የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 36

36
1“ባስ​ል​ኤ​ልና ኤል​ያብ፥ ለመ​ቅ​ደ​ስም ማገ​ል​ገያ ሥራ ሁሉ ያደ​ርጉ ዘንድ እን​ዲ​ያ​ውቁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጥበ​ብ​ንና ማስ​ተ​ዋ​ልን የሰ​ጣ​ቸው በል​ባ​ቸ​ውም ጥበ​በ​ኞች የሆኑ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ነገር ሁሉ አደ​ረጉ።”
ሕዝቡ ያቀ​ረ​ቡት ስጦታ
2ሙሴም ባስ​ል​ኤ​ል​ንና ኤል​ያ​ብን፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ዕው​ቀ​ት​ንና ጥበ​ብን በል​ቡ​ና​ቸው ያሳ​ደ​ረ​ባ​ቸ​ው​ንና ጥበብ ያላ​ቸ​ውን፥ ሥራ​ው​ንም ለመ​ሥ​ራት ይቀ​ርብ ዘንድ ልቡ ያስ​ነ​ሣ​ውን ሁሉ ሥራ​ውን ሠር​ተው ይፈ​ጽሙ ዘንድ ጠራ​ቸው። 3እነ​ር​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለመ​ቅ​ደስ ማገ​ል​ገያ ሥራ ያመ​ጡ​ትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀ​በሉ። እነ​ዚ​ያም እንደ ፈቃ​ዳ​ቸው ማለዳ ማለዳ ስጦ​ታ​ውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር። 4እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው በሚ​ሠ​ሩት የመ​ቅ​ደ​ሱን ሥራ የሚ​ሠሩ ጠቢ​ባን ሁሉ መጡ፤ 5እነ​ር​ሱም ለሙሴ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይደ​ረግ ዘንድ ላዘ​ዘው ሥራ ከሚ​በቃ በላይ እጅግ የሚ​በ​ልጥ ሕዝቡ አመጡ” ብለው ነገ​ሩት። 6ሙሴም አዘ​ዘና፥ “ወንድ ወይም ሴት ለመ​ቅ​ደስ ስጦታ ከዚህ የበ​ለጠ የሚ​ያ​መጣ አይ​ኑር” ብሎ በሰ​ፈሩ ውስጥ አወጀ። ሕዝ​ቡም እን​ዳ​ያ​መጡ ተከ​ለ​ከሉ። 7ያመ​ጡ​ትም ነገር ሥራን ሁሉ ለመ​ፈ​ጸም በቅቶ ገና ይተ​ርፍ ነበ​ረና።
የድ​ን​ኳኑ አሠ​ራር
(ዘፀ. 26፥1-37)
8በእ​ነ​ር​ሱም ዘንድ ያሉት፥ ሥራ ሲሠሩ የነ​በ​ሩት በል​ባ​ቸው ጥበ​በ​ኞች ሁሉ ድን​ኳ​ኑን ከዐ​ሥር መጋ​ረ​ጃ​ዎች ሠሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ሠሩ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በጥ​ልፍ ሥራ ኪሩ​ቤ​ልን አደ​ረ​ጉ​ባ​ቸው።#ምዕ. 36 ከቍ. 8 እስከ 38 የግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ከግ​እ​ዙና ከዕብ. ይለ​ያል። 9የእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መጋ​ረጃ ርዝ​መት ሃያ ስም​ንት ክንድ፥ ወር​ዱም አራት ክንድ ነበረ፤ የመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎቹ ሁሉ ልክ ትክ​ክል ነበረ። 10አም​ስ​ቱ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አን​ዱን ከሌ​ላው ጋር አጋ​ጠሙ፤ አም​ስ​ቱ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው እን​ዲሁ አጋ​ጠሙ። 11ከሚ​ጋ​ጠ​ሙ​ትም መጋ​ረ​ጃ​ዎች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ የሰ​ማ​ያ​ዊ​ውን ግምጃ ቀለ​በ​ቶች አደ​ረጉ፤ ደግሞ ከተ​ጋ​ጠ​ሙት ከሌ​ሎቹ በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ ላይ እን​ዲሁ አደ​ረጉ። 12አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን በአ​ንድ መጋ​ረጃ አደ​ረጉ፤ አም​ሳ​ው​ንም ቀለ​በ​ቶች በሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ ዘርፍ አደ​ረጉ፤ ቀለ​በ​ቶቹ እርስ በር​ሳ​ቸው ፊት ለፊት የሚ​ተ​ያዩ ነበሩ። 13አም​ሳም የወ​ርቅ መያ​ዣ​ዎ​ችን ሠሩ፤ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ንም አን​ዱን ከሌ​ላው በመ​ያ​ዣ​ዎች አጋ​ጠ​ሙ​አ​ቸው፤ አንድ ድን​ኳ​ንም ሆነ። 14ከድ​ን​ኳ​ኑም በላይ የሚ​ሆኑ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ችን ከፍ​የል ጠጕር አደ​ረጉ፤ ዐሥራ አንድ መጋ​ረ​ጃ​ዎ​ች​ንም አደ​ረጉ። 15እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ርዝ​መቱ ሠላሳ ክንድ፥ እያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ ወርዱ አራት ክንድ ነበረ፤ የእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም መጋ​ረጃ መጠኑ ትክ​ክል ነበረ። 16አም​ስ​ቱ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች እርስ በር​ሳ​ቸው አንድ አደ​ረጉ፤ ስድ​ስ​ቱ​ንም መጋ​ረ​ጃ​ዎች አንድ አድ​ር​ገው አጋ​ጠ​ሙ​አ​ቸው። 17ከተ​ጋ​ጠ​ሙ​ትም መጋ​ረ​ጃ​ዎች በአ​ን​ደ​ኛው መጋ​ረጃ ጠርዝ ላይ አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን አደ​ረጉ፤ እን​ዲ​ሁም በሁ​ለ​ተ​ኛው መጋ​ረጃ ጠርዝ በሚ​ጋ​ጠ​ሙ​በት በኩል አምሳ ቀለ​በ​ቶ​ችን አደ​ረጉ። 18ድን​ኳ​ኑም አንድ እን​ዲ​ሆን ያጋ​ጥ​ሙት ዘንድ አምሳ የናስ መያ​ዣ​ዎ​ችን ሠሩ። 19ለድ​ን​ኳ​ኑም መደ​ረ​ቢያ ከቀይ አውራ በግ የተ​ለፋ ቍር​በት፥ ከዚ​ያም በላይ ሌላ መደ​ረ​ቢያ ከአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት#“ሌላ መደ​ረ​ቢያ ከአ​ቆ​ስጣ ቍር​በት” የሚ​ለው በግ​እዙ የለም። አደ​ረጉ።
20ለድ​ን​ኳ​ኑም ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት የሚ​ቆ​ሙ​ትን ሳን​ቆች አደ​ረጉ። 21የሳ​ን​ቃው ሁሉ ርዝ​መቱ ዐሥር ክንድ፥ ወር​ዱም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ። 22ለእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ አን​ዱን በአ​ንዱ ላይ የሚ​ያ​ያ​ይዙ ሁለት ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ነበሩ፤ ለድ​ን​ኳ​ኑም ሳን​ቆች ሁሉ እን​ዲሁ አደ​ረጉ። 23ለድ​ን​ኳ​ኑም በደ​ቡብ ወገን ሃያ ሳን​ቆ​ችን አደ​ረጉ፤ 24ከሃ​ያ​ውም ሳን​ቆች በታች አርባ የብር እግ​ሮች አደ​ረጉ፤ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች ለሁ​ለቱ ማጋ​ጠ​ሚ​ያ​ዎች ሁለት እግ​ሮች ነበሩ። 25ለድ​ን​ኳ​ኑም ለሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን በሰ​ሜን በኩል ሃያ ሳን​ቆች አደ​ረጉ፤ 26ለእ​ነ​ር​ሱም አርባ የብር እግ​ሮች፥ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች ሁለት እግ​ሮች አደ​ረጉ። 27ለድ​ን​ኳ​ኑም በም​ዕ​ራቡ ወገን በስ​ተ​ኋላ ስድ​ስት ሳን​ቆች አደ​ረጉ። 28ለድ​ን​ኳ​ኑም ለሁ​ለቱ ማዕ​ዘን በስ​ተ​ኋላ ሁለት ሳን​ቆች አደ​ረጉ። 29ከታ​ችም እስከ ላይ እስከ አን​ደ​ኛው ቀለ​በት ድረስ አንድ ሳንቃ ድርብ ነበረ፤ ለሁ​ለ​ቱም ማዕ​ዘን እን​ዲሁ ሁለት ነበሩ። 30ስም​ንት ሳን​ቆ​ችና ዐሥራ ስድ​ስቱ የብር እግ​ሮ​ቻ​ቸው፥ ከእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ሳንቃ በታች ሁለት ሁለት እግ​ሮች ነበሩ።
31ከማ​ይ​ነ​ቅዝ ዕን​ጨት በድ​ን​ኳኑ በአ​ን​ደ​ኛው ወገን ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ 32በድ​ን​ኳ​ኑም በሁ​ለ​ተ​ኛው ወገን ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ከድ​ን​ኳ​ኑም በስ​ተ​ኋላ በም​ዕ​ራቡ ወገን ላሉት ሳን​ቆች አም​ስት መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ችን አደ​ረጉ። 33መካ​ከ​ለ​ኛ​ው​ንም መወ​ር​ወ​ሪያ በሳ​ን​ቆቹ መካ​ከል ከዳር እስከ ዳር እን​ዲ​ያ​ልፍ አደ​ረጉ። 34ሳን​ቆ​ቹ​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጡ​አ​ቸው፤ ቀለ​በ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም የመ​ወ​ር​ወ​ሪያ ቤት እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ቸው ከወ​ርቅ አደ​ረጉ፤ መወ​ር​ወ​ሪ​ያ​ዎ​ቹ​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጡ​አ​ቸው። 35መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከተ​ፈ​ተ​ለም ከጥሩ በፍታ አደ​ረጉ፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንም በጥ​ልፍ ሥራ በእ​ርሱ ላይ አደ​ረጉ። 36ከማ​ይ​ነ​ቅ​ዝም ዕን​ጨት አራት ምሰ​ሶ​ዎች አደ​ረ​ጉ​ለት፤በወ​ር​ቅም ለበ​ጡ​አ​ቸው፤ ኵላ​ቦ​ቻ​ቸ​ውም የወ​ርቅ ነበሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አራት የብር እግ​ሮች አደ​ረጉ። 37ለድ​ን​ኳ​ኑም ደጃፍ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከተ​ፈ​ተ​ለም ከጥሩ በፍታ በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መጋ​ረጃ አደ​ረጉ፤ 38አም​ስ​ቱ​ንም ምሰ​ሶ​ዎች፥ ኵላ​ቦ​ቻ​ቸ​ው​ንም አደ​ረጉ፤ ጉል​ላ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንና ዘን​ጎ​ቻ​ቸ​ው​ንም በወ​ርቅ ለበ​ጡ​አ​ቸው፤ አም​ስ​ቱም እግ​ሮ​ቻ​ቸው የናስ ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ