የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 32

32
ያዕ​ቆብ ላባን ለመ​ገ​ና​ኘት እንደ ተዘ​ጋጀ
1ያዕ​ቆ​ብም መን​ገ​ዱን ሄደ፤ በዐ​ይ​ኖ​ቹም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሠራ​ዊት ከት​መው አየ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መላ​እ​ክ​ትም ተገ​ና​ኙት። 2ያዕ​ቆ​ብም በአ​ያ​ቸው ጊዜ፥ “እነ​ዚህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ናቸው” አለ፤ የዚ​ያ​ንም ስፍራ ስም “ተዓ​ይን” ብሎ ጠራው።
3ያዕ​ቆ​ብም ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም ሀገር በፊቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤ 4እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው፦ ባሪ​ያህ ያዕ​ቆብ እን​ዲህ አለ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ በላባ ዘንድ በስ​ደት ተቀ​መ​ጥሁ፤ እስከ ዛሬ ድረስ ቈየሁ፤ 5ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ አህ​ዮ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም፥ ወን​ዶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም፥ ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ንም አገ​ኘሁ፤ አሁ​ንም በፊ​ትህ ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው ለመ​ን​ገር ላክሁ።” 6የላ​ካ​ቸው መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ወደ ያዕ​ቆብ ተመ​ል​ሰው እን​ዲህ አሉት፥ “ወደ ወን​ድ​ምህ ወደ ዔሳው ሄደን ነበር፤ እር​ሱም ደግሞ ሊቀ​በ​ልህ ይመ​ጣል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች አሉ።” 7ያዕ​ቆ​ብም እጅግ ፈራ፤ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንም አጣ። ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉ​ትን ሰዎች ላሞ​ች​ንም፥ ግመ​ሎ​ች​ንም፥ በጎ​ች​ንም ሁለት ወገን አድ​ርጎ ከፈ​ላ​ቸው፤ 8ያዕ​ቆ​ብም እን​ዲህ አለ፥ “ዔሳው መጥቶ አን​ዱን ወገን የመታ እንደ ሆነ የቀ​ረው ወገን ይድ​ናል።” 9ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “የአ​ባቴ የአ​ብ​ር​ሃም አም​ላክ ሆይ፥ የአ​ባቴ የይ​ስ​ሐቅ አም​ላክ ሆይ፥ ‘ወደ ምድ​ርህ ወደ ተወ​ለ​ድ​ህ​በ​ትም ስፍራ ተመ​ለስ፤ በጎ​ነ​ት​ንም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ’ ያል​ኸኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሆይ፥ 10ለባ​ሪ​ያህ በአ​ደ​ረ​ግ​ኸው በም​ሕ​ረ​ት​ህና በእ​ው​ነ​ት​ህም ሁሉ በጎ​ውን አድ​ር​ግ​ልኝ፤ በት​ሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ግሬ ነበ​ርና፥ አሁን ግን የሁ​ለት ክፍል ሠራ​ዊት ሆንሁ። 11አቤቱ ከወ​ን​ድሜ ከዔ​ሳው እጅ አድ​ነኝ፤ መጥቶ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋኝ፥ እና​ትን#ዕብ. “እና​ቶ​ችን ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር” ይላል። ከል​ጆ​ችዋ ጋር እን​ዳ​ያ​ጠፋ እኔ እፈ​ራ​ዋ​ለ​ሁና። 12አን​ተም፦ ‘በር​ግጥ መል​ካም አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ፥ ዘር​ህ​ንም ከብ​ዛቱ የተ​ነሣ እን​ደ​ማ​ይ​ቈ​ጠር እንደ ባሕር አሸዋ አደ​ር​ጋ​ለሁ ብለህ ነበር።’ ”
13በዚ​ያ​ችም ሌሊት በዚ​ያው አደረ። ለወ​ን​ድሙ ለዔ​ሳ​ውም የሚ​ወ​ስ​ደ​ውን እጅ መንሻ አወጣ፤ 14ሁለት መቶ እን​ስት ፍየ​ሎ​ች​ንና ሃያ የፍ​የል አው​ራ​ዎ​ችን፥ ሁለት መቶ እን​ስት በጎ​ች​ንና ሃያ የበግ አው​ራ​ዎ​ችን፥ 15ሃምሳ#ዕብ. “ሠላሳ” ይላል። የሚ​ያ​ጠቡ ግመ​ሎ​ችን ከግ​ል​ገ​ሎ​ቻ​ቸው ጋር፥ አርባ ላም፥ ዐሥር በሬ፥ ሃያ እን​ስት አህያ፥ ዐሥ​ርም የአ​ህያ ውር​ን​ጫ​ዎች፤ 16መን​ጎ​ቹ​ንም ለየ​ብቻ ከፍሎ ለብ​ላ​ቴ​ኖቹ ሰጣ​ቸው፤ ብላ​ቴ​ኖ​ቹ​ንም፥ “በፊቴ እለፉ፤ መን​ጋ​ውን ከመ​ን​ጋው አርቁ” አላ​ቸው።
17የፊ​ተ​ኛ​ው​ንም እን​ዲህ ብሎ አዘ​ዘው፥ “ወን​ድሜ ዔሳው ያገ​ኘህ እንደ ሆነ፦ ‘አንተ የማን ነህ? ወዴ​ትስ ትሄ​ዳ​ለሀ? በፊ​ትህ ያለው ይህስ መንጋ የማን ነው?’ ብሎ የጠ​የ​ቀ​ህም እን​ደ​ሆነ፥ 18በዚያ ጊዜ አንተ፦ ‘ለጌ​ታዬ ለዔ​ሳው እጅ መንሻ የላ​ከው የአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የያ​ዕ​ቆብ ነው፤ እር​ሱም ደግሞ እነሆ ከኋ​ላ​ችን ተከ​ት​ሎ​ናል’ በለው።” 19እን​ዲ​ሁም ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንና ሦስ​ተ​ኛ​ውን፥ በፊቱ የሚ​ሄ​ዱ​ት​ንና መን​ጋ​ውን የሚ​ነ​ዱ​ትን ሁሉ እን​ዲሁ ብሎ አዘዘ፦“ ወን​ድሜ ዔሳ​ውን ባገ​ኛ​ች​ሁት ጊዜ ይህ​ንኑ ነገር ንገ​ሩት፤ 20እን​ዲ​ህም በሉ፦ እነሆ አገ​ል​ጋ​ይህ ያዕ​ቆብ ከኋ​ላ​ችን ነው። በፊቴ በሚ​ሄ​ደው እጅ መንሻ እታ​ረ​ቀ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ ምና​ል​ባት ይራ​ራ​ል​ኛል፤ ፊቱ​ንም አያ​ለሁ ብሎ​አ​ልና።” 21እጅ መን​ሻ​ውን ከእ​ርሱ አስ​ቀ​ድሞ ላከ፤ እርሱ ግን በዚ​ያች ሌሊት በሰ​ፈር አደረ።
የያ​ዕ​ቆብ ትግል
22በዚ​ያ​ችም ሌሊት ተነሣ፥ ሁለ​ቱን ሚስ​ቶ​ቹ​ንና ሁለ​ቱን ዕቁ​ባ​ቶ​ቹን ዐሥራ አን​ዱ​ንም ልጆ​ቹን ይዞ የያ​ቦ​ቅን ወንዝ ተሻ​ገረ። 23ወሰ​ዳ​ቸ​ውም፤ ወን​ዙ​ንም አሻ​ገ​ራ​ቸው፤ ገን​ዘ​ቡ​ንም ሁሉ አሻ​ገረ። 24ያዕ​ቆብ ግን ለብ​ቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታ​ገ​ለው ነበር። 25እን​ዳ​ላ​ሸ​ነ​ፈ​ውም ባየ ጊዜ የጭ​ኑን ሹልዳ ያዘው፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም የጭኑ ሹልዳ ሲታ​ገ​ለው ደነ​ዘዘ። 26እን​ዲ​ህም አለው፥ “ሊነጋ ጎሕ ቀድ​ዶ​አ​ልና ልቀ​ቀኝ።” እር​ሱም “ከአ​ል​ባ​ረ​ክ​ኸኝ አል​ለ​ቅ​ህም” አለው። 27እን​ዲ​ህም አለው፥ “ስምህ ማን ነው?” እር​ሱም፥ “ያዕ​ቆብ ነኝ” አለው። 28አለ​ውም፥ “ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይባል እንጂ ያዕ​ቆብ አይ​ባል፤ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና ከሰው ጋር ታግ​ለህ በር​ት​ተ​ሃ​ልና።” 29ያዕ​ቆ​ብም፥ “ስም​ህን ንገ​ረኝ” ብሎ ጠየ​ቀው። እር​ሱም፥ “ስሜን ለምን ትጠ​ይ​ቃ​ለህ? ድንቅ ነውና”#“ድንቅ ነውና” በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. እና በዕብ. የለም። አለው። 30በዚ​ያም ስፍራ ባረ​ከው። ያዕ​ቆ​ብም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰው​ነ​ቴም ዳነች” ሲል የዚ​ያን ቦታ ስም “ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር” ብሎ ጠራው። 31ራእየ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም በተወ ጊዜ ፀሐይ ወጣ​ች​በት። እር​ሱም በጭኑ ምክ​ን​ያት ያነ​ክስ ነበር። 32ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እስከ ዛሬ ድረስ የወ​ር​ችን ሹልዳ አይ​በ​ሉም፤ የያ​ዕ​ቆ​ብን ጭን ይዞ የወ​ር​ቹን ሹልዳ አደ​ን​ዝ​ዞ​አ​ልና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ