ኦሪት ዘፍጥረት 29
29
ያዕቆብ ወደ ላባ ቤት መድረሱ
1ያዕቆብም በማለዳ ተነሥቶ የያዕቆብና የዔሳው እናት የርብቃ ወንድም የሶርያ ሰው የባቱኤል ልጅ ወደሚሆን ወደ ላባ ሄደ። 2በተመለከተም ጊዜ በሜዳው እነሆ ጕድጓድን አየ፤ በዚያም ሦስት የበጎች መንጎች በላዩ ተመስገው ነበር፤ ከዚያች ጕድጓድ በጎቹን ያጠጡ ነበርና፤ በጕድጓድዋም አፍ ታላቅ ድንጋይ ነበረች። 3መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተሰበሰቡ ጊዜ እረኞች ድንጋይዋን ከጕድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፤ ድንጋይዋንም ወደ ስፍራው መልሰው በጕድጓዱ አፍ እንደገና ይገጥሙት ነበር። 4ያዕቆብም፥ “ወንድሞች ሆይ፥ እናንት ከወዴት ናችሁ?” አላቸው። 5እነርሱም፥ “እኛ ከካራን ነን” አሉት። “የናኮርን ልጅ ላባን ታውቁታላችሁን?” አላቸው። እነርሱም፥ “እናውቀዋለን” አሉት። 6“እርሱ ደኅና ነውን?” አላቸው። እነርሱም፥ “አዎ ደኅና ነው፤ አሁንም ልጁ ራሔል የአባቷን በጎች ይዛ ትመጣለች” አሉት። 7እርሱም፥ “ቀኑ ገና ቀትር ነው፥ ከብቶቹ የሚሰበሰቡበት ሰዓቱም ገና አልደረሰም፤ አሁንም በጎቹን አጠጡና ሄዳችሁ አሰማሩአቸው” አላቸው። 8እነርሱም አሉ፥ “እረኞች ሁሉ ካልተሰበሰቡና ድንጋዪቱን ከጕድጓዱ አፍ ካላነሡአት በቀር አንችልም፤ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።” 9እርሱም ገና ከእነርሱ ጋር ሲነጋገር እነሆ፥ የላባ ልጅ ራሔል የአባትዋን በጎች ይዛ ደረሰች፤ እርስዋ የአባቷን በጎች ትጠብቅ ነበርና። 10ያዕቆብም የእናቱን ወንድም የላባን ልጅ ራሔልንና የአጎቱን የላባን በጎች በአየ ጊዜ ቀረበ፤ ከጕድጓዱም አፍ ድንጋዩን አነሣ፤ የአጎቱን የላባን በጎችም አጠጣ። 11ያዕቆብም ራሔልን ሳማት፤ ቃሉንም ከፍ አድርጎ አለቀሰ። 12ያዕቆብም የአባቷ ዘመድና የርብቃ ልጅ መሆኑን ለራሔል አስታወቃት፤ እርስዋም ሮጣ ሄዳ ለአባቷ ይህን ነገር ነገረችው።
13ላባም የእኅቱን የርብቃን ልጅ የያዕቆብን ስም#ዕብ. “ዜና” ይላል። በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ሮጠ፥ አቅፎም ሳመው፥ ወደ ቤቱም አገባው። ነገሩንም ሁሉ ለላባ ነገረው። 14ላባም ያዕቆብን፥ “በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።
ያዕቆብ ስለ ራሔልና ልያ ላባን ማገልገሉ
15ላባም ያዕቆብን፥ “ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ አታገለግለኝም ደመወዝህ ምንድን ነው? ንገረኝ” አለው 16ለላባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ የታላቂቱ ስም ልያ የታናሺቱም ስም ራሔል ነበረ። 17ልያም ዓይነ ልም ነበረች፤ ራሔል ግን መልከ መልካም ነበረች፥ ፊቷም ውብ ነበረ። 18ያዕቆብም ራሔልን ወደዳት፤ ያዕቆብም ላባን እንዲህ አለው፥ “ስለ ታናሺቱ ልጅህ ስለ ራሔል ሰባት ዓመት እገዛልሃለሁ። ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እርስዋን ስጠኝ”#“ሚስት ትሆነኝ ዘንድ እርስዋን ስጠኝ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። አለው። 19ላባም፥ “ለሌላ ሰው ከምሰጣት ይልቅ ለማውቅህ ለዘመዴ ለአንተ ብሰጣት ይሻላል፤ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። 20ያዕቆብም ስለ ራሔል ሰባት ዓመት ተገዛ፤ እርስዋንም ይወድዳት ስለነበረ በእርሱ ዘንድ ጥቂት ቀን ሆነለት።
21ያዕቆብም ላባን፥ “እንግዲህ ወደ እርስዋ እገባ ዘንድ ሚስቴን ስጠኝ፥ ቀኔ ተፈጽሞአልና አለው።” 22ላባም የዚያን ስፍራ ሰዎች ሁሉ ሰበሰበ፥ ሰርግም አደረገ። 23በመሸም ጊዜ ልጁን ልያን ወስዶ ወደ ያዕቆብ አስገባት፤ ያዕቆብም ወደ እርስዋ ገባ። 24ላባም ለልጁ ልያ አገልጋዪቱን ዘለፋን አገልጋይ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። 25በነጋም ጊዜ እነሆ ልያ ነበረች፤ ያዕቆብም ላባን፥ “ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለገልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ?” አለው። 26ላባም እንዲህ አለ፥ “በሀገራችን ታላቂቱ ሳለች፥ ታናሺቱን እንሰጥ ዘንድ ወግ አይደለም፤ 27ለዚችም ሰባት ዓመት ፈጽም፤ ሌላ ሰባት ዓመት ደግሞ እኔን ስለምታገለግለኝ አገልግሎት እርስዋን ደግሞ እሰጥሃለሁ።” 28ያዕቆብም እንዲህ አደረገ፤ ለዚችም ሰባት ዓመት ፈጸመ፤ ልጁን ራሔልንም ለእርሱ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው። 29ላባም ለልጁ ለራሔል አገልጋዪቱን ባላን አገልጋይ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። 30ያዕቆብም ወደ ራሔል ደግሞ ገባ። ራሔልንም ከልያ ይልቅ ወደዳት፤ ሌላ ሰባት ዓመትም ተገዛለት።
ለያዕቆብ የተወለዱ ልጆች
31እግዚአብሔርም ልያ የተጠላች መሆንዋን በአየ ጊዜ ማኅፀንዋን ከፈተላት፤ ራሔል ግን መካን ነበረች። 32ልያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ “እግዚአብሔር መዋረዴን አይቶአልና፥ እንግዲህስ ወዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል። 33ልያም ዳግመኛ ፀነሰች፤ ሁለተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችለት፤ “እኔ እንደ ተጠላሁ እግዚአብሔር ስለ ሰማ ይህን ጨመረልኝ” አለች፤ ስሙንም ስምዖን ብላ ጠራችው ። 34ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ “ከእንግዲህ ወዲህስ ባሌ ወደ እኔ ይጠጋል፤ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወልጄለታለሁና” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ሌዊ ብላ ጠራችው። 35ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ በዚህም ጊዜ “እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 29: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ