የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሕዝ​ቅ​ኤል 46

46
የእ​ስ​ራ​ኤል መስ​ፍ​ንና የበ​ዓ​ላት አከ​ባ​በር
1ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በው​ስ​ጠ​ኛው አደ​ባ​ባይ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ሥራ በሚ​ሠ​ራ​በት በስ​ድ​ስቱ ቀን ተዘ​ግቶ ይቈይ፤ ነገር ግን በሰ​ን​በት ቀን ይከ​ፈት፤ በመ​ባቻ ቀንም ይከ​ፈት። 2አለ​ቃው በስተ ውጭ ባለው በር በደጀ ሰላሙ መን​ገድ ገብቶ በበሩ መቃን አጠ​ገብ ይቁም፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ር​ሱን የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርቡ፥ እር​ሱም በበሩ መድ​ረክ ላይ ይስ​ገድ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ በሩ ግን እስከ ማታ ድረስ አይ​ዘጋ። 3የሀ​ገ​ርም ሕዝብ በዚያ በር መግ​ቢያ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በሰ​ን​በ​ታ​ትና በመ​ባቻ ይስ​ገዱ። 4አለ​ቃ​ውም በሰ​ን​በት ቀን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸው ስድ​ስት የበግ ጠቦ​ቶች፥ ነው​ርም የሌ​ለ​በት አንድ አውራ በግ ይሁን፤ 5የእ​ህ​ሉም ቍር​ባን ለአ​ውራ በጉ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ይሁን፤ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም የእ​ህል ቍር​ባን እጁ እንደ ቻለ ያህል ይሁን፥ ለአ​ን​ዱም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ያቅ​ርብ። 6በመ​ባ​ቻም ቀን ነውር የሌ​ለ​በ​ትን አንድ ወይ​ፈን፥ ነውር የሌ​ለ​ባ​ቸ​ው​ንም ስድ​ስት ጠቦ​ቶ​ችና አንድ አውራ በግ ያቅ​ርብ፤ 7ለወ​ይ​ፈ​ኑም አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ው​ራ​ውም በግ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እጁ እንደ ቻለው ያህል፥ ለአ​ን​ዱም የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ለእ​ህሉ ቍር​ባን ያቅ​ርብ። 8አለ​ቃ​ውም በሚ​ገ​ባ​በት ጊዜ በበሩ ደጀ ሰላም መን​ገድ ይግባ፤ በዚ​ያ​ውም ይውጣ።
9“የሀ​ገሩ ሕዝብ ግን በየ​ክ​ብረ በዓሉ ቀን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በመጡ ጊዜ በሰ​ሜን በር በኩል ሊሰ​ግድ የሚ​ገ​ባው በደ​ቡብ በር በኩል ይውጣ፤ በደ​ቡ​ብም በር የሚ​ገ​ባው በሰ​ሜን በር በኩል ይውጣ፤ በፊት ለፊት ይውጣ እንጂ በገ​ባ​በት በር አይ​መ​ለስ። 10ሕዝቡ በሚ​ገ​ቡ​በት ጊዜ አለ​ቃው በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይግባ፤ በሚ​ወ​ጡ​በ​ትም ጊዜ ይውጣ። 11በበ​ዓ​ላ​ትና በክ​ብረ በዓል ቀኖች የእ​ህሉ ቍር​ባን ለወ​ይ​ፈኑ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለአ​ውራ በጉ አንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ፥ ለጠ​ቦ​ቶ​ቹም እጁ እን​ደ​ሚ​ች​ለው ያህል፥ ለአ​ንድ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዱቄት አንድ የኢን መስ​ፈ​ሪያ ዘይት ይሆ​ናል። 12አለ​ቃ​ውም በፈ​ቃዱ የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም በፈ​ቃዱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ያ​ቀ​ር​በ​ውን የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት በአ​ቀ​ረበ ጊዜ፥ ወደ ምሥ​ራቅ የሚ​መ​ለ​ከ​ተው በር ይከ​ፈ​ት​ለት፤ በሰ​ን​በ​ትም ቀን እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ርግ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት ያቅ​ርብ፤ ከዚ​ያም በኋላ ይውጣ፤ ከወ​ጣም በኋላ በሩ ይዘጋ።
13“በየ​ዕ​ለ​ቱም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነውር የሌ​ለ​በ​ትን የአ​ንድ ዓመት የበግ ጠቦት ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ በየ​ማ​ለ​ዳው ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ። 14ከእ​ር​ሱም ጋር የእ​ህ​ልን ቍር​ባን፥ በኢን መስ​ፈ​ሪያ ሢሶ ዘይት የተ​ለ​ወሰ የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ስድ​ስ​ተኛ እጅ የስ​ንዴ ዱቄ​ትን፤ በየ​ማ​ለ​ዳው ታቀ​ር​ባ​ለህ፤ ይህ የሚ​ደ​ረግ ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ሥር​ዐት ነው። 15እን​ዲሁ ዘወ​ትር ለሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ጠቦ​ቱ​ንና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን ዘይ​ቱ​ንም በየ​ማ​ለ​ዳው ያቀ​ር​ባሉ።”
16ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “አለ​ቃው ከል​ጆቹ ለአ​ንዱ ከር​ስቱ ስጦታ ቢሰጥ ለል​ጆቹ ይሁን፤ የር​ስት ይዞታ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል። 17ነገር ግን ከአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ ለአ​ንዱ ከር​ስቱ ስጦታ ቢሰጥ እስከ ነፃ​ነት ዓመት ድረስ ለእ​ርሱ ይሁን፥ ከዚ​ያም በኋላ ለአ​ለ​ቃው ይመ​ለስ፤ ርስቱ ግን ለል​ጆቹ ይሁን። 18አለ​ቃ​ውም ሕዝ​ቡን ከይ​ዞ​ታ​ቸው ያወ​ጣ​ቸው ዘንድ ከር​ስ​ታ​ቸው በግድ አይ​ወ​ሰድ፤ ሕዝቤ ሁሉ ከየ​ይ​ዞ​ታ​ቸው እን​ዳ​ይ​ነ​ቀሉ ከገዛ ይዞ​ታው ለል​ጆቹ ርስ​ትን ይስጥ።”
19በበ​ሩም አጠ​ገብ በአ​ለው መግ​ቢያ ወደ ሰሜን ወደ​ሚ​መ​ለ​ከ​ተው ለካ​ህ​ናት ወደ​ሚ​ሆን ወደ ተቀ​ደ​ሰው ዕቃ ቤት አገ​ባኝ፤ እነ​ሆም በኋ​ላው በባ​ሕር በኩል አንድ ስፍራ ነበረ። 20እር​ሱም እን​ዲህ አለኝ፥ “ካህ​ናቱ ሕዝ​ቡን ለመ​ቀ​ደስ ወደ ውጭው አደ​ባ​ባይ እን​ዳ​ይ​ወጡ የበ​ደ​ሉን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​በ​ስ​ሉ​በት፥ የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን የሚ​ጋ​ግ​ሩ​በት ስፍራ ይህ ነው።”
21በው​ጭው አደ​ባ​ባይ አወ​ጣኝ፤ በአ​ደ​ባ​ባ​ይም ወዳ​ለው ወደ አራቱ ማዕ​ዘን አዞ​ረኝ፤ እነ​ሆም፥ በአ​ደ​ባ​ባዩ ማዕ​ዘን ሁሉ አደ​ባ​ባይ ነበረ። 22በአ​ደ​ባ​ባዩ በአ​ራቱ ማዕ​ዘን ርዝ​መቱ አርባ ክንድ፥ ወር​ዱም ሠላሳ ክንድ የሆነ የታ​ጠረ አደ​ባ​ባይ ነበረ፤ በማ​ዕ​ዘኑ ላሉ ለእ​ነ​ዚህ ለአ​ራቱ ስፍ​ራ​ዎች አንድ ልክ ነበ​ራ​ቸው። 23በአ​ራ​ቱም ዙሪያ ሁሉ ግንብ ነበረ፥ በግ​ን​ቡም ሥር በዙ​ሪ​ያው የመ​ቀ​ቀያ ቦታ ነበረ። 24እር​ሱም፥ “እነ​ዚህ የቤቱ አገ​ል​ጋ​ዮች የሕ​ዝ​ቡን መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ያ​በ​ስ​ሉ​ባ​ቸው ስፍ​ራ​ዎች ናቸው” አለኝ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ