የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ወደ ገላ​ትያ ሰዎች 5

5
በእ​ም​ነት ስለ መጽ​ደቅ
1እን​ግ​ዲህ ጸን​ታ​ችሁ ቁሙ፤ እንደ ገናም በባ​ር​ነት ቀን​በር አት​ኑሩ። 2እነሆ፥ እኔ ጳው​ሎስ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ “ብት​ገ​ዘ​ሩም በክ​ር​ስ​ቶስ ዘንድ ምንም አይ​ጠ​ቅ​ማ​ች​ሁም።” 3ደግ​ሞም ለተ​ገ​ዘረ ሰው ሁሉ የኦ​ሪ​ትን ሕግ መፈ​ጸም እን​ደ​ሚ​ገ​ባው እመ​ሰ​ክ​ራ​ለሁ። 4በኦ​ሪት ልት​ጸ​ድቁ የም​ት​ፈ​ልጉ እና​ንተ ከክ​ር​ስ​ቶስ ተለ​ይ​ታ​ችሁ ከጸ​ጋዉ ወድ​ቃ​ች​ኋል። 5እኛ ግን በመ​ን​ፈስ ቅዱስ፥ በእ​ም​ነ​ትም ልን​ጸ​ድቅ ተስፋ እና​ደ​ር​ጋ​ለን። 6በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ዘንድ በፍ​ቅር የም​ት​ሠራ እም​ነት እንጂ መገ​ዘር አይ​ጠ​ቅ​ም​ምና፤ አለ​መ​ገ​ዘ​ርም ግዳጅ አይ​ፈ​ጽ​ም​ምና። 7ቀድ​ሞስ በመ​ል​ካም ተፋ​ጥ​ና​ችሁ ነበር፤ በእ​ው​ነት እን​ዳ​ታ​ምኑ ማን አሰ​ና​ከ​ላ​ችሁ? 8ይህ መፋ​ጠ​ና​ችሁ ከሚ​ጠ​ራ​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምና።#ግሪኩ “ይህ ማባ​በል ከሚ​ጠ​ራ​ችሁ አይ​ደ​ለ​ምና” ይላል። 9#1ቆሮ. 5፥6። ጥቂት እርሾ ብዙ​ውን ዱቄት መጻጻ ያደ​ር​ገው የለ​ምን? 10እኔ ሌላ እን​ዳ​ታ​ስቡ በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ አም​ኛ​ችሁ ነበር፤ የሚ​ያ​ው​ካ​ችሁ ግን የሆ​ነው ቢሆን ፍዳ​ውን ይሸ​ከ​ማል። 11ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እኔ ግዝ​ረ​ትን ገና የም​ሰ​ብክ ከሆነ፥ እን​ግ​ዲህ ለምን ያሳ​ድ​ዱ​ኛል? እን​ግ​ዲህ የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት እን​ዲ​ያው ቀር​ቶ​አል። 12የሚ​ያ​ው​ኩ​አ​ች​ሁም ሊለዩ ይገ​ባል።
ለነ​ጻ​ነት ስለ መጠ​ራት
13ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ እና​ን​ተስ ለነ​ጻ​ነት ተጠ​ር​ታ​ች​ኋል፤ ነገር ግን በሥ​ጋ​ችሁ ፈቃድ ለነ​ጻ​ነ​ታ​ችሁ ምክ​ን​ያት አታ​ድ​ር​ጉ​ላት፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁም በፍ​ቅር ተገዙ። 14#ዘሌ. 19፥18። “ወን​ድ​ም​ህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚ​ለው አንድ ቃል ሕግን ሁሉ ይፈ​ጽ​ማ​ልና። 15እርስ በር​ሳ​ችሁ የም​ት​በ​ላ​ሉና የም​ት​ነ​ካ​ከሱ ከሆነ ግን፥ እርስ በር​ሳ​ችሁ እን​ዳ​ት​ተ​ላ​ለቁ ተጠ​ን​ቀቁ።#ግእዙ “... ተኃ​ልቆ ተር​ፈ​ክሙ” ይላል።
16እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ በመ​ን​ፈስ ኑሩ እንጂ የሥ​ጋ​ች​ሁን ፈቃድ አታ​ድ​ርጉ። 17#ሮሜ 7፥15-23። ሥጋ መን​ፈስ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ መን​ፈ​ስም ሥጋ የማ​ይ​ሻ​ውን ይሻ​ልና፥ የም​ት​ሹ​ት​ንም እን​ዳ​ታ​ደ​ርጉ እርስ በር​ሳ​ቸው ይጣ​ላሉ። 18የመ​ን​ፈ​ስን ፈቃድ የም​ት​ከ​ተሉ ከሆ​ና​ችሁ፥ ከኦ​ሪት ወጥ​ታ​ች​ኋል። 19የሥ​ጋም ሥራው ይታ​ወ​ቃል፤ እር​ሱም ዝሙት፥ ርኵ​ሰት፥ መዳ​ራት፥ 20ጣዖት ማም​ለክ፥ ሥራይ ማድ​ረግ፥ መጣ​ላት፥ ኵራት፥ የም​ን​ዝር ጌጥ፥ ቅናት፥ ቍጣ፥ ጥር​ጥር፥ ፉክ​ክር፥ ምቀ​ኝ​ነት፥ መጋ​ደል፥ ስካር ይህ​ንም የመ​ሰለ ሁሉ ነው። 21አስ​ቀ​ድሜ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ይህን የሚ​ያ​ደ​ርግ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ግ​ሥት አያ​ይም። 22የመ​ን​ፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕ​ግ​ሥት፥ ምጽ​ዋት፥ ቸር​ነት፥ እም​ነት፥ ገር​ነት፥ ንጽ​ሕና ነው። 23ከዚህ ሕግ የሚ​በ​ልጥ የለም። 24በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ያመኑ ግን ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ከም​ኞ​ትና ከኀ​ጢ​አት ለዩ። 25አሁ​ንም በመ​ን​ፈስ እን​ኑር፤ በመ​ን​ፈ​ስም እን​መ​ላ​ለስ። 26ኩሩ​ዎች አን​ሁን፤ እርስ በር​ሳ​ችን አን​ተ​ማማ፤ እርስ በር​ሳ​ች​ንም አን​ቀ​ናና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ