ኦሪት ዘፍጥረት 34
34
የኤሞር ልጅ ዲናን እንደ አስነወራት
1ለያዕቆብ የተወለደች የልያ ልጅ ዲናም የዚያን ሀገር ሴቶች ልጆችን ለማየት ወጣች። 2የሀገሩ አለቃ የኤዊያዊው ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት፤ ወሰዳትም፤ ከእርስዋም ጋር ተኛ፤ አስነወራትም። 3ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ፤ ብላቴናዪቱንም ወደዳት፤ ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት። 4ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፥ “ይህችን ብላቴና አጋባኝ” ብሎ ነገረው። 5ያዕቆብም ልጁን ዲናን የኤሞር ልጅ እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም ልጆቹ እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ። 6የሴኬም አባት ኤሞርም ይነግረው ዘንድ ወደ ያዕቆብ መጣ። 7የያዕቆብም ልጆች ከምድረ በዳ መጡ፤ ይህንም በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ደነገጡ፤ የያዕቆብን ልጅ በመተኛቱ በእስራኤል ላይ ኀፍረትን ስላደረገ አዘኑ፤ እጅግም ተቈጡ፤ እንዲህ አይደረግምና። 8ኤሞርም እንዲህ ብሎ ነገራቸው፥ “ልጄ ሴኬም ልጃችሁን ወዶአታልና ሚስት እንድትሆነው እርስዋን ስጡት። 9ጋብቾችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆቻችሁን ስጡን፤ እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች ለልጆቻችሁ ውሰዱ። 10ከእኛም ጋር ተቀመጡ፤ ምድራችንም በፊታችሁ ሰፊ ናት፤ ኑሩባት፤ ነግዱም፤ ግዙአትም።” 11ሴኬምም አባቷንና ወንድሞችዋን እንዲህ አለ፥ “በፊታችሁ ሞገስን በአገኝ የምትሉትን ሁሉ እሰጣለሁ። 12ብዙ ማጫ አምጣ በሉኝ፤ በምትጠይቁኝም መጠን እሰጣለሁ፤ ይህችን ብላቴና ግን ሚስት ትሆነኝ ዘንድ ስጡኝ።” 13የያዕቆብም ልጆች ለሴኬምና ለአባቱ ለኤሞር በተንኰል መለሱ፤ እኅታቸውን ዲናን አስነውሮአታልና፤ 14የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊም እንዲህ አሉአቸው፥ “እኅታችንን ላልተገረዘ ሰው ለመስጠት ይህን ነገር እናደርግ ዘንድ አይቻለንም፤ ይህ ነውር ይሆንብናልና። 15እናንተም እንደ እኛ ወንዶቻችሁን ሁሉ ብትገርዙ በዚህ ብቻ እንመስላችኋለን፤ ከእናንተም ጋር እንኖራለን፤ 16ሴቶች ልጆቻችንንም እንሰጣችኋለን፤ የእናንተንም ሴቶች ልጆች ለሚስትነት እንወስዳለን፤ አንድ ሕዝብም ሆነን ከእናንተ ጋር እንኖራለን። 17ትገረዙ ዘንድ እኛን ባትሰሙ ግን ልጃችንን ይዘን እንሄዳለን።”
18ነገራቸውም ኤሞርንና የኤሞርን ልጅ ሴኬምን ደስ አሰኛቸው። 19ብላቴናውም ይህን ነገር ያደርግ ዘንድ አልዘገየም፤ የያዕቆብን ልጅ ወድዶአልና፤ እርሱም ከአባቱ ቤተ ሰብእ ሁሉ የከበረ ነበረ። 20ኤሞርና ልጁ ሴኬምም ሄዱና ወደ ከተማቸው በር ደረሱ፤ ለከተማቸውም ሰዎች ሁሉ እንዲህ ብለው ነገሩ፦ 21“እነዚህ ሰዎች በእኛ ዘንድ የሰላም ሰዎች ናቸው፤ በምድራችን ይቀመጡ፤ ይነግዱባትም፤ እነሆም፥ ምድሪቱ ሰፊ ናት፤ ሴቶች ልጆቻቸውን ለሚስትነት እንውሰድ፤ ለእነርሱም ሴቶች ልጆቻችንን እንስጥ። 22እነርሱ እንደ እኛ ይሆኑ ዘንድ በዚህ ብቻ እንምሰላቸው። አንድ ወገንም እንሁን፤ እነርሱ እንደሚገርዙ ወንዶቻችንን ሁሉ እንገርዛለን። 23መንጋቸውም፥ የጋማ ከብቶቻቸውም፥ ገንዘባቸውም ሁሉ ለእኛ አይደሉምን? ነገር ግን በዚህ ብቻ ከመሰልናቸው ከእኛ ጋር ይቀመጣሉ።” 24በከተማዪቱም በር የሚገቡ ሁሉ ኤሞርንና ልጁን ሴኬምን እሺ አሉ፤ ወንዶችም ሁሉ የሰውነታቸውን ሸለፈት ተገረዙ።#ዕብ. “ከከተማዪቱ አደባባይ የሚወጡት ወንዶች ሁሉ ተገረዙ” ይላል።
የዲና ወንድሞች በቀል
25እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን እጅግ ቈስለው ሳሉ ሁለቱ የያዕቆብ ልጆች የዲና ወንድሞች ስምዖንና ሌዊ እየራሳቸው ሰይፋቸውን ይዘው ተደፋፍረው ወደ ከተማ ገቡ፤ ወንዱንም ሁሉ ገደሉ፤ 26ኤሞርንና ልጁን ሴኬምንም በሰይፍ ገደሉ፤ እኅታቸው ዲናንም ከሴኬም ቤት ይዘው ወጡ። 27የያዕቆብ ልጆችም ወደ ሞቱት ገብተው እኅታቸው ዲናን ያስነወሩባትን ከተማዪቱን ዘረፉ፤ 28ላሞቻቸውንም፥ በጎቻቸውንም፥ አህዮቻቸውንም በሜዳም፥ በከተማም ያለውን ወሰዱ ። 29ሎሌዎቻቸውንና ሚስቶቻቸውን፥ የቤታቸውንም ቈሳቍስ#ዕብ. “ሀብታቸውን ሁሉ፥ ሕፃናቶቻቸውን ሁሉ፥ ሴቶቻቸውንም ሁሉ” ይላል። ሁሉ ማረኩ፤ በቤትና በከተማ ያለውንም ሁሉ ዘረፉ። 30ያዕቆብም ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፥ “ክፉ አደረጋችሁብኝ፤ በዚች ሀገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዜዎናውያን ሰዎች ዘንድ አስጠላችሁኝ። እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፤ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይወጉኛል፤ እኔና ቤቴም እንጠፋለን።” 31እነርሱም፥ “እኅታችንን እንደ አመንዝራ አድርገው ለምን አዋረዷት?” አሉት።
Currently Selected:
ኦሪት ዘፍጥረት 34: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ