ትንቢተ ሕዝቅኤል 15
15
የወይን ተክል ምሳሌ
1የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦ 2“የሰው ልጅ ሆይ! የወይን ግንድ ከዱር ዛፎች ሁሉና ከዱር ዛፎች ቅርንጫፎች ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድን ነው? 3በውኑ ሥራ የሚሠራበትን እንጨት ከእርሱ ይወስዳሉን? ወይስ ሰዎች ዕቃ የሚንጠለጠልበትን ኩላብ ከእርሱ ይወስዳሉን? 4እነሆ ለመቃጠል በእሳት ላይ ተጥሎአል፤ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹን በልቶአል፤#“እሳቱም ሁለቱን ጫፎች በልቶአል” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። መካከሉም ተቃጥሎአል፤ በውኑ ለሥራ ይጠቅማልን? 5ከውፍረቱም የተነሣ ለሥራ አይሆንም፤ ለምትበላና ለምታጠፋ እሳት ይሆናል እንጂ ከዚያ በኋላ በውኑ ለሥራ ይሆናልን? 6ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በዱር ዛፎች መካከል ያለውን የወይን ግንድ እሳት ይበላው ዘንድ እንደ ሰጠሁት፥ እንዲሁ በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን አሳልፌ እሰጣለሁ። 7ፊቴንም በእነርሱ ላይ አጸናለሁ፤ ከእሳትም አይወጡም፤#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ይወጣሉ” ይላል። እሳትም ይበላቸዋል፤ ፊቴንም በእነርሱ ላይ በአጸናሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። 8ዐመፅን አድርገዋልና ምድሪቱን ባድማ አደርጋለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 15: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ