የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 31

31
ያዕ​ቆብ ከላባ መሸሹ
1ያዕ​ቆ​ብም የላባ ልጆች ያሉ​ትን ነገር፥ “ያዕ​ቆብ ለአ​ባ​ታ​ችን የሆ​ነ​ውን ሁሉ ወሰደ፤ ይህ​ንም ሁሉ ክብር ከአ​ባ​ታ​ችን ከብት አገኘ” ሲሉ ሰማ። 2ያዕ​ቆ​ብም የላ​ባን ፊት አየ፤ እነ​ሆም፥ ከእ​ርሱ ጋር እንደ ዱሮው አል​ሆ​ነም። 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ያዕ​ቆ​ብን፥ “ወደ አባ​ት​ህና ወደ ዘመ​ዶ​ችህ ሀገር ተመ​ለስ፤ እኔም ከአ​ንተ ጋር እሆ​ና​ለሁ” አለው። 4ያዕ​ቆ​ብም ልኮ ራሔ​ል​ንና ልያን ወደ በጎቹ መሰ​ማ​ሪያ ወደ ሜዳ ጠራ​ቸው፤ 5እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “እነሆ፥ የአ​ባ​ታ​ችሁ ፊት እንደ ዱሮ ከእኔ ጋር እን​ዳ​ል​ሆነ አያ​ለሁ፤ ነገር ግን የአ​ባቴ አም​ላክ ከእኔ ጋር ነው። 6እኔ ባለኝ ጕል​በቴ ሁሉ አባ​ታ​ች​ሁን እን​ዳ​ገ​ለ​ገ​ልሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ። 7አባ​ታ​ችሁ ግን አሳ​ዘ​ነኝ፥ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ደመ​ወ​ዜን በዐ​ሥር በጎች ዋጋ ለወ​ጠ​ብኝ” ይላል። ለወጠ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ክፉን ያደ​ር​ግ​ብኝ ዘንድ አል​ፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም። 8ደመ​ወ​ዝህ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮቹ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችን ወለዱ፤ ነጫ​ጮቹ ደመ​ወ​ዝህ ይሁኑ ቢለኝ በጎቹ ሁሉ ነጫ​ጮ​ችን ወለዱ። 9እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የአ​ባ​ታ​ች​ሁን በጎች ሁሉ ነሥቶ ለእኔ ሰጠኝ። 10እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በጎቹ በሚ​ፀ​ንሱ ጊዜ ዐይ​ኔን አን​ሥቼ በሕ​ልም አየሁ፤ እነ​ሆም፥ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮ​ችና ሐመደ ክቦ ነበሩ። 11እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም#ዕብ. “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ” ይላል። በሕ​ልም፦ ‘ያዕ​ቆብ ያዕ​ቆብ’ አለኝ፤ እኔም፦ ‘እነ​ሆኝ ምን​ድን ነው?’ አል​ሁት። 12እን​ዲ​ህም አለኝ፦ ዐይ​ን​ህን አቅ​ን​ተህ እይ፤ በበ​ጎ​ችና በፍ​የ​ሎች ላይ የሚ​ን​ጠ​ላ​ጠ​ሉት የበ​ጎ​ችና የፍ​የ​ሎች አው​ራ​ዎች ነጭ፥ ሐመደ ክቦና ዝን​ጕ​ር​ጕ​ሮች ናቸው፤ ላባ በአ​ንተ ላይ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን አይ​ቻ​ለ​ሁና። 13ሐው​ል​ቱን ዘይት በቀ​ባ​ህ​ባት፥ በዚ​ያች ለእኔ ስእ​ለት በተ​ሳ​ል​ህ​ባት ሀገር የተ​ገ​ለ​ጥ​ሁ​ልህ ፈጣ​ሪህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ። አሁ​ንም ተነ​ሥ​ተህ ከዚህ ሀገር ውጣ፤ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​ባ​ትም ምድር ተመ​ለስ፤ እኔም ከአ​ንተ ጋር እኖ​ራ​ለሁ።” 14ራሔ​ልና ልያም መል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “በአ​ባ​ታ​ችን ቤት ለእኛ ድርሻ ወይም ርስት በውኑ አለን? 15እኛ በእ​ርሱ ዘንድ እንደ ባዕድ የተ​ቈ​ጠ​ርን አይ​ደ​ለ​ምን? እርሱ እኛን ሽጦ ዋጋ​ች​ንን በል​ቶ​አ​ልና። 16ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ባ​ታ​ችን የነ​ሣው ይህ ሁሉ ሀብ​ትና ክብር ለእ​ኛና ለል​ጆ​ቻ​ችን ነው፤ አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ህን ሁሉ አድ​ርግ።”
17ያዕ​ቆ​ብም ተነሣ፤ ልጆ​ቹ​ንና ሚስ​ቶ​ቹ​ንም በግ​መ​ሎች ላይ አስ​ቀ​መጠ። 18መን​ጎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ የቤ​ቱ​ንም ዕቃ ሁሉ፥ በሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል ሳለ ያገ​ኛ​ቸ​ውን ከብ​ቶች ሁሉ ይዞ ወደ አባቱ ወደ ይስ​ሐቅ ወደ ከነ​ዓን ምድር ሄደ። 19ላባ ግን በጎ​ቹን ለመ​ሸ​ለት ሄዶ ነበር፤ ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ሰረ​ቀች። 20ያዕ​ቆ​ብም ነገ​ሩን ከሶ​ር​ያ​ዊው ከላባ ሰወረ፤ እን​ደ​ሚ​ሄ​ድም አል​ነ​ገ​ረ​ውም። 21እር​ሱም ያለ​ውን ሁሉ ይዞ ኰበ​ለለ፤ ተነ​ሥ​ቶም ወን​ዙን ተሻ​ገረ፤ በገ​ለ​ዓድ ተራ​ራም አደረ።
ላባ ያዕ​ቆ​ብን መከ​ታ​ተሉ
22ለሶ​ር​ያ​ዊው ላባም ያዕ​ቆብ እንደ ኰበ​ለለ ነገ​ሩት። 23ላባም ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ ይዞ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ተከ​ተ​ላ​ቸው፤ በገ​ለ​ዓድ ተራ​ራም ላይ አገ​ኛ​ቸው።#ምዕ. 31 ቍ. 22 በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ ሊ. “በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን የያ​ዕ​ቆብ መኰ​ብ​ለል ለላባ ተነ​ገ​ረው” ሲል ቍ. 23 “ከወ​ን​ድ​ሞ​ቹም ጋር ሆኖ የሰ​ባት ቀን ያህል መን​ገድ ተከ​ተ​ለው” ይላል። 24እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ ሶር​ያ​ዊው ወደ ላባ በሌ​ሊት በሕ​ልም መጥቶ፥ “በባ​ሪ​ያዬ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ክፉ ነገር እን​ዳ​ት​ና​ገር ተጠ​ን​ቀቅ” አለው። 25ላባም ያዕ​ቆ​ብን አገ​ኘው፤ ያዕ​ቆ​ብም ድን​ኳ​ኑን በተ​ራ​ራው ላይ ተክሎ ነበር፤ ላባም ወን​ድ​ሞ​ቹን በገ​ለ​ዓድ ተራራ አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው። 26ላባም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “ለምን እን​ዲህ አደ​ረ​ግህ? ከእኔ በስ​ውር የኰ​በ​ለ​ልህ? ልጆ​ች​ንስ ሰር​ቀህ በሰ​ይፍ እን​ደ​ማ​ረከ የወ​ሰ​ድ​ኻ​ቸው? 27ብት​ነ​ግ​ረኝ ኑሮ በደ​ስ​ታና በሐ​ሴት፥ በዘ​ፈን፥ በከ​በ​ሮና በበ​ገና በሸ​ኘ​ሁህ ነበር። 28ወይስ ወን​ዶ​ቹ​ንና ሴቶ​ቹን ልጆ​ችን እስም ዘንድ አይ​ገ​ባ​ኝ​ምን? አሁ​ንም ይህን እንደ አላ​ዋቂ አደ​ረ​ግህ። 29አሁ​ንም በአ​ንተ ላይ ክፉ ማድ​ረግ በቻ​ልሁ ነበር፤ ነገር ግን የአ​ባ​ትህ አም​ላክ ትና​ንት፦ በያ​ዕ​ቆብ ላይ ክፉ እን​ዳ​ታ​ደ​ርግ ተጠ​ን​ቀቅ ብሎ ነገ​ረኝ። 30አሁ​ንም የአ​ባ​ት​ህን ቤት ከና​ፈ​ቅህ ሂድ፤ ነገር ግን አም​ላ​ኮ​ቼን ለምን ሰረ​ቅህ?” 31ያዕ​ቆ​ብም መለሰ፤ ላባ​ንም እን​ዲህ አለው፥ “ልጆ​ች​ህ​ንና ገን​ዘ​ቤን ሁሉ ከእኔ የም​ት​ቀ​ማኝ ስለ​መ​ሰ​ለ​ኝና ስለ​ፈ​ራሁ ይህን አደ​ረ​ግሁ።” 32ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “አም​ላ​ኮ​ች​ህን የም​ታ​ገ​ኝ​በት ሰው ግን እርሱ ይሙት፤ ገን​ዘ​ብ​ህም በእኔ ዘንድ ካለ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ፊት እይ፤ ለአ​ን​ተም ውሰ​ደው” አለ። ያዕ​ቆብ ሚስቱ ራሔል እንደ ሰረ​ቀ​ቻ​ቸው አያ​ው​ቅም ነበ​ርና።
33ላባም ወደ ያዕ​ቆብ ድን​ኳ​ንና ወደ ልያም ድን​ኳን ገባና በረ​በረ፤ አላ​ገ​ኘ​ምም፤ ከዚ​ያም ወጣና ወደ ሁለቱ ዕቁ​ባ​ቶቹ ድን​ኳን ገባ፤ ነገር ግን አላ​ገ​ኘም። ወደ ራሔ​ልም ድን​ኳን ገባ። 34ራሔ​ልም የአ​ባ​ቷን ጣዖ​ቶች ወስዳ ከግ​መል ኮርቻ በታች ሸሸ​ገች፤ በላ​ዩም ተቀ​መ​ጠ​ች​በት። ላባም ድን​ኳ​ኑን ሁሉ ፈለገ፤ አን​ዳ​ችም አላ​ገ​ኘም። 35እር​ስ​ዋም አባ​ቷን፥ “ጌታዬ በፊ​ትህ ለመ​ቆም ስላ​ል​ቻ​ልሁ የአ​ቀ​ለ​ል​ሁህ አይ​ም​ሰ​ልህ፤ በሴ​ቶች የሚ​ደ​ርስ ግዳጅ ደር​ሶ​ብ​ኛ​ልና” አለ​ችው። ላባም የራ​ሔ​ልን ድን​ኳን በረ​በረ፤ ነገር ግን ጣዖ​ቶ​ቹን አላ​ገ​ኘም።
36ያዕ​ቆ​ብም ተቈጣ፤ ላባ​ንም ወቀ​ሰው፤ ያዕ​ቆ​ብም መለሰ፤ ላባ​ንም እን​ዲህ አለው፥ “የበ​ደ​ል​ሁህ በደል ምን​ድን ነው? ኀጢ​አ​ቴስ ምን​ድን ነው? ይህን ያህል ያሳ​ደ​ድ​ኸኝ? 37አሁ​ንም ዕቃ​ዬን ሁሉ በረ​በ​ርህ፤ ከቤ​ት​ህስ ዕቃ ሁሉ ምን አገ​ኘህ? እነ​ርሱ በእኛ በሁ​ለ​ታ​ችን መካ​ከል ይፈ​ርዱ ዘንድ በወ​ን​ድ​ሞ​ችና በወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ፊት አቅ​ር​በው። 38ሃያ አንድ ዓመት በጎ​ች​ህ​ንና ፍየ​ሎ​ች​ህን ስጠ​ብቅ ኖርሁ፥#ግሪክ ሰባ. ሊ. ዕብ. “ሃያ ዓመት ሙሉ ከአ​ንተ ጋር ነበ​ርሁ እን​ስት በጎ​ች​ህና ፍየ​ሎ​ች​ህም አል​ጨ​ነ​ገ​ፉም” ይላል። ከበ​ጎ​ች​ህም ጠቦ​ቶ​ችን አል​በ​ላ​ሁም፤ 39አውሬ የሰ​በ​ረ​ው​ንም አላ​መ​ጣ​ሁ​ል​ህም ነበር፤ በቀ​ንም ሆነ በሌ​ሊት የተ​ሰ​ረቀ ቢኖር ከእኔ እከ​ፍ​ልህ ነበር። 40የቀን ሐሩር፥ የሌ​ሊት ቍር ይበ​ላኝ ነበር፤ ዕን​ቅ​ል​ፍም ከዐ​ይኔ ጠፋ። 41ለአ​ንተ ቤት የተ​ገ​ዛ​ሁ​ልህ ዛሬ ሃያ አንድ ዓመት ነው፤ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆ​ችህ፥ ሰባት#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ስድ​ስት” ይላል። ዓመት ስለ በጎ​ችህ ተገ​ዛ​ሁ​ልህ፤ ደመ​ወ​ዜ​ንም ዐሥር ጊዜ ለዋ​ወ​ጥ​ኸው። 42የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የይ​ስ​ሐ​ቅም ፍር​ሀት ከእኔ ጋር ባይ​ሆ​ንስ ዛሬ ባዶ እጄን በሰ​ደ​ድ​ኸኝ ነበር፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መዋ​ረ​ዴ​ንና የእ​ጆ​ችን ድካም አየ፤ ትና​ን​ትም ገሠ​ጸህ።”
የያ​ዕ​ቆ​ብና የላባ ስም​ም​ነት
43ላባም ለያ​ዕ​ቆብ እን​ዲህ ብሎ መለ​ሰ​ለት፥ “ሴቶቹ ልጆች ልጆች ናቸው፤ ወን​ዶ​ቹም ልጆች ልጆች ናቸው፤ መን​ጎ​ቹም ከብ​ቶች ናቸው፤ ይህ የም​ታ​የው ሁሉ የእኔ ነው፤ የል​ጆ​ችም ሀብት ነው፤ ዛሬም በእ​ነ​ዚህ በሴ​ቶች ልጆ​ችና በወ​ለ​ዱ​አ​ቸው ልጆ​ቻ​ቸው ላይ ምን አደ​ር​ጋ​ለሁ? 44አሁ​ንም ና፤ አን​ተና እኔ ቃል ኪዳን እን​ጋባ፤ በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ይሁን።” 45ያዕ​ቆ​ብም ድን​ጋይ ወስዶ ሐው​ልት አቆመ። 46ያዕ​ቆ​ብም ወን​ድ​ሞ​ቹን፥ “ድን​ጋይ ሰብ​ስቡ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ድን​ጋይ ሰብ​ስ​በው ከመሩ፤ በድ​ን​ጋ​ዩም ክምር ላይ በሉ። 47ላባም፥ “ይህች የድ​ን​ጋይ ክምር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ትሁን” አለው። ላባም “ወግረ ስምዕ” ብሎ ጠራት፤ ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲሁ አላት። 48ላባም፥ “ይህች ያቆ​ም​ኋት የድ​ን​ጋይ ክምር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ዛሬ ምስ​ክር ናት” አለ። ስለ​ዚ​ህም ስምዋ ወግረ ስምዕ ተባለ። 49ላባም አለው፥ “እኛ አን​ዳ​ችን ከሌ​ላው እን​ለ​ያ​ያ​ለ​ንና ራእ​ይን የገ​ለ​ጠ​ልኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ሆኖ ይመ​ል​ከት። 50ልጆ​ችን ብት​በ​ድ​ላ​ቸው ወይም በላ​ያ​ቸው ላይ ሚስ​ቶ​ችን ብታ​ገ​ባ​ባ​ቸው እነሆ፥ ከእኛ ጋር ያለ ሰው እን​ደ​ሌለ አስ​ተ​ውል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ኔና በአ​ንተ መካ​ከል ምስ​ክር ነው።” 51ላባም ያዕ​ቆ​ብን አለው፥ “እነሆ፥ ይህች የድ​ን​ጋይ ክም​ርና ይህ​ችም ሐው​ልት ምስ​ክ​ሮች ናቸው። 52እኔ ወደ አንተ በክ​ፋት ባልፍ ይህች የድ​ን​ጋይ ክምር፥ ይህ​ችም ሐው​ልት በክፉ ነገር ትከ​ተ​ለኝ። 53አን​ተም ወደ እኔ ብታ​ልፍ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ የና​ኮ​ርም አም​ላክ በእኛ መካ​ከል ይፍ​ረድ።” ያዕ​ቆ​ብም በአ​ባቱ በይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ማለ። 54ያዕ​ቆ​ብም በተ​ራ​ራው ላይ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም ጠራ፤ እነ​ር​ሱም በሉ፤ ጠጡም፤ በዚ​ያም በተ​ራ​ራው አደሩ። 55ላባም ማልዶ ተነ​ሥቶ ወን​ዶ​ች​ንና ሴቶ​ችን ልጆ​ቹን ሳመ፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ ላባም ተመ​ልሶ ወደ ስፍ​ራው ሄደ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ