የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ሆሴዕ 10

10
የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ በእ​ስ​ራ​ኤል ጣዖት ላይ
1እስ​ራ​ኤል ፍሬው የበ​ዛ​ለት የለ​መ​ለመ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠ​ዊ​ያ​ዉን አብ​ዝ​ቶ​አል፤ እንደ ምድ​ሩም ማማር መጠን ሐው​ል​ቶ​ችን ሠር​ተ​ዋል። 2ልባ​ቸው ተከ​ፈለ፤ አሁ​ንም ይጠ​ፋሉ፤ እርሱ መሠ​ዊ​ያ​ቸ​ውን ያፈ​ር​ሳል፤ ሐው​ል​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ያጠ​ፋል። 3አሁ​ንም፥ “ንጉሥ የለ​ንም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ፈ​ራ​ን​ምና፤ ንጉ​ሥስ ምን ያደ​ር​ግ​ል​ናል?” ይላሉ።
4የማ​ይ​ረ​ባ​ውን የሐ​ሰት ቃል ይና​ገ​ራሉ፤ ቃል ኪዳ​ንም ያደ​ር​ጋሉ፤ ስለ​ዚህ መር​ዛም ሣር በእ​ርሻ ትልም ላይ እን​ደ​ሚ​በ​ቅል ፍርድ ይበ​ቅ​ል​ባ​ቸ​ዋል። 5የሰ​ማ​ርያ ሰዎች በቤ​ት​አ​ዌን እን​ቦሳ አጠ​ገብ ይኖ​ራሉ፤ ሕዝቡ ያለ​ቅ​ሱ​ለ​ታል፤ ክብ​ሩም ከእ​ርሱ ዘንድ ወጥ​ቶ​አ​ልና እን​ዳ​ዘ​ኑ​በት እን​ዲሁ በክ​ብሩ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። 6ለን​ጉሡ ለኢ​ያ​ሪም እጅ መንሻ ይሆን ዘንድ አስ​ረው ወደ አሦር ይወ​ስ​ዱ​ታል፤ ኤፍ​ሬ​ምን እፍ​ረት ይይ​ዘ​ዋል፤ እስ​ራ​ኤ​ልም በም​ክሩ ያፍ​ራል። 7ሰማ​ርያ ንጉ​ሥ​ዋን እንደ ጥራጊ በውኃ ላይ ጣለ​ችው። 8የእ​ስ​ራ​ኤል ኀጢ​አት የሆ​ኑት የአ​ዎን የኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገ​ጃ​ዎች ይፈ​ር​ሳሉ፤ እሾ​ህና አሜ​ከ​ላም በመ​ሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ላይ ይበ​ቅ​ላሉ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም፥ “ክደ​ኑን፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም፦ ውደ​ቁ​ብን” ይሉ​አ​ቸ​ዋል።
9እስ​ራ​ኤል ከጊ​ብዓ#ግእዝ “አው​ግር” ይላል። ዘመን ጀምሮ ኀጢ​አ​ትን ሠር​ቶ​አል፤ በዚ​ያም ጸን​ተ​ዋል፤ በጊ​ብዓ ላይ ጦር አይ​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ው​ምን? መጥ​ቶም የዐ​መፅ ልጆ​ችን ገሠ​ጻ​ቸው፤ 10ስለ ሁለ​ቱም ኀጢ​አ​ቶ​ቻ​ቸው በገ​ሠ​ጻ​ቸው ጊዜ አሕ​ዛብ በላ​ያ​ቸው ይሰ​በ​ሰ​ቡ​ባ​ቸ​ዋል። 11ኤፍ​ሬ​ምም ቀን​በ​ርን እንደ ለመ​ደች ጊደር ነው፤ እኔ ግን በአ​ን​ገቱ ውበት እጫ​ን​በ​ታ​ለሁ፤ በኤ​ፍ​ሬም ላይ እጠ​ም​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ይሁ​ዳ​ንም እለ​ጕ​መ​ዋ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብም ለራሱ መን​ግ​ሥ​ትን ያስ​ተ​ካ​ክ​ላል።#ዕብ. “ይሁ​ዳም ያር​ሳል” ይላል።
12ለእ​ና​ንተ ጽድ​ቅን ዝሩ፤ የሕ​ይ​ወት ፍሬን ሰብ​ስቡ፤ የጥ​በ​ብ​ንም ብር​ሃን ለራ​ሳ​ችሁ አብሩ፤ የጽ​ድ​ቃ​ችሁ መከር እስ​ኪ​ደ​ርስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት። 13ዐመ​ፅን ለምን ተከ​ላ​ችሁ? ኀጢ​አ​ት​ንስ ለምን አጨ​ዳ​ችሁ፤ የሐ​ሰ​ት​ንም ፍሬ በል​ታ​ች​ኋል፤ በሠ​ረ​ገ​ሎ​ች​ህና በሠ​ራ​ዊ​ትህ ብዛት ታም​ነ​ሃል። 14በሕ​ዝ​ብ​ህም መካ​ከል ጥፋት ይነ​ሣል፤ እና​ትም በል​ጆ​ችዋ ላይ በተ​ጣ​ለች ጊዜ የሰ​ል​ማን አለቃ ቤት​አ​ር​ብ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ቀን እን​ዳ​ፈ​ረሰ፥ አም​ባ​ዎ​ችህ ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ። 15የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ከኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ ክፋት የተ​ነሣ እን​ዲሁ አደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ በነ​ጋም ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ንጉሥ ይጥ​ሉ​ታል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ