ትንቢተ ሕዝቅኤል 44
44
የተዘጋችው የምሥራቅ በር
1ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወደ አለው ወደ መቅደሱ በር መለሰኝ፤ ተዘግቶም ነበር። 2እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ይህች በር ተዘግታ ትኖራለች እንጂ አትከፈትም፤ ሰውም አይገባባትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶባታልና ተዘግታ ትኖራለች። 3አለቃው ግን እርሱ በእግዚአብሔር ፊት እንጀራ ይበላ ዘንድ ይቀመጥባታል፤ በበሩ ይገባል፤ በዚያም መንገድ ይወጣል።”
4በሰሜኑም በር መንገድ በቤቱ ፊት አገባኝ፤ እኔም አየሁ እነሆም የእግዚአብሔር ክብር የእግዚአብሔርን ቤት መልቶት ነበር፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ። 5እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ልብ አድርግ፤ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዐትና ሕግ ሁሉ የምነግርህን ሁሉ በዐይንህ ተመልከት፤ በጆሮህም ስማ፤ የቤቱንም መግቢያ፥ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ። 6ለዐመፀኛው ለእስራኤል ቤት እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ! ርኵሰታችሁ ሁሉ ይብቃችሁ። 7እንጀራዬን፥ ስብንና ደምን በምታቀርቡበት ጊዜ በመቅደሴ ውስጥ ይሆኑ ዘንድ ቤቴንም ያረክሱ ዘንድ፥ በልባቸውና በሥጋቸው ያልተገረዙትን እንግዶችን ሰዎች አግብታችኋልና፥ በርኵሰታችሁም ሁሉ ቃል ኪዳኔን አፍርሳችኋልና። 8የመቅደሴን ሥርዐት አልጠበቃችሁም፤ ነገር ግን የመቅደሴን ሥርዐት የሚጠብቁ ሌሎችን ለራሳችሁ ሾማችሁ።”
9ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእስራኤል ልጆች መካከል ከአሉት ሁሉ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ የባዕድ ልጅ እንግዳ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ። 10ከእኔ ዘንድ የራቁ፥ እስራኤልም በሳቱ ጊዜ ጣዖታቸውን ተከትለው ከእኔ ዘንድ የሳቱ ሌዋውያን ሳይቀር ኀጢአታቸውን ይሸከማሉ። 11ነገር ግን በመቅደሴ ውስጥ አገልጋዮች ይሆናሉ፤ በቤቱም በሮች በረኞች ይሆናሉ፤ በቤቱም ውስጥ ያገለግላሉ፤ ለሕዝቡም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሌላ መሥዋዕትን ይሠዋሉ፤ ያገለግሉአቸውም ዘንድ በፊታቸው ይቆማሉ። 12በጣዖቶቻቸውም ፊት አገልግለዋቸው ነበሩና፥ ለእስራኤልም ቤት የኀጢአት እንቅፋት ሆነዋልና ስለዚህ እጄን በላያቸው አንሥቻለሁ፤ ኀጢአታቸውንም ይሸከማሉ፥#“ኀጢአታቸውንም ይሸከማሉ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 13እኔንም በክህነት ለማገልገል ወደ እኔ አይቀርቡም፤ ወደ ተቀደሰውም ነገሬና ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ነገር አይቀርቡም፤ እፍረታቸውንና የሠሩትንም ርኵሰታቸውን ይሸከማሉ። 14ነገር ግን ለአገልግሎቱ ሁሉና በእርሱ ውስጥ ለሚደረገው ሁሉ የቤቱን ሥርዐት ጠባቂዎች አደርጋቸዋለሁ።
15“ነገር ግን የእስራኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመቅደሴን ሥርዐት የጠበቁ የሳዶቅ ልጆች ሌዋውያን ካህናት ያገለግሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀርባሉ፤ ስቡንና ደሙንም ወደ እኔ ያቀርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆማሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር። 16ወደ መቅደሴም ይገባሉ፤ ያገለግሉኝም ዘንድ ወደ ገበታዬ ይቀርባሉ፤ ሥርዐቴንም ይጠብቃሉ። 17ወደ ውስጠኛውም አደባባይ በር በገቡ ጊዜ የተልባ እግር ልብስ ይልበሱ፤ በውስጠኛውም አደባባይ በርና በቤቱ ውስጥ በአገለገሉ ጊዜ ከበግ ጠጕር አንዳች ነገር በላያቸው አይሁን። 18በራሳቸው ላይ የተልባ እግር መጠምጠሚያ ይሁን፤ በወገባቸውም ላይ የተልባ እግር ሱሪ ይሁን፤ የሚያልብ ነገር አይታጠቁ። 19ወደ ውጭውም አደባባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገለገሉበትን ልብሳቸውን ያውልቁ፤ በተቀደሰውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑሩት፤ ሕዝቡንም በልብሳቸው እንዳይቀድሱ ሌላውን ልብስ ይልበሱ። 20ራሳቸውንም አይላጩ፥ የራሳቸውንም ጠጕር ይከርከሙ እንጂ ጠጕራቸውን አያሳድጉ። 21ካህናቱም ሁሉ በውስጠኛው አደባባይ ሲገቡ የወይን ጠጅ አይጠጡ። 22መበለቲቱንና የተፈታችይቱን አያግቡ፤ ከእስራኤል ቤት ዘር ግን ድንግሊቱን ወይም የካህን ሚስት የነበረችይቱን መበለት ያግቡ። 23በተቀደሰውና ባልተቀደሰው መካከል ይለዩ ዘንድ ሕዝቤን ያስተምሩ፤ ንጹሕና ንጹሕ ባልሆነው መካከል ይለዩ ዘንድ ያሳዩአቸው። 24ክርክርም በሆነ ጊዜ ለመፍረድ ይቁሙ፤ እንደ ፍርዴ ይፍረዱ፤ በበዓላቴ ሁሉ ሕጌንና ሥርዐቴን ይጠብቁ፤ ሰንበታቴንም ይቀድሱ። 25እንዳይረክሱም ወደ ሞተ ሰው አይግቡ፤ ነገር ግን ለአባት፥ ወይም ለእናት፥ ወይም ለወንድ ልጅ፥ ወይም ለሴት ልጅ፥ ወይም ለወንድም፥ ወይም ላልተዳረች እኅት ይርከሱ። 26ከነጻም በኋላ ሰባት ቀን ይቍጠሩለት። 27በመቅደስም ውስጥ ያገለግል ዘንድ ወደ ውስጠኛው አደባባይ ወደ መቅደሱ በሚገባበት ቀን የኀጢአትን መሥዋዕት ያቅርብ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
28“ርስት አይሆንላቸውም፤ እኔ ርስታቸው ነኝ፤ በእስራኤልም ልጆች ዘንድ ርስት አትስጡአቸው፤ እኔ ርስታቸው ነኝ፤ 29የእህሉን ቍርባንና የኀጢአትን መሥዋዕት የንስሓንም መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤልም ዘንድ እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል። 30የበኵራቱ ሁሉ መጀመሪያ ከየዓይነቱ፥ ከቍርባናችሁም ሁሉ የማንሣት ቍርባን ሁሉ ለካህናት ይሆናል፤ በቤታችሁም ውስጥ በረከት ያድር ዘንድ የአዝመራችሁን ቀዳምያት ለካህናቱ ትሰጣላችሁ። 31ከዎፍም ሆነ ከእንስሳ የበከተውንና አውሬ የሰበረውን ካህናት አይብሉት።
Currently Selected:
ትንቢተ ሕዝቅኤል 44: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ