የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 21

21
የይ​ስ​ሐቅ ልደት
1እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው ሣራን ጐበ​ኛት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገ​ረው ለሣራ አደ​ረ​ገ​ላት። 2ሣራም ፀነ​ሰች፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በተ​ና​ገ​ረው ወራት ለአ​ብ​ር​ሃም በእ​ር​ጅ​ናዋ ወንድ ልጅን ወለ​ደ​ች​ለት። 3አብ​ር​ሃ​ምም ሣራ የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን የል​ጁን ስም ይስ​ሐቅ ብሎ ጠራው። 4አብ​ር​ሃ​ምም ልጁን ይስ​ሐ​ቅን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን ገረ​ዘው። 5አብ​ር​ሃ​ምም ልጁ ይስ​ሕቅ በተ​ወ​ለ​ደ​ለት ጊዜ መቶ ዓመቱ ነበረ። 6ሣራም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ደስ አሰ​ኘኝ፤ ይህን የሚ​ሰማ ሁሉ በእኔ ምክ​ን​ያት ደስ ይሰ​ኛ​ልና” አለች። 7ደግ​ሞም ሣራ “በእ​ር​ጅ​ናዋ የወ​ለ​ደ​ች​ውን ሕፃን እን​ድ​ታ​ጠባ ለአ​ብ​ር​ሃም ማን በነ​ገ​ረው?” አለች። 8ሕፃ​ኑም አደገ፤ ጡት​ንም አስ​ጣ​ሉት፤ አብ​ር​ሃ​ምም ይስ​ሐ​ቅን ጡት ባስ​ጣ​ለ​በት ቀን ትልቅ ግብ​ዣን አደ​ረገ።
የአ​ጋ​ርና የይ​ስ​ማ​ኤል መባ​ረር
9ሣራም ግብ​ፃ​ዊቱ አጋር ለአ​ብ​ር​ሃም የወ​ለ​ደ​ች​ለ​ትን ልጅ ይስ​ማ​ኤ​ልን ከል​ጅዋ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር ሲጫ​ወት አየ​ችው። 10ሣራም አብ​ር​ሃ​ምን አለ​ችው፥ “ይህ​ችን ባሪያ ከነ​ል​ጅዋ አባ​ር​ራት፤ የዚ​ህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይ​ስ​ሐቅ ጋር አይ​ወ​ር​ስ​ምና።” 11ይህም ነገር በአ​ብ​ር​ሃም ዘንድ ስለ ልጁ እጅግ ችግር ሆነ​በት። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አብ​ር​ሃ​ምን አለው፥ “ስለ​ዚች አገ​ል​ጋ​ይ​ህና ስለ ሕፃኑ አት​ዘን፤ ሣራም የም​ት​ነ​ግ​ር​ህን ቃል ሁሉ ስማ፤ በይ​ስ​ሐቅ ዘር ይጠ​ራ​ል​ሃ​ልና። 13የባ​ሪ​ያ​ዪ​ቱን ልጅ ደግሞ ታላቅ ሕዝብ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ፤ ዘርህ ነውና።” 14አብ​ር​ሃ​ምም ማልዶ ተነሣ፤ እን​ጀ​ራ​ንም ወሰደ፤ የውኃ አቍ​ማ​ዳ​ንም ለአ​ጋር በት​ከ​ሻዋ አሸ​ከ​ማት፤ ሕፃ​ኑ​ንም ሰጥቶ አስ​ወ​ጣት፤ እር​ስ​ዋም ሄደች፤ በዐ​ዘ​ቅተ መሐ​ላም በኩል ባለው ምድረ በዳ ተቅ​በ​ዘ​በ​ዘች። 15ውኃ​ውም ከአ​ቍ​ማ​ዳው አለቀ፤ ሕፃ​ኑ​ንም ከአ​ንድ ቍጥ​ቋጦ ሥር ጥላው ሄደች፤ 16ልጄ ሲሞት አላ​የ​ውም ብላ ቀስት ተወ​ር​ውሮ የሚ​ደ​ር​ስ​በ​ትን ያህል ርቃ በአ​ን​ጻሩ እየ​ተ​መ​ለ​ከ​ተች፥ ፊት ለፊት ተቀ​መ​ጠች፤ ቃል​ዋ​ንም አሰ​ምታ አለ​ቀ​ሰች።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ሕፃኑ ቃሉን አሰ​ምቶ አለ​ቀሰ” ይላል። 17እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕ​ፃ​ኑን ጩኸት ሰማ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ከሰ​ማይ አጋ​ርን እን​ዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የል​ጅ​ሽን ድምፅ ባለ​በት ስፍራ ሰም​ቶ​አ​ልና አት​ፍሪ። 18ተነሺ፤ ልጅ​ሽ​ንም አንሺ፤ በእ​ጅ​ሽም አጽ​ኚው፤ ትልቅ ሕዝብ አደ​ር​ገ​ዋ​ለ​ሁና።” 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ጋር ዐይ​ን​ዋን ከፈ​ተ​ላት፤ የውኃ ጕድ​ጓ​ድ​ንም አየች፤ ሄዳም አቍ​ማ​ዳ​ውን በውኃ ሞላች፤ ልጅ​ዋ​ንም አጠ​ጣ​ችው። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከዚያ ሕፃን ጋር ነበረ፤ አደ​ገም፤ በም​ድረ በዳም ተቀ​መጠ፤ ቀስ​ተ​ኛም ሆነ። 21በፋ​ራን ምድረ በዳም ተቀ​መጠ፤ እና​ቱም ከም​ድረ ግብፅ ሚስት ወሰ​ደ​ች​ለት።
በአ​ብ​ር​ሃ​ምና በአ​ቤ​ሜ​ሌክ መካ​ከል የተ​ደ​ረገ ስም​ም​ነት
22በዚያ ዘመን አቤ​ሜ​ሌክ፥ ሚዜው አኮ​ዘ​ትና የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮል ወደ አብ​ር​ሃም ሄደው አሉት፥ “በም​ታ​ደ​ር​ገው ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ጋር ነው፤ 23አሁ​ንም በእ​ኔም፥ በል​ጄም፥ በወ​ገ​ኔም፥ ከእ​ኔም ጋር ባለ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ር​ግ​ብኝ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማል​ልኝ፤ ነገር ግን በእ​ን​ግ​ድ​ነት መጥ​ተህ ለአ​ንተ ቸር​ነት እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ አን​ተም ለእኔ፥ ለተ​ቀ​ም​ጥ​ህ​ባ​ትም ምድር ቸር​ነ​ትን ታደ​ር​ጋ​ለህ።” 24አብ​ር​ሃ​ምም፥ “እሺ እኔ እም​ላ​ለሁ” አለ። 25አብ​ር​ሃ​ምም አቤ​ሜ​ሌ​ክን ብላ​ቴ​ኖቹ በቀ​ሙት በውኃ ጕድ​ጓድ ምክ​ን​ያት ወቀ​ሰው። 26አቤ​ሜ​ሌ​ክም አለ፥ “ይህን ነገር ማን እን​ዳ​ደ​ረ​ገው አላ​ወ​ቅ​ሁም፤ አን​ተም ደግሞ ምንም አል​ነ​ገ​ር​ኸ​ኝም፤ እኔም ከዛሬ በቀር አል​ሰ​ማ​ሁም።” 27አብ​ር​ሃ​ምም በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን አም​ጥቶ ለአ​ቤ​ሜ​ሌክ ሰጠው፤ ሁለ​ቱም ቃል ኪዳን አደ​ረጉ። 28አብ​ር​ሃ​ምም ሰባ#ዕብ. “ሰባት” ይላል። ቄቦች በጎ​ችን ለብ​ቻ​ቸው አቆመ። 29አቤ​ሜ​ሌ​ክም አብ​ር​ሃ​ምን፥ “ለብ​ቻ​ቸው ያቆ​ም​ሃ​ቸው እነ​ዚያ ሰባ#ዕብ. “ሰባት” ይላል። ቄቦች በጎች ምን​ድን ናቸው?” አለው። 30እር​ሱም፥ “እኔ ይህ​ችን የውኃ ጕድ​ጓድ እን​ደ​ቈ​ፈ​ርሁ ምስ​ክር ይሆ​ኑ​ልኝ ዘንድ እነ​ዚ​ህን ሰባ ቄቦች በጎች ከእጄ ትወ​ስ​ዳ​ለህ” አለው። 31ስለ​ዚ​ህም ያን ጕድ​ጓድ ዐዘ​ቅተ መሐላ ብሎ ጠራው፤ በዚያ እርስ በር​ሳ​ቸው ተማ​ም​ለ​ዋ​ልና። 32በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ አጠ​ገ​ብም ቃል ኪዳ​ንን አደ​ረጉ። አቤ​ሜ​ሌ​ክና ሚዜው አኮ​ዞት፥ የሠ​ራ​ዊቱ አለቃ ፋኮ​ልም ተነ​ሥ​ተው ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ተመ​ለሱ። 33አብ​ር​ሃ​ምም በዐ​ዘ​ቅተ መሐላ አጠ​ገብ የተ​ምር ዛፍን ተከለ፤ በዚ​ያም የዘ​ለ​ዓ​ለ​ሙን አም​ላክ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም ጠራ። 34አብ​ር​ሃ​ምም በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ምድር ብዙ ቀን እን​ግዳ ሆኖ ተቀ​መጠ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ