የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 37

37
1የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በላዬ ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በመ​ን​ፈሱ አወ​ጣኝ፤ አጥ​ን​ቶ​ችም በሞ​ሉ​በት ሸለቆ መካ​ከል አኖ​ረኝ። 2በእ​ነ​ር​ሱም አን​ጻር በዙ​ሪ​ያ​ቸው አዞ​ረኝ፤ እነ​ሆም በሜ​ዳው እጅግ ነበሩ፤ እነ​ሆም እጅግ ደር​ቀው ነበር። 3እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራ​ሉን?” አለኝ። እኔም፥ “ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ! አንተ ታው​ቃ​ለህ” አልሁ። 4እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “በእ​ነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች ላይ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ እና​ንተ የደ​ረ​ቃ​ችሁ አጥ​ን​ቶች ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ። 5ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በእ​ና​ንተ ላይ የሕ​ይ​ወ​ትን መን​ፈስ አመ​ጣ​ለሁ።#ዕብ. “ትን​ፋ​ሽን አገ​ባ​ባ​ች​ኋ​ለሁ ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ” ይላል። 6ጅማ​ት​ንም እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ሥጋ​ንም አወ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በእ​ና​ን​ተም ላይ ቍር​በ​ትን እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ ትን​ፋ​ሽ​ንም አገ​ባ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።”
7እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም ትን​ቢት ተና​ገ​ርሁ፤ ስና​ገ​ርም ድምፅ ሆነ፤ እነ​ሆም መና​ወጥ ሆነ፤ አጥ​ን​ቶ​ች​ንም እየ​ራሱ በሆነ በሰ​ው​ነቱ ከአ​ጥ​ን​ቶች ጋር አንድ አደ​ረ​ጋ​ቸው። 8እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም ጅማት ነበ​ረ​ባ​ቸው፤ ሥጋም ወጣ፤ ቍር​በ​ትም በላ​ያ​ቸው ተዘ​ረጋ፤ ትን​ፋሽ ግን አል​ነ​በ​ረ​ባ​ቸ​ውም። 9እር​ሱም፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋስ ትን​ቢት ተና​ገር፤ ለነ​ፋ​ስም፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ነፋስ ሆይ! ከአ​ራቱ ነፋ​ሳት ዘንድ ና፤ እነ​ዚህ ሙታን በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እፍ በል​ባ​ቸው በል” አለኝ። 10እን​ዳ​ዘ​ዘ​ኝም ትን​ቢት ተና​ገ​ርሁ፤ ትን​ፋ​ሽም ገባ​ባ​ቸው፤ ሕያ​ዋ​ንም ሆኑ፤ እጅ​ግም ታላቅ ሠራ​ዊት ሆነው በእ​ግ​ራ​ቸው ቆሙ።
11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ተና​ገ​ረኝ፤ እን​ዲ​ህም አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! እነ​ዚህ አጥ​ን​ቶች የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ናቸው፤ እነሆ! አጥ​ን​ቶ​ቻ​ችን ደር​ቀ​ዋል፤ ተስ​ፋ​ች​ንም ጠፍ​ቶ​አል፤ ፈጽ​መ​ንም ተቈ​ር​ጠ​ናል ብለ​ዋል። 12ስለ​ዚህ ትን​ቢት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በላ​ቸው፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሕዝቤ ሆይ! እነሆ መቃ​ብ​ራ​ች​ሁን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ከመ​ቃ​ብ​ራ​ች​ሁም አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አገ​ባ​ች​ኋ​ለሁ። 13ሕዝቤ ሆይ! መቃ​ብ​ራ​ች​ሁን በከ​ፈ​ትሁ ጊዜ፥ ከመ​ቃ​ብ​ራ​ች​ሁም በአ​ወ​ጣ​ኋ​ችሁ ጊዜ፥ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 14መን​ፈ​ሴ​ንም በው​ስ​ጣ​ችሁ አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ እና​ን​ተም በሕ​ይ​ወት ትኖ​ራ​ላ​ችሁ፤ በገዛ ምድ​ራ​ች​ሁም አኖ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ርሁ፥ እን​ዳ​ደ​ረ​ግ​ሁም ታው​ቃ​ላ​ችሁ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”
የይ​ሁ​ዳና የእ​ስ​ራ​ኤል መን​ግ​ሥት አንድ ስለ መሆኑ
15የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ወደ እኔ እን​ዲህ ሲል መጣ፦ 16“አንተ የሰው ልጅ ሆይ! አንድ በትር ውሰ​ድና፦ ይሁ​ዳ​ንና ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹን፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች በላዩ ጻፍ፤ ሌላም በትር ውሰ​ድና፦ የኤ​ፍ​ሬም በትር ለዮ​ሴ​ፍና ለባ​ል​ን​ጀ​ሮቹ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ብለህ በላዩ ጻፍ። 17አንድ በት​ርም እን​ዲ​ሆኑ አን​ዱን ከሁ​ለ​ተ​ኛው ጋር ለአ​ንተ አጋ​ጥም፤ በእ​ጅ​ህም ውስጥ አንድ ይሁኑ። 18የሕ​ዝ​ብ​ህም ልጆች፦ ይህ የም​ታ​ደ​ር​ገው ነገር ምን ማለት እንደ ሆነ አት​ነ​ግ​ረ​ን​ምን? ብለው በተ​ና​ገ​ሩህ ጊዜ፥ አንተ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ 19እነሆ በኤ​ፍ​ሬም እጅ ያለ​ውን የዮ​ሴ​ፍን በትር ባል​ን​ጀ​ሮ​ቹ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገ​ዶች እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ከእ​ር​ሱም ከይ​ሁዳ በትር ጋር አጋ​ጥ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አንድ በት​ርም አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በእ​ጄም ውስጥ አንድ ይሆ​ናሉ በላ​ቸው። 20የም​ት​ጽ​ፍ​ባ​ቸ​ውም በት​ሮች በፊ​ታ​ቸው በእ​ጅህ ውስጥ ይሆ​ናሉ። 21አን​ተም እን​ዲህ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከገ​ቡ​ባ​ቸው ከአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እወ​ስ​ዳ​ለሁ፤ ከስ​ፍ​ራም ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እስ​ራ​ኤ​ልም ምድር አመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ 22በም​ድ​ርም ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ተራ​ሮች ላይ አንድ ሕዝብ አደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለሁ፥ አንድ ንጉ​ሥም በሁ​ላ​ቸው ላይ ይነ​ግ​ሣል፤ ከዚያ ወዲያ ሁለት ሕዝብ አይ​ሆ​ኑም፤ ከዚያ ወዲ​ያም ሁለት መን​ግ​ሥት ሆነው አይ​ለ​ያ​ዩም። 23ከዚያ ወዲ​ያም በጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውና በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸው፥ በመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም#“በር​ኵ​ሰ​ታ​ቸ​ውም፥ በመ​ተ​ላ​ለ​ፋ​ቸ​ውም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ሁሉ አይ​ረ​ክ​ሱም፤ ኀጢ​አ​ትም ከሠ​ሩ​ባት ዐመፅ ሁሉ አድ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አነ​ጻ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ ሕዝ​ብም ይሆ​ኑ​ኛል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ።
24“ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት በላ​ያ​ቸው ንጉሥ ይሆ​ናል፤ ለሁ​ሉም አንድ እረኛ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ በፍ​ር​ዴም ይሄ​ዳሉ ትእ​ዛ​ዜ​ንም ይጠ​ብ​ቃሉ፤ ያደ​ር​ጓ​ት​ማል። 25አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በኖ​ሩ​ባት፤ ለባ​ሪ​ያዬ ለያ​ዕ​ቆብ በሰ​ጠ​ኋት ምድር ይኖ​ራሉ፤ እነ​ር​ሱና ልጆ​ቻ​ቸው፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም#“እነ​ር​ሱና ልጆ​ቻ​ቸው፥ የልጅ ልጆ​ቻ​ቸ​ውም” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይኖ​ሩ​ባ​ታል፤ ባሪ​ያ​ዬም ዳዊት ለዘ​ለ​ዓ​ለም አለቃ ይሆ​ና​ቸ​ዋል። 26የሰ​ላ​ምም ቃል ኪዳን ከእ​ነ​ርሱ ጋር አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ቃል ኪዳን ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ እኔም እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ አበ​ዛ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤#“እኔ እባ​ር​ካ​ቸ​ዋ​ለሁ አበ​ዛ​ቸ​ዋ​ለ​ሁም” የሚ​ለው በዕብ. ብቻ። መቅ​ደ​ሴ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አኖ​ራ​ለሁ። 27ማደ​ሪ​ያ​ዬም በላ​ያ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ እኔም አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል። 28መቅ​ደ​ሴም ለዘ​ለ​ዓ​ለም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በሆነ ጊዜ፥ እኔ እስ​ራ​ኤ​ልን የም​ቀ​ድ​ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ አሕ​ዛብ ያው​ቃሉ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ