ኦሪት ዘፍጥረት 18
18
እግዚአብሔር ለአብርሃም እንደ ተገለጠ
1በቀትርም ጊዜ አብርሃም በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ ዛፍ ሥር ተገለጠለት። 2ዐይኑንም በአነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤ 3እንዲህም አለ፥ “አቤቱ በፊትህስ ባለሟልነትን አግኝቼ እንደ ሆነ ባሪያህን አትለፈው፤ 4ውኃ እናምጣላችሁ፤ እግራችሁንም እንጠባችሁ። 5ከዛፉም ሥር ዕረፉ፤ እንጀራም እናምጣላችሁና ብሉ፤ ከዚያም በባሪያችሁ ዘንድ ከአረፋችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰባችሁት ትሄዳላችሁ።” እነርሱም፥ “እንዳልህ እንዲሁ አድርግ” አሉት። 6አብርሃምም ወደ ድንኳን ወደ ሚስቱ ወደ ሣራ ፈጥኖ ገባና፥ “ሦስት መስፈሪያ የተሰለቀ ዱቄት ፈጥነሽ ለውሺ፤ እንጎቻም አድርጊ” አላት። 7አብርሃምም ወደ ላሞቹ ሮጠ፤ እጅግ የሰባም ታናሽ ጥጃ ያዘና ለብላቴናው ሰጠው፤ ያዘጋጅም ዘንድ ተቻኮለ። 8እርጎና መዓር፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. እና ዕብ. “ቅቤና ወተት” ይላል። ያን ያዘጋጀውንም ጥጃ አመጣ፤ በፊታቸውም አቀረበው፤ እርሱም ከዛፉ በታች በፊታቸው ቆሞ ያሳልፍላቸው ነበር፤ እነርሱም በሉ።
ለአብርሃም ወንድ ልጅ እንደሚወለድለት የተሰጠው ተስፋ
9እርሱም፥ “ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት?” አለው። እርሱም፥ “በድንኳኑ ውስጥ ናት” አለው። 10እርሱም፥ “የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ወደ አንተ ተመልሼ እመጣለሁ፤ ሚስትህ ሣራም ልጅን ታገኛለች” አለ። 11ሣራም በድንኳኑ ደጃፍ በስተኋላው ቆማ ሳለች ይህን ሰማች። አብርሃምና ሣራም በዕድሜያቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር፤ በሴቶች የሚሆነውም ልማድ ከሣራ ተቋርጦ ነበር። 12ሣራም ለብቻዋ በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፥ “እስከ ዛሬ ገና ነኝን? ጌታዬም ፈጽሞ ሽምግሎአል።” 13እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “ሣራን ለብቻዋ በልብዋ ምን አሳቃት? እስከ ዛሬ ገና ነኝን? በእውነትስ እወልዳለሁን? ጌታዬም አርጅትዋል#“እስከ ዛሬ ገና ነኝን ጌታዬም አርጅትዋል” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። እነሆ፥ እኔም አርጅቻለሁ ብላለችና። 14በውኑ ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገኛለች።” 15ሣራም ስለ ፈራች “አልሳቅሁም” ብላ ካደች። እርሱም፥ “አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት።
አብርሃም ለሰዶም እንደ ማለደ
16እነዚያም ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ#“ገሞራ” በዕብ. የለም። አቀኑ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ፤ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ።#“አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ” የሚለው በዕብ. እና በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 17እግዚአብሔርም አለ፥ “እኔ የማደርገውን ከወዳጄ አብርሃም አልሰውርም፤ 18አብርሃም በእውነት ታላቅና ብርቱ ሕዝብ ይሆናልና፤ የምድር ሕዝቦችም ሁሉ በእርሱ ይባረካሉና። 19ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ፥ ልጆቹንና ቤቱን ያዝዛቸው ዘንድ እንዳለው አውቃለሁና፤ ይህም እግዚአብሔር ለአብርሃም የተናገረውን ሁሉ ያደርግላቸው ዘንድ ነው።” 20እግዚአብሔርም ለአብርሃም አለው፥ “የሰዶምና የገሞራ ጩኸት በእኔ ዘንድ በዛ፤ ኀጢአታቸውም እጅግ ከበደች፤ 21እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸቷ ይፈጽሙአት እንደ ሆነ አይ ዘንድ እወርዳለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ።”
22ሰዎቹም ከዚያ በተመለሱ ጊዜ ወደ ሰዶም መጡ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር። 23አብርሃምም ቀረበ፤ አለም፥ “አቤቱ፥ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ጻድቁ እንደ ኃጥኡ አይሁን። 24አምሳ ጻድቃን በከተማዪቱ ውስጥ ቢገኙ በውኑ ሁሉን ታጠፋለህን? ከተማዪቱንስ በእርስዋ ስለሚገኙ አምሳ ጻድቃን አትምርምን? 25አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።” 26እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፥ “በሰዶም ከተማ ውስጥ አምሳ ጻድቃን ባገኝ ከተማውን ሁሉ ስለ እነርሱ አድናለሁ።” 27አብርሃምም መለሰ፤ አለም፥ “እኔ አፈርና አመድ ስሆን ከጌታዬ ከእግዚአብሔር ጋር እናገር ዘንድ አሁን ጀመርሁ፤ 28ከእነዚያ አምሳ ጻድቃን አምስት ቢጐድሉ ከተማዪቱን ሁሉ በጐደሉት በአምስቱ ምክንያት ታጠፋለህን?” እግዚአብሔርም፥ “ከዚያ አርባ አምስት ባገኝ ስለ እነርሱ አላጠፋትም” አለው። 29አብርሃምም አለው፥ “ከዚያ አርባ ቢገኙሳ?” እግዚአብሔርም፥ “ለአርባው ስል አላጠፋትም” አለው። 30አብርሃምም እንደገና ነገሩን ደገመ፤ እንዲህም አለው፥ “ከዚያ ሠላሳ ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ሠላሳው አላጠፋትም” አለው። 31ደግሞም፥ “እነሆ፥ ከጌታዬ ከእግዚአብሔር ጋር እነጋገር ዘንድ ባለሟልነትን ካገኘሁ ከዚያ ሃያ ቢገኙሳ?” አለው። እርሱም፥ “ስለ ሃያው አላጠፋትም” አለው። 32አብርሃምም አለው፥ “አቤቱ እንደገና እናገር ዘንድ ፍቀድልኝ፤ ከዚያ ዐሥር ቢገኙሳ?” እርሱም፥ “ስለ ዐሥሩ አላጠፋትም” አለው።#ምዕ. 18 ቍ. 30 እና 32 ላይ በግሪክ ሰባ. ሊ. “ጌታዬ ሆይ እንደ ገና አንድ ጊዜ ብናገር በእኔ ላይ አንዳች ነገር ይሆናልን?” ይላል። 33እግዚአብሔርም ከአብርሃም ጋር ንግግሩን በጨረሰ ጊዜ ሄደ፤ አብርሃምም ወደ ስፍራው ተመለሰ።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 18: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ