ትንቢተ ሕዝቅኤል 42
42
1በውጭም አደባባይ በሰሜኑ መንገድ በምሥራቅ በኩል አወጣኝ፤ በልዩውም ስፍራ አንጻርና በሰሜን በኩል በአለው ግቢ ፊት ለፊት ወዳሉት አምስት ዕቃ ቤቶች አገባኝ። 2መቶ ክንድ በሆነው ርዝመት ፊት በሰሜን በኩል መዝጊያ ነበረ፤ ወርዱም አምሳ ክንድ ነበረ። 3በውስጠኛውም አደባባይ በሃያው ክንድ አንጻር፥ በውጭውም አደባባይ በወለሉ አንጻር በሦስት ደርብ በትይዩ የተሠራ መተላለፊያ ነበረ። 4በዕቃ ቤቶቹም ፊት በስተውስጥ ወርዱ ዐሥር ክንድ፥ ርዝመቱ መቶ ክንድ የሆነ መንገድ ነበረ፤ መግቢያዎቻቸውም ወደ ሰሜን ይመለከቱ ነበር። 5መተላለፊያውም አሳጥሮአቸዋልና ላይኞቹ ዕቃ ቤቶች ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ አጫጭር ነበሩ። 6በሦስትም ደርብ ተሠርተው ነበርና፥ በአደባባዩም እንዳሉት አዕማድ፥ አዕማድ አልነበሩላቸውምና ስለዚህ ከመካከለኞቹና ከታችኞቹ ይልቅ ጠባብ ነበሩ። 7በውጭ በዕቃ ቤቶቹ አጠገብ ያለው፥ ወደ ውጭው አደባባይ የሚያመለክተው ቅጥር፥ በዕቃ ቤቶች ትይዩ የሆነ ርዝመቱ አምሳ ክንድ ነበረ። 8በመቅደሱ ፊት የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው መቶ ክንድ ሲሆን፥ በውጭው አደባባይ በኩል የነበሩት ዕቃ ቤቶች ርዝመታቸው አምሳ ክንድ ነበረና። 9ከእነዚህም ዕቃ ቤቶች በታች በስተምሥራቅ በኩል፥ ሰው ከውጭው አደባባይ የሚገባበት መግቢያ ነበረ፤ ይህም በቅጥሩ ራስ አጠገብ ነበረ።
10በደቡብም በኩል በልዩው ስፍራና በግቢው አንጻር ዕቃ ቤቶች ነበሩ። 11በስተፊታቸውም የነበረ መንገድ በሰሜን በኩል እንደ ነበረው እንደ ዕቃ ቤቶቹ መንገድ አምሳል ነበር። ርዝመታቸውም፥ ወርዳቸውም፥ መውጫቸውም፥ ሥርዐታቸውም፥ መዝጊያዎቻቸውም በዚያው ልክ ነበሩ። 12በደቡብም በኩል ከአሉት ዕቃ ቤቶች በታች በምሥራቅ በኩል በቅጥሩ ራስ አጠገብ መግቢያ በር ነበር።
13እንዲህም አለኝ፥ “በልዩ ስፍራ አንጻር በሰሜንና በደቡብ በኩል ያሉ ዕቃ ቤቶች፥ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ የሳዶቅ ልጆች ካህናቱ ከሁሉ ይልቅ የተቀደሰውን ምግብ የሚበሉባቸው ቤቶች ናቸው። ስፍራው ቅዱስ ነውና በዚያ የተቀደሰውን ነገር፥ የእህሉን ቍርባን፥ የኀጢአቱንና የበደሉን መሥዋዕት ያኖራሉ። 14ካህናቱም በገቡ ጊዜ ከመቅደሱ በውጭው አደባባይ አይወጡም፤ የሚያገለግሉበትን ልብሳቸውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖሩታል፤ ሌላም ልብስ ለብሰው ወደ ሕዝብ ይወጣሉ።”
15ውስጠኛውንም ቤት ለክቶ በፈጸመ ጊዜ ወደ ምሥራቅ በሚመለከተው በር መንገድ አወጣኝ፤ እርሱንም ዙሪያውን ለካው። 16ወደ ምሥራቅ በሚመለከተውም በር ኋላ ቆመ፤ የምሥራቁን ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 17ወደ ሰሜንም ዞረ፤ የሰሜኑንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 18ወደ ደቡብም ዞረ፤ የደቡቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 19ወደ ምዕራብም ዞረ፤ የምዕራቡንም ወገን በመለኪያ ዘንግ አምስት መቶ ክንድ አድርጎ ለካ። 20በአራቱም ወገን ለካ፤ የተቀደሰውንና ያልተቀደሰውን ይለይ ዘንድ ርዝመቱ አምስት መቶ ክንድ፥ ወርዱም አምስት መቶ ክንድ የሆነ ቅጥር በዙሪያው ነበረ።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 42: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ