ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 33:12-16

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 33:12-16 አማ2000

አን​ተም የሰው ልጅ ሆይ! የሕ​ዝ​ብ​ህን ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፦ በበ​ደ​ለ​በት ቀን የጻ​ድቅ ጽድቁ አያ​ድ​ነ​ውም፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛም ከኀ​ጢ​አቱ በተ​መ​ለ​ሰ​በት ቀን በኀ​ጢ​አቱ አይ​ሰ​ና​ከ​ልም፤ ጻድ​ቁም ኀጢ​አት በሠ​ራ​በት ቀን በጽ​ድቁ በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም። እኔ ጻድ​ቁን፦ በር​ግጥ በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ በጽ​ድቁ ታምኖ ኀጢ​አት ቢሠራ በሠ​ራው ኀጢ​አት ይሞ​ታል እንጂ ጽድቁ አይ​ታ​ሰ​ብ​ለ​ትም። እኔም ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን፦ በር​ግጥ ትሞ​ታ​ለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ ከኀ​ጢ​አቱ ተመ​ልሶ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን ቢያ​ደ​ርግ፤ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውም መያ​ዣን ቢመ​ልስ፥ የነ​ጠ​ቀ​ው​ንም ቢከ​ፍል፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ትእ​ዛዝ ቢሄድ፥ ኀጢ​አ​ትም ባይ​ሠራ፥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል እንጂ አይ​ሞ​ትም። የሠ​ራ​ውም ኀጢ​አት ሁሉ አይ​ታ​ሰ​ብ​በ​ትም፤ ፍር​ድ​ንና ቅን ነገ​ርን አድ​ር​ጎ​አ​ልና፤ በእ​ር​ግጥ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል።