የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 41

41
1ወደ መቅ​ደ​ሱም አገ​ባኝ፤ የግ​ን​ቡ​ንም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድ​ስት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን ስድ​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ። 2የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ወርድ ዐሥር ክንድ ነበረ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም መቃ​ኖች በዚህ ወገን አም​ስት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን አም​ስት ክንድ ነበሩ፤ ርዝ​መ​ቱ​ንም አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካ።
3ወደ ውስ​ጥም ገባ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ው​ንም የግ​ንብ አዕ​ማድ ወርድ ሁለት ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ወርድ ስድ​ስት ክንድ ነበረ፤ የመ​ግ​ቢ​ያ​ውም ግንብ ወርድ በዚህ ወገን ሰባት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን ሰባት ክንድ ነበረ። 4በመ​ቅ​ደ​ሱም ፊት ርዝ​መ​ቱን አርባ ክንድ፥ ወር​ዱ​ንም ሃያ ክንድ አድ​ርጎ ለካና፥ “ይህ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን ነው” አለኝ።
5የመ​ቅ​ደ​ሱ​ንም ግንብ ስድ​ስት ክንድ፥ በመ​ቅ​ደ​ሱም ዙሪያ ሁሉ ያሉ​ትን የጓ​ዳ​ዎ​ቹን ሁሉ ወርድ አራት ክንድ አድ​ርጎ ለካ። 6ጓዳ​ዎ​ቹም አንዱ ከአ​ንዱ በላይ በሦ​ስት ደርብ ነበሩ፤ በእ​ያ​ን​ዳ​ን​ዱም ደርብ ሠላሳ ጓዳ​ዎች ነበሩ። በመ​ቅ​ደ​ሱም ግንብ ዙሪያ ደገ​ፋ​ዎች ይሆኑ ዘንድ አረ​ፍ​ቶች ነበሩ፤ ከመ​ቅ​ደሱ ግንብ ጋር ግን​አ​ል​ተ​ያ​ያ​ዙም ነበር። 7በቤ​ቱም ዙሪያ ባለ ግንብ ውስጥ በነ​በ​ሩት አረ​ፍ​ቶች ምክ​ን​ያት ላይ​ኞቹ ጓዳ​ዎች ከታ​ች​ኞቹ ጓዳ​ዎች ይበ​ልጡ ነበር፤ ከታ​ች​ኛ​ውም ደርብ ወደ መካ​ከ​ለ​ኛው፥ ከመ​ካ​ከ​ለ​ኛ​ውም ደርብ ወደ ሦስ​ተ​ኛው የሚ​ወ​ጣ​በት ደረጃ ነበረ። 8ለመ​ቅ​ደ​ሱም ከፍ ያለ ወለል በዙ​ሪ​ያው እን​ዳ​ለው አየሁ፤ የጓ​ዳ​ዎ​ቹም መሠ​ረት ቁመቱ ሙሉ ዘንግ የሚ​ያ​ህል ስድ​ስት ክንድ ነበረ። 9የጓ​ዳ​ዎ​ቹም የው​ጭው ግንብ ወርድ አም​ስት ክንድ ነበረ፤ በመ​ቅ​ደ​ሱም ጓዳ​ዎች አጠ​ገብ የቀረ አንድ ባዶ ስፍራ ነበረ። 10በዕቃ ቤቶ​ቹም መካ​ከል ወርዱ በቤቱ ዙሪያ ሁሉ ሃያ ክንድ ነበረ። 11የጓ​ዳ​ዎ​ቹም መግ​ቢያ ብቻ​ውን ወደ​ሚ​ኖ​ረው ስፍራ ነበረ፤ አንዱ ደጅ ወደ ሰሜን መን​ገድ፤ አን​ዱም ደጅ ወደ ደቡብ መን​ገድ፥ ብቻ​ውን የሚ​ኖ​ረው ስፍራ ወርዱ አም​ስት ክንድ በዙ​ሪ​ያው ነበር።
12በም​ዕ​ራ​ብም በኩል በልዩ ስፍራ አን​ጻር የነ​በረ ግቢ ስፋቱ ሰባ ክንድ ነበረ። በግ​ቢ​ውም ዙሪያ የነ​በረ ግንብ ወርዱ አም​ስት ክንድ፥ ርዝ​መ​ቱም ዘጠና ክንድ ነበረ።
13የቤተ መቅ​ደ​ሱ​ንም ርዝ​መት መቶ ክንድ፥ የል​ዩ​ውን ስፍ​ራና ግቢ​ውን ከግ​ንቡ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ። 14ደግ​ሞም በም​ሥ​ራቅ በኩል የነ​በ​ረ​ውን የቤተ መቅ​ደ​ሱ​ንና የል​ዩ​ውን ስፍራ ወር​ድና ቁመት አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ። 15ወደ​ኋ​ላ​ውም በአ​ለው በልዩ ስፍራ አን​ጻር የነ​በ​ረ​ውን የግ​ቢ​ውን ርዝ​መት፥ በዚ​ህና በዚያ ከነ​በ​ሩት ከግ​ን​ቦቹ ጋር አንድ መቶ ክንድ አድ​ርጎ ለካ፤ የው​ስ​ጡ​ንም መቅ​ደስ፥ የአ​ዳ​ራ​ሹ​ንም መዛ​ነ​ቢ​ያ​ዎች ለካ።
16መድ​ረ​ኮቹ፥ መስ​ኮ​ቶ​ቹና አዕ​ማዱ፥ በስ​ተ​ው​ስጥ ያለው ክፍል ደጀ ሰላ​ሙም በእ​ን​ጨት ተለ​ብ​ጠው ነበር፤ በሦ​ስ​ቱም ዙሪያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶች ነበሩ። መቅ​ደ​ሱም በመ​ድ​ረኩ አን​ጻር ከመ​ሬት ጀምሮ እስከ መስ​ኮ​ቶቹ ድረስ በእ​ን​ጨት ተለ​ብጦ ነበር፤ መስ​ኮ​ቶ​ቹም የዐ​ይነ ርግብ ነበሩ፤ 17በደ​ጁም ላይ እስከ ውስ​ጠ​ኛው ክፍል ድረስ፥ በው​ጭም ግንቡ ሁሉ ውስ​ጡም፥ ውጭ​ውም ዙሪ​ያ​ውን ተለ​ብጦ ነበር። 18ኪሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባ​ባው ዛፎች ተቀ​ር​ጸ​ው​በት ነበር፤ የዘ​ን​ባ​ባ​ውም ዛፍ ከኪ​ሩ​ብና ከኪ​ሩብ መካ​ከል ነበረ፤ ለእ​ያ​ን​ዳ​ዱም ኪሩብ ሁለት ፊት ነበ​ረው። 19በአ​ንድ ወገን ወደ አለው የዘ​ን​ባባ ዛፍ የሰው ፊት ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በሌ​ላ​ውም ወገን ወደ አለው ዘን​ባባ የአ​ን​በሳ ፊት ይመ​ለ​ከት ነበር፤ በቤቱ ሁሉ ዙሪያ እን​ደ​ዚህ ተቀ​ርጾ ነበር። 20ከመ​ሬት አን​ሥቶ እስከ ደጁ ራስ ድረስ ኪሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባባ ዛፎች ተቀ​ር​ጸው ነበር፤ የመ​ቅ​ደሱ ግንብ እን​ደ​ዚህ ነበረ።
21የመ​ቅ​ደሱ መቃ​ኖ​ችም አራት ማዕ​ዘን ነበሩ፤ የመ​ቅ​ደሱ ፊትም መልኩ እን​ደ​ሌ​ላው መልክ ነበረ። 22መሠ​ዊ​ያ​ውም ቁመቱ ሦስት ክንድ፥ ርዝ​መቱ ሁለት ክንድ፥ ወር​ዱም ሁለት ክንድ ሆኖ ከእ​ን​ጨት ተሠ​ርቶ ነበር፤ ማዕ​ዘ​ኖ​ቹም፥ እግ​ሩም፥ አገ​ዳ​ዎ​ቹም ከእ​ን​ጨት ተሠ​ር​ተው ነበር፤ እር​ሱም፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያለ​ችው ገበታ ይህች ናት” አለኝ። 23ለመ​ቅ​ደ​ሱና ለተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ሁለት መዝ​ጊ​ያ​ዎች ነበ​ሩ​አ​ቸው። 24ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ መዝ​ጊ​ያም ሁለት ተዘ​ዋ​ዋሪ ሳን​ቃ​ዎች ነበ​ሩት፤ ለአ​ንዱ መዝ​ጊያ ሁለት፥ ለሌ​ላ​ውም መዝ​ጊያ ሁለት ሳን​ቃ​ዎች ነበ​ሩት። 25በግ​ን​ቡም ላይ በተ​ቀ​ረ​ጹት ዓይ​ነት በእ​ነ​ዚህ በመ​ቅ​ደሱ መዝ​ጊ​ያ​ዎች ላይ ኪሩ​ቤ​ልና የዘ​ን​ባባ ዛፎች ተቀ​ር​ጸው ነበር፤ በስ​ተ​ው​ጭም በአ​ለው በደጀ ሰላሙ ፊት የእ​ን​ጨት መድ​ረክ ነበረ። 26በደጀ ሰላ​ሙም በሁ​ለቱ ወገን በዚ​ህና በዚያ የዐ​ይነ ርግብ መስ​ኮ​ቶ​ችና የተ​ቀ​ረጹ የዘ​ን​ባባ ዛፎች ነበ​ሩ​በት፤ የመ​ቅ​ደ​ሱም ጓዳ​ዎ​ችና የእ​ን​ጨቱ መድ​ረክ እን​ዲሁ ነበሩ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ