የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 45

45
የም​ድር ርስት አከ​ፋ​ፈል
1“ርስ​ትም አድ​ር​ጋ​ችሁ ምድ​ርን በዕጣ በም​ታ​ካ​ፍ​ሉ​በት ጊዜ ከም​ድር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን የዕጣ ክፍል መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ። ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ፥ ወር​ዱም ሃያ ሺህ ክንድ ይሆ​ናል፤ በዳ​ር​ቻው ሁሉ ዙሪ​ያው የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል። 2ከእ​ር​ሱም ርዝ​መቱ አም​ስት መቶ፥ ወር​ዱም አም​ስት መቶ ክንድ አራት ማዕ​ዘን የሆነ ቦታ ለመ​ቅ​ደሱ ይሆ​ናል፤ በዙ​ሪ​ያ​ውም ባዶ ስፍራ የሚ​ሆን አምሳ ክንድ ይሆ​ናል። 3ከዚ​ያው ልክ ደግሞ ርዝ​መቱ ሃያ አም​ስት ሺህ ክንድ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ ክንድ የሆነ ስፍራ ትለ​ካ​ለህ፤ በእ​ር​ሱም ውስጥ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳን የሆነ መቅ​ደስ ይሆ​ናል። 4ከም​ድ​ርም የተ​ቀ​ደሰ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያገ​ለ​ግሉ ዘንድ ለሚ​ቀ​ርቡ ለመ​ቅ​ደሱ አገ​ል​ጋ​ዮች ለካ​ህ​ናቱ ይሆ​ናል፤ ለቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ሆን ስፍራ፥ ለመ​ቅ​ደ​ስም የሚ​ሆን የተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይሆ​ናል። 5ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ፥ ወር​ዱም ዐሥር ሺህ የሆነ ስፍራ ለቤቱ አገ​ል​ጋ​ዮች ለሌ​ዋ​ው​ያን መኖ​ሪያ ርስት ከሃያ ዕቃ ቤቶች ጋር#“ሃያ ዕቃ ቤቶች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ይሆ​ናል።
6“ለከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ይዞታ በተ​ቀ​ደ​ሰው የዕጣ ክፍል መባ አጠ​ገብ ወርዱ አም​ስት ሺህ፥ ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ የሆ​ነ​ውን ስፍራ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ። እር​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ይሆ​ናል። 7ለአ​ለ​ቃ​ውም የሆነ የዕጣ ክፍል በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ አጠ​ገብ በዚ​ህና በዚያ ይሆ​ናል፤ በተ​ቀ​ደ​ሰው መባና በከ​ተ​ማ​ዪቱ ይዞታ ፊት በም​ዕ​ራብ በኩል ወደ ምዕ​ራብ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ወደ ምሥ​ራቅ ይሆ​ናል፤ ርዝ​መ​ቱም እንደ አንድ ነገድ ዕጣ ክፍል ሆኖ ከም​ድሩ ከም​ዕ​ራቡ ዳርቻ ጀምሮ እስከ ምሥ​ራቁ ዳርቻ ድረስ ይሆ​ናል። 8ይህም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ይዞታ ይሆ​ን​ለ​ታል፤ የሕ​ዝቤ አለ​ቆ​ችም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ምድ​ሪ​ቱን እንደ ነገ​ዳ​ቸው መጠን ይሰ​ጡ​አ​ቸ​ዋል እንጂ ሕዝ​ቤን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አያ​ስ​ጨ​ን​ቋ​ቸ​ውም።”
9ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አለ​ቆች ሆይ! ይብ​ቃ​ችሁ፤ ግፍ​ንና ዐመ​ፅን አስ​ወ​ግዱ፤ ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅ​ንም አድ​ርጉ፤ ቅሚ​ያ​ች​ሁን ከሕ​ዝቤ ላይ አርቁ፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 10እው​ነ​ተኛ ሚዛን፥ እው​ነ​ተ​ኛም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ እው​ነ​ተ​ኛም የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ ይሁ​ን​ላ​ችሁ። 11እን​ዲ​ሁም የኢ​ፍና የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ አንድ ይሁን፤ የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ፥ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል፥ የኢፍ መስ​ፈ​ሪ​ያ​ውም የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል ይሁን። መስ​ፈ​ሪ​ያው እንደ ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ይሁን። 12ሰቅ​ሉም ሃያ አቦሊ ይሁን፤ ሃያ ሰቅል፥ ሃያ አም​ስት ሰቅል፥ ዐሥራ አም​ስት ሰቅል፥ ምናን ይሁ​ን​ላ​ችሁ።
13“የም​ታ​ቀ​ር​ቡት መባ ይህ ነው፤ ከአ​ንድ ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ስንዴ አንድ ስድ​ስ​ተኛ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ከአ​ን​ድም ቆሮስ መስ​ፈ​ሪያ ገብስ አንድ ስድ​ስ​ተኛ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ። 14የዘ​ይ​ቱም ደንብ፥ ከእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ የባ​ዶ​ስን ዐሥ​ረኛ ክፍል ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ዐሥር የባ​ዶስ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የቆ​ሮስ መስ​ፈ​ሪያ ነውና። 15ከእ​ስ​ራ​ኤል ማሰ​ማ​ርያ ከመ​ን​ጋው ከሁ​ለት መቶው አን​ዱን የበግ ጠቦት ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ፤ ይህ ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ችሁ ዘንድ ለእ​ህል ቍር​ባ​ንና ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት ይሆ​ናል” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 16የሀ​ገ​ሩም ሕዝብ ሁሉ ይህን መባ ለእ​ስ​ራ​ኤል አለቃ ይሰ​ጣሉ። 17በየ​በ​ዓ​ላ​ቱም፥ በየ​መ​ባ​ቻ​ውም፥ በየ​ሰ​ን​በ​ታ​ቱም በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ዓመት በዓል ሁሉ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን መስ​ጠት በአ​ለ​ቃው ላይ ይሆ​ናል፤ እርሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ያስ​ተ​ሰ​ርይ ዘንድ የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል።”
18ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ከመ​ን​ጋው ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ወይ​ፈን ውሰድ፤ መቅ​ደ​ሱ​ንም አንጻ። 19ካህ​ኑም ከኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ደም ወስዶ በመ​ቅ​ደሱ መቃ​ኖ​ችና በመ​ሠ​ዊ​ያው እር​ከን በአ​ራቱ ማዕ​ዘን፥ በው​ስ​ጠ​ኛ​ውም አደ​ባ​ባይ በበሩ መቃ​ኖች ላይ ይር​ጨው። 20ከወ​ሩም በሰ​ባ​ተ​ኛው ቀን እን​ዲሁ አድ​ርግ፤ ይኸ​ውም ስለ ሳተ​ውና ስለ በደ​ለው ሁሉ ነው። እን​ዲሁ ስለ ቤቱ አስ​ተ​ስ​ርዩ።
21“በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አራ​ተ​ኛው ቀን የፋ​ሲ​ካን በዓል ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ። እስከ ሰባት ቀንም ድረስ ቂጣ ትበ​ላ​ላ​ችሁ። 22በዚ​ያም ቀን አለ​ቃው ለራ​ሱና ለሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን ወይ​ፈን ያቅ​ርብ። 23በበ​ዓ​ሉም በሰ​ባቱ ቀኖች የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቅ​ርብ፤ ሰባ​ቱን ቀኖች በየ​ዕ​ለቱ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ወይ​ፈ​ንና ሰባት አውራ በጎች ያቅ​ርብ፤ ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት በየ​ዕ​ለቱ ከፍ​የ​ሎች አንድ አውራ ፍየል ያቅ​ርብ። 24ለአ​ን​ድም ወይ​ፈን አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ን​ድም አውራ በግ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ን​ድም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ለእ​ህል ቍር​ባን ያቅ​ርብ። 25በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ወር ከወ​ሩም በዐ​ሥራ አም​ስ​ተ​ኛው ቀን በበ​ዓሉ ሰባት ቀኖች፥ የኃ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን ከዘ​ይቱ ጋር እን​ዲሁ ያቅ​ርብ።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ