የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፀ​አት 7

7
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ እኔ ለፈ​ር​ዖን አም​ላክ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ወን​ድ​ም​ህም አሮን ነቢይ ይሆ​ን​ል​ሃል። 2ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ነገር ሁሉ አንተ ትነ​ግ​ረ​ዋ​ለህ፤ ወን​ድ​ም​ህም አሮን የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሀ​ገሩ ይለ​ቅቅ ዘንድ ለፈ​ር​ዖን ይን​ገ​ረው። 3እኔም የፈ​ር​ዖ​ንን ልብ አጸ​ና​ለሁ፤ በግ​ብፅ ምድ​ርም ድን​ቄ​ንና ተአ​ም​ራ​ቴን አበ​ዛ​ለሁ። 4ፈር​ዖ​ንም አይ​ሰ​ማ​ች​ሁም፤ እጄ​ንም በግ​ብፅ ላይ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሕዝ​ቤን በኀ​ይሌ በታ​ላቅ ፍርድ ከግ​ብፅ ሀገር አወ​ጣ​ለሁ። 5ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጄን በግ​ብፅ ላይ በዘ​ረ​ጋሁ ጊዜ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በአ​ወ​ጣሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።” 6ሙሴና አሮ​ንም እን​ዲህ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው አደ​ረጉ። 7ፈር​ዖ​ን​ንም በተ​ና​ገ​ሩት ጊዜ ሙሴ ሰማ​ንያ ዓመት ሆኖት ነበር፤ አሮ​ንም ሰማ​ንያ ሦስት ዓመት ሆኖት ነበረ።
የአ​ሮን ተአ​ም​ራ​ዊት በትር
8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ራ​ቸው፦ 9“ፈር​ዖን፦ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን አሳ​ዩኝ ሲላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ምህ አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ወስ​ደህ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ጣላት’ በለው፤ እባ​ብም ትሆ​ና​ለች።” 10ሙሴና አሮ​ንም ወደ ፈር​ዖን ገቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ አሮ​ንም በት​ሩን በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ጣለ፤ እባ​ብም ሆነች። 11ፈር​ዖ​ንም ጠቢ​ባ​ን​ንና መተ​ተ​ኞ​ችን ጠራ፤ የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ ደግሞ አደ​ረጉ። 12እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ውም በት​ራ​ቸ​ውን ጣሉ፤ እባ​ቦ​ችም ሆኑ፤ የአ​ሮን በትር ግን በት​ራ​ቸ​ውን ዋጠች። 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ የፈ​ር​ዖን ልብ ጸና፤ መስ​ማ​ት​ንም እንቢ አለ።
ዐሥሩ መቅ​ሠ​ፍ​ታት
1፥ የውኃ ወደ ደም መለ​ወጥ
14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሕዝ​ቡን እን​ዳ​ይ​ለ​ቅቅ የፈ​ር​ዖን ልብ ደነ​ደነ። 15ማል​ደህ ወደ ፈር​ዖን ሂድ፤ እነሆ፥ ወደ ውኃ ይወ​ጣል፤ ትገ​ና​ኘ​ውም ዘንድ አንተ በወ​ንዝ ዳር ትቆ​ማ​ለህ፤ እባ​ብም ሆና የተ​ለ​ወ​ጠ​ች​ዉን በትር በእ​ጅህ ትወ​ስ​ዳ​ለህ። 16እን​ዲ​ህም ትለ​ዋ​ለህ፦ ‘የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፦ በም​ድረ በዳ እን​ዲ​ያ​መ​ል​ኩኝ ሕዝ​ቤን ልቀቅ’ ብሎ ወደ አንተ ላከኝ፤ እነ​ሆም፥ እስከ ዛሬ አል​ሰ​ማ​ህም። 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ በዚህ ታው​ቃ​ለህ፤ እነሆ፥ እኔ የወ​ን​ዙን ውኃ በእጄ ባለ​ችው በትር እመ​ታ​ለሁ፤ ውኃ​ውም ወደ ደም ይለ​ወ​ጣል። 18በወ​ን​ዙም ያሉት ዓሦች ይሞ​ታሉ፤ ወን​ዙም ይገ​ማል፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም የወ​ን​ዙን ውኃ ለመ​ጠ​ጣት አይ​ች​ሉም።” 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ወን​ድ​ምህ አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ውሰድ፤ በግ​ብፅ ውኆች፥ በወ​ን​ዞ​ቻ​ቸው፥ በመ​ስ​ኖ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በኩ​ሬ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ በውኃ ማከ​ማ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ላይ እጅ​ህን ዘርጋ’ በለው፤ ደምም ይሆ​ናል፤” በግ​ብ​ፅም ሀገር ሁሉ በዕ​ን​ጨት ዕቃና በድ​ን​ጋይ ዕቃ ሁሉ ደም ሆነ።
20ሙሴና አሮ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ አሮ​ንም በት​ሩን አነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት የወ​ን​ዙን ውኃ መታ፤ የወ​ን​ዙም ውኃ ሁሉ ተለ​ውጦ ደም ሆነ። 21በወ​ን​ዙም የነ​በሩ ዓሦች ሞቱ፤ ወን​ዙም ገማ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ከወ​ንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አል​ቻ​ሉም፤ ደሙም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ሆነ። 22የግ​ብ​ፅም ጠን​ቋ​ዮች በአ​ስ​ማ​ታ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ የፈ​ር​ዖን ልብ ጸና፤ አል​ሰ​ማ​ቸ​ው​ምም። 23ፈር​ዖ​ንም ተመ​ልሶ ወደ ቤቱ ገባ፤ በዚ​ህም ሁሉ ልቡ አል​ተ​መ​ለ​ሰም። 24ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም ሁሉ ከወ​ንዙ ውኃ ይጠጡ ዘንድ አል​ቻ​ሉ​ምና በወ​ንዙ ዳር ውኃ ሊጠጡ ቈፈሩ። 25እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወን​ዙን ከመታ በኋላ ሰባት ቀን ተፈ​ጸመ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ