የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ገላ​ትያ ሰዎች 1

1
ስለ ጳው​ሎስ ሹመ​ትና ትም​ህ​ርት
1በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስና ከሙ​ታን ለይቶ በአ​ስ​ነ​ሣው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ነው እንጂ ከሰ​ዎች ወይም በሰው ሐዋ​ርያ ካል​ሆነ ከጳ​ው​ሎስ፥ 2አብ​ረ​ውኝ ካሉ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም፥ በገ​ላ​ትያ ላሉ አብ​ያተ ክር​ስ​ቲ​ያን፤ 3ከአ​ባ​ታ​ችን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከጌ​ታ​ችን ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስም ሰላ​ምና ጸጋ ለእ​ና​ንተ ይሁን። 4በክፉ ከሚ​ቃ​ወም ከዚህ ዓለም ያድ​ነን ዘንድ በአ​ባ​ታ​ችን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈቃድ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ራሱን አሳ​ልፎ ሰጠ። 5ለእ​ርሱ ክብር ይሁን፤ ከዘ​ለ​ዓ​ለም እስከ ዘለ​ዓ​ለም አሜን።
6በጸ​ጋዉ የጠ​ራ​ች​ሁን ክር​ስ​ቶ​ስን ከማ​መን ወደ ልዩ ወን​ጌል እን​ዴት ፈጥ​ነው እን​ዳ​ስ​ወ​ጧ​ችሁ አደ​ን​ቃ​ለሁ። 7እርሱ ግን ሌላ አይ​ደ​ለም፤ የሚ​ያ​ው​ኳ​ችሁ ከክ​ር​ስ​ቶ​ስም ወን​ጌል ሊያ​ጣ​ምሙ የሚ​ወዱ አሉ እንጂ። 8እና​ንተ ግን የእ​ኛን ፍለጋ ተከ​ተሉ፤#“እና​ንተ ግን የእ​ኛን ፍለጋ ተከ​ተሉ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። እና​ን​ተስ እኛም ብን​ሆን ወይም መል​አክ ከሰ​ማይ ወርዶ እኛ ካስ​ተ​ማ​ር​ና​ችሁ ወን​ጌል ሌላ ቢሰ​ብ​ክ​ላ​ችሁ ውጉዝ ይሁን። 9አስ​ቀ​ድሜ እንደ አልሁ አሁ​ንም ደግሞ እላ​ለሁ፦ ካስ​ተ​ማ​ር​ና​ችሁ ሌላ ትም​ህ​ርት ያስ​ተ​ማ​ራ​ችሁ ቢኖር ውጉዝ ይሁን።
10አሁ​ንስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለሰው ብዬ አስ​ተ​ም​ራ​ለ​ሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰ​ኛ​ለ​ሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወ​ድስ የክ​ር​ስ​ቶስ ባሪያ አይ​ደ​ለ​ሁም።
ቅዱስ ጳው​ሎስ ለሐ​ዋ​ር​ያ​ነት እንደ ተጠራ
11ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ ወን​ጌል ስለ ሰው እን​ዳ​ይ​ደለ አስ​ታ​ው​ቃ​ች​ኋ​ለሁ። 12ጌታ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ገለ​ጠ​ልኝ እንጂ፥ እኔ ከሰው አል​ተ​ቀ​በ​ል​ሁ​ትም፤ አል​ተ​ማ​ር​ሁ​ት​ምም። 13#የሐዋ. 8፥3፤ 22፥4-5፤ 26፥9-11። በአ​ይ​ሁድ ሥር​ዐት ውስጥ በነ​በ​ርሁ ጊዜ፥ የነ​በ​ረ​ውን የቀ​ድሞ ሥራ​ዬን ሰም​ታ​ች​ኋል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን እጅግ አሳ​ድ​ድና መከራ አጸ​ና​ባ​ቸው ነበር። 14#የሐዋ. 22፥3። ለአ​ባ​ቶች ሥር​ዐት እጅግ ቀና​ተኛ ነበ​ር​ሁና በወ​ገ​ኖች ዘንድ ከጓ​ደ​ኞች ሁሉ በአ​ይ​ሁድ ዘንድ እጅግ ከበ​ርሁ። 15ከእ​ናቴ ማኅ​ፀን ለይቶ ያወ​ጣኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በወ​ደደ ጊዜ በጸ​ጋው ጠራኝ። 16#የሐዋ. 9፥3-6፤ 22፥6-10፤ 26፥13-18። በስ​ሙም ለአ​ሕ​ዛብ ወን​ጌ​ልን አስ​ተ​ምር ዘንድ፥ በእ​ጄም የልጁ ክብር ይታ​ወቅ ዘንድ#“በእ​ጄም የልጁ ክብር ይታ​ወቅ ዘንድ” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። ልጁን ገለ​ጠ​ልኝ፤ ያን​ጊ​ዜም ከሥ​ጋ​ዊና ከደ​ማዊ ሰው ጋር አል​ተ​ማ​ከ​ር​ሁም። 17ከእኔ በፊት ወደ ነበ​ሩት ወደ ሐዋ​ር​ያ​ትም ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም አል​ወ​ጣ​ሁም፤ ነገር ግን ወደ ዐረብ ሀገር ሄድሁ፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ ደማ​ስቆ ተመ​ለ​ስሁ።
መጀ​መ​ሪያ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ስለ መው​ጣቱ
18 # የሐዋ. 9፥26-30። ከሦ​ስት ዓመት በኋላ ግን ኬፋን ላየው ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ወጣሁ፤ በእ​ርሱ ዘን​ድም ዐሥራ አም​ስት ቀን ሰነ​በ​ትሁ። 19ነገር ግን የጌ​ታ​ችን ወን​ድም ያዕ​ቆ​ብን እንጂ ከሐ​ዋ​ር​ያት ሌላ አላ​የ​ሁም። 20ስለ​ም​ጽ​ፍ​ላ​ች​ሁም ነገር እነሆ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሐሰት አል​ና​ገ​ርም። 21ከዚ​ህም በኋላ ወደ ሶር​ያና ወደ ቂል​ቅያ አው​ራጃ መጣሁ። 22በክ​ር​ስ​ቶ​ስም ያሉት የይ​ሁዳ ሀገር ማኅ​በረ ክር​ስ​ቲ​ያን ፊቴን አያ​ው​ቁም ነበር። 23ነገር ግን “ቀድሞ ምእ​መ​ና​ንን ያሳ​ድድ የነ​በ​ረው እርሱ በፊት ያጠ​ፋው የነ​በ​ረ​ውን የሃ​ይ​ማ​ኖት ትም​ህ​ርት ዛሬ ይሰ​ብ​ካል” ሲባል ወሬ​ዬን ይሰሙ ነበር። 24ስለ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ያመ​ሰ​ግ​ኑት ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ