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 18“የመ​ታ​ጠ​ቢያ ሰን ከናስ፥ መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ከናስ ሥራ፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳ​ንና በመ​ሠ​ዊ​ያው መካ​ከል ታኖ​ረ​ዋ​ለህ፤ ውኃም ትጨ​ም​ር​በ​ታ​ለህ። 19አሮ​ንና ልጆ​ቹም እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይታ​ጠ​ቡ​በ​ታል። 20ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በገቡ ጊዜ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ሳት መሥ​ዋ​ዕት ያቃ​ጥሉ ዘንድ ወደ መሠ​ዊ​ያው ሊያ​ገ​ለ​ግሉ በቀ​ረቡ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሞቱ ይታ​ጠ​ቡ​በ​ታል። 21ወደ ምስ​ክ​ሩም ድን​ኳን በገቡ ጊዜ እን​ዳ​ይ​ሞቱ እጆ​ቻ​ቸ​ው​ንና እግ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ይታ​ጠቡ፤ ይህም ለእ​ነ​ርሱ ከእ​ነ​ር​ሱም በኋላ ለል​ጆ​ቻ​ቸው የዘ​ለ​ዓ​ለም ሥር​ዐት ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።”
የቅ​ብ​ዐት ዘይት
22እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦ 23“አን​ተም ክቡ​ሩን ሽቱ ውሰድ፤ የተ​መ​ረጠ የከ​ርቤ አበባ አም​ስት መቶ ሰቅል፥ የዚ​ህም ግማሽ ጣፋጭ ቀረፋ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ ያማረ የጠጅ ሣርም እን​ዲሁ ሁለት መቶ አምሳ ሰቅል፤ 24ብር​ጉ​ድም አም​ስት መቶ ሰቅል እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን፥ የወ​ይራ ዘይ​ትም አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ትወ​ስ​ዳ​ለህ። 25በቀ​ማ​ሚም ብል​ሃት እንደ ተሠራ ቅመም፥ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ታደ​ር​ገ​ዋ​ለህ፤ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ይሆ​ናል። 26የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ድን​ኳን፥ የም​ስ​ክ​ሩ​ንም ታቦት፥ 27ገበ​ታ​ው​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ መቅ​ረ​ዙ​ንም፥ ዕቃ​ው​ንም፥ የዕ​ጣን መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም፥ 28ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያና ዕቃ​ው​ንም ሁሉ፥ የመ​ታ​ጠ​ቢ​ያ​ውን ሰንና መቀ​መ​ጫ​ው​ንም ትቀ​ባ​በ​ታ​ለህ። 29ሁሉ​ንም ትቀ​ድ​ሳ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳ​ንም ይሆ​ናሉ፤ የሚ​ነ​ካ​ቸ​ውም ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል። 30በክ​ህ​ነ​ትም ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ አሮ​ን​ንና ልጆ​ቹን ቅባ​ቸው፤ ቀድ​ሳ​ቸ​ውም። 31አን​ተም ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፤ ይህ ለልጅ ልጃ​ችሁ የተ​ቀ​ደሰ የቅ​ብ​ዐት ዘይት ይሁን። 32በሌላ ሰው ሥጋ ላይ አይ​ፍ​ሰስ፤ እንደ እር​ሱም የተ​ሠራ ሌላ ቅብ​ዐት አታ​ድ​ርጉ፤ ቅዱስ ነው፤ ለእ​ና​ን​ተም ቅዱስ ይሁን። 33እንደ እርሱ ያለ​ውን የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው፥ በሌ​ላም ሰው ላይ የሚ​ያ​ፈ​ስ​ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።”
የዕ​ጣን ዝግ​ጅት
34እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ጣፋጭ ሽቱ ውሰድ፤ የሚ​ን​ጠ​ባ​ጠብ ሙጫ፥ በዛ​ጎል ውስጥ የሚ​ገኝ ሽቱ፥ የሚ​ሸ​ት​ትም ሙጫ፥ ጥሩም ዕጣን ውሰድ፤ የሁ​ሉም መጠን ትክ​ክል ይሁን። 35በቀ​ማሚ ብል​ሃት እንደ ተሠራ፥ የተ​ቀ​መመ ንጹ​ሕና ቅዱስ ዕጣን አድ​ር​ገው። 36ከእ​ር​ሱም ጥቂት ትወ​ቅ​ጣ​ለህ፤ ታል​መ​ው​ማ​ለህ፤ ከዚ​ያም ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ በም​ስ​ክሩ ፊት ታኖ​ረ​ዋ​ለህ። እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሁ​ን​ላ​ችሁ። 37በዚ​ህም አሠ​ራር የዚ​ህን ዕጣን ዐይ​ነት ለእ​ና​ንተ አታ​ድ​ርጉ፤ በእ​ና​ን​ተም ዘንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሁን። 38ሊያ​ሸ​ት​ተ​ውም እንደ እርሱ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ከሕ​ዝቡ ተለ​ይቶ ይጥፋ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ