የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 33

33
ያዕ​ቆብ ዔሳ​ውን እንደ ተገ​ና​ኘው
1ያዕ​ቆ​ብም ዐይ​ኑን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ዔሳ​ውን ሲመጣ አየው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆ​ቹ​ንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለ​ቱም ዕቁ​ባ​ቶቹ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ 2ዕቁ​ባ​ቶ​ቹ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊት አደ​ረገ፤ ልያ​ንና ልጆ​ች​ዋን በኋላ፥ ራሔ​ል​ንና ዮሴ​ፍ​ንም ከሁሉ በኋላ አደ​ረገ። 3እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው አለፈ፤ ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳ​ውም እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ። 4ዔሳ​ውም ሊገ​ና​ኘው ሮጠ፤ አን​ገ​ቱ​ንም አቅፎ ሳመው፤ ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት አለ​ቀሱ። 5ዔሳ​ውም ዐይ​ኑን አነ​ሣና ሴቶ​ች​ንና ልጆ​ችን አየ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እነ​ዚህ ምኖ​ችህ ናቸው?” እር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ የሰ​ጠኝ ልጆች ናቸው” አለ። 6ዕቁ​ባ​ቶ​ቹም ከል​ጆ​ቻ​ቸው ጋር ቀር​በው ሰገዱ፤ 7ደግ​ሞም ልያና ልጆ​ችዋ ቀር​በው ሰገ​ዱ​ለት፤ ከዚ​ያም በኋላ ዮሴ​ፍና ራሔል ቀር​በው ሰገዱ። 8ዔሳ​ውም፥ “ያገ​ኘ​ሁት ይህ ሠራ​ዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እር​ሱም፥ “በጌ​ታዬ ፊት ሞገ​ስን አገኝ ዘንድ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ልህ ነው” አለ። 9ዔሳ​ውም፥ “ለእኔ ብዙ አለኝ፤ ወን​ድሜ ሆይ፥ የአ​ንተ ለአ​ንተ ይሁን” አለ። 10ያዕ​ቆ​ብም አለ፥ “እን​ደ​ዚህ አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን በፊ​ትህ ሞገ​ስን አግ​ኝቼ እንደ ሆንሁ እጅ መን​ሻ​ዬን ከእጄ ተቀ​በ​ለኝ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፊት እን​ደ​ሚ​ያይ ፊት​ህን አይ​ቻ​ለ​ሁና፥ በቸ​ር​ነ​ትም ተቀ​ብ​ለ​ኸ​ኛ​ልና። 11ከወ​ደ​ድ​ኸ​ኝስ ይህ​ችን ያመ​ጣ​ሁ​ል​ህን በረ​ከ​ቴን ተቀ​በል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ራር​ቶ​ል​ኛ​ልና፥ ለእ​ኔም ብዙ አለ​ኝና።” እስ​ኪ​ቀ​በ​ለ​ውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀ​በ​ለ​ውም። 12እር​ሱም፥ “ተነ​ሣና ወደ ፊት እን​ሂድ” አለው። 13እር​ሱም አለው፥ “ጌታዬ ሆይ፥ ልጆቹ ደካ​ሞች እንደ ሆኑ ታው​ቃ​ለህ፤ በጎ​ችና ላሞ​ችም ግል​ገ​ሎ​ቻ​ቸ​ውን ያጠ​ባሉ፤ ሰዎ​ችም በአ​ንድ ወይም በሁ​ለት ቀን በች​ኮላ የነ​ዱ​አ​ቸው እንደ ሆነ ከብ​ቶቹ ሁሉ ይሞ​ታሉ። 14ጌታዬ ከአ​ገ​ል​ጋዩ ፊት ቀድሞ ይለፍ፤ እኛም እንደ ቻልን እን​ሄ​ዳ​ለን፤ በጎ​ዳ​ናም እን​ው​ላ​ለን፤ ወደ ጌታ​ችን ወደ ሴይር እስ​ክ​ን​ደ​ር​ስም በሕ​ፃ​ናቱ ርምጃ መጠን እን​ሄ​ዳ​ለን” አለው። 15ዔሳ​ውም፥ “ከእኔ ጋር ካሉ ሰዎች ከፍዬ ልተ​ው​ል​ህን?” አለ። እር​ሱም፥ “ይህ ለም​ን​ድን ነው? በጌ​ታዬ ዘንድ ሞገ​ስን ማግ​ኘቴ ይበ​ቃ​ኛል” አለ። 16ዔሳ​ውም በዚያ ቀን ወደ ሴይር ተመ​ለሰ። 17ያዕ​ቆብ ግን በሰ​ፈሩ አደረ፤#ዕብ. “ያዕ​ቆብ ግን ወደ ሱኮት ሄደ” ይላል። በዚ​ያም ለእ​ርሱ ቤትን ሠራ፤ ለከ​ብ​ቶ​ቹም ዳሶ​ችን አደ​ረገ፤ ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያን ቦታ ስም ማኅ​ደር ብሎ ጠራው።
18ያዕ​ቆ​ብም ከሁ​ለቱ ወን​ዞች መካ​ከል በተ​መ​ለሰ ጊዜ በከ​ነ​ዓን ምድር ወዳ​ለ​ችው ወደ ሰቂ​ሞን ከተማ ወደ ሴሎም መጣ፤ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ፊት ለፊት ሰፈረ። 19ድን​ኳ​ኑን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ርሻ ክፍል ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው። 20በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን አቆመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ጠራ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ