የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 18

18
“ኀጢ​አት የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች”
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 2“በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፦ ‘አባ​ቶች ጨርቋ የወ​ይን ፍሬ በሉ፥ የል​ጆ​ችም ጥር​ሶች ጠረሱ’ ብላ​ችሁ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ የም​ት​መ​ስ​ሉት ምሳሌ ምን​ድን ነው? 3እኔ ሕያው ነኝ! እን​ግ​ዲህ ወዲህ ይህን ምሳሌ በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ አት​መ​ስ​ሉ​ትም፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 4እነሆ ነፍ​ሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአ​ባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እን​ዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢ​አት የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች።
5“ሰውም ጻድቅ ቢሆን ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ፤ 6በተ​ራ​ራም ላይ ባይ​በላ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ጣዖ​ታት ባያ​ነሣ፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሚስት ባያ​ረ​ክስ፥ አደ​ፍም ወዳ​ለ​ባት ሴት ባይ​ቀ​ርብ፤ 7ሰው​ንም ባያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ለባለ ዕዳም መያ​ዣ​ውን ቢመ​ልስ፥ ፈጽ​ሞም ባይ​ቀማ፥ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ለተ​ራበ ቢሰጥ፥ የተ​ራ​ቈ​ተ​ው​ንም ከል​ብሱ ቢያ​ለ​ብስ፤ 8በአ​ራጣ ባያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ባይ​ወ​ስድ፥ እጁ​ንም ከኀ​ጢ​አት ቢመ​ልስ፥ በሰ​ውና በሰው መካ​ከ​ልም የእ​ው​ነ​ትን ፍርድ ቢፈ​ርድ፥ 9በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እው​ነ​ት​ንም ለማ​ድ​ረግ ፍር​ዴን ቢጠ​ብቅ፥ እርሱ ጻድቅ ነው፤ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
10“እር​ሱም ቀማ​ኛና ደም አፍ​ሳሽ ልጅን፥ ከዚ​ህም ሁሉ አን​ዳ​ቸ​ውን የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ቢወ​ልድ፥ 11እር​ሱም በጻ​ድቅ አባቱ መን​ገድ ባይ​ሄድ፥ በተ​ራ​ራም ላይ ቢበላ፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሚስት ቢያ​ረ​ክስ፥ 12ድሀ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ውን ቢያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ ቢቀ​ማም፥ መያ​ዣ​ው​ንም ባይ​መ​ልስ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ ጣዖ​ታት ቢያ​ነሣ፥ ርኩ​ስ​ንም ነገር ቢያ​ደ​ርግ፥ 13በአ​ራጣ ቢያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ቢወ​ስድ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሰው በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም፤ ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ይሞ​ታል፤ ደሙም በላዩ ይሆ​ናል።
14“እነ​ሆም ልጅ ቢወ​ልድ፥ እር​ሱም አባቱ የሠ​ራ​ውን ኀጢ​አት አይቶ ቢፈራ፥ እን​ደ​ር​ሱም ባይ​ሠራ፥ 15በተ​ራራ ላይ ባይ​በላ፥ ዐይ​ኖ​ቹ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል ቤት ጣዖ​ታት ባያ​ነሣ፥ የባ​ል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም ሚስት ባያ​ረ​ክስ፤ 16ሰው​ንም ባያ​ስ​ጨ​ንቅ፥ መያ​ዣ​ው​ንም ባይ​ወ​ስድ፥ ባይ​ቀ​ማም፥ ከእ​ን​ጀ​ራ​ውም ለተ​ራበ ቢሰጥ፥ ለተ​ራ​ቈ​ተ​ውም ልብ​ስን ቢያ​ለ​ብስ፥ 17እጁ​ንም ከዐ​መፅ ቢመ​ልስ፥ አራ​ጣ​ንም አት​ርፎ ባይ​ወ​ስድ፥ ፍር​ዴ​ንም ቢያ​ደ​ርግ፥ በት​እ​ዛ​ዜም ቢሄድ፥ እርሱ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ በአ​ባቱ ኀጢ​አት አይ​ሞ​ትም። 18አባቱ ግን ፈጽሞ በድ​ሎ​አ​ልና፥ ወን​ድ​ሙ​ንም ቀም​ቶ​አ​ልና፥ በሕ​ዝ​ቡም መካ​ከል ክፉን ነገር አድ​ር​ጎ​አ​ልና እነሆ እርሱ በበ​ደሉ ይሞ​ታል።
19“እና​ንተ ግን፦ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት ስለ ምን አይ​ሸ​ከ​ምም? ትላ​ላ​ችሁ። ልጅ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን በአ​ደ​ረገ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ በጠ​በ​ቀና በአ​ደ​ረገ ጊዜ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል። 20ኀጢ​አ​ትን የም​ት​ሠራ ነፍስ እር​ስዋ ትሞ​ታ​ለች፤ ልጅ የአ​ባ​ቱን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ አባ​ትም የል​ጁን ኀጢ​አት አይ​ሸ​ከ​ምም፤ የጻ​ድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ የኀ​ጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ኀጢ​አት በራሱ ላይ ይሆ​ናል።
21“ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከአ​ደ​ረ​ጋት ኀጢ​አት ሁሉ ቢመ​ለስ፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ሁሉ ቢጠ​ብቅ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም። 22የበ​ደ​ለው በደል ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​በ​ትም፤ በሠ​ራው ጽድቅ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል። 23በውኑ ኀጢ​አ​ተኛ ይሞት ዘንድ መፍ​ቀ​ድን እፈ​ቅ​ዳ​ለ​ሁን? ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከክፉ መን​ገዱ ይመ​ለ​ስና በሕ​ይ​ወት ይኖር ዘንድ ነው እንጂ። 24ጻድቁ ግን ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም ቢሠራ፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ገው ርኵ​ሰት ሁሉ ቢያ​ደ​ርግ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ልን? የሠ​ራው ጽድቅ ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም፤ በአ​ደ​ረ​ገው ዐመ​ፅና በሠ​ራት ኀጢ​አት በዚ​ያች ይሞ​ታል።
25“እና​ንተ ግን፦ የጌታ መን​ገድ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ችም ትላ​ላ​ችሁ። የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እን​ግ​ዲህ ስሙ፤ በውኑ መን​ገዴ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ይል​ቅስ የእ​ና​ንተ መን​ገድ ያል​ቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? 26ጻድቁ ከጽ​ድቁ ቢመ​ለስ፥ ኀጢ​አ​ት​ንም በሠራ ጊዜ፥ በዚያ ቢሞት፥ እርሱ በአ​ደ​ረ​ገው በደል ይሞ​ታል። 27ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም ከሠ​ራው ኀጢ​አት ቢመ​ለስ፥ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ር​ንም ቢያ​ደ​ርግ ነፍ​ሱን ይጠ​ብ​ቃል። 28ከሠ​ራው ሁሉ በደል አይቶ ተመ​ል​ሶ​አ​ልና ፈጽሞ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም። 29ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት፦ የጌታ መን​ገድ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ችም ይላሉ። የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በውኑ መን​ገዴ የቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? ይል​ቅስ የእ​ና​ንተ መን​ገድ ያል​ቀ​ናች አይ​ደ​ለ​ች​ምን? 30የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ​ዚህ እንደ መን​ገዱ በየ​ሰዉ ሁሉ እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንስሓ ግቡ፤ ኀጢ​አ​ትም ዕን​ቅ​ፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ባ​ችሁ ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ሁሉ ተመ​ለሱ። 31የበ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን በደል ሁሉ ከእ​ና​ንተ ጣሉ፤ አዲስ ልብና አዲስ መን​ፈ​ስ​ንም ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ ምን ትሞ​ታ​ላ​ችሁ? 32የም​ዋ​ቹን ሞት አል​ፈ​ቅ​ድ​ምና፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ስለ​ዚህ በን​ስሓ ተመ​ለ​ሱና በሕ​ይ​ወት ኑሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ