ትንቢተ ኢሳይያስ 1
1
በይሁዳ የተነገረ ትንቢት
1በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም፥ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ስለ ይሁዳና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው የአሞጽ ልጅ የኢሳይያስ ራእይ።
2እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፥ “ሰማይ ስማ፤#ዕብ. “ሰማያት ስሙ” ይላል። ምድርም አድምጪ፤ ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም፤ እነርሱም ዐመፁብኝ። 3በሬ ገዢውን አህያም የጌታውን ጋጥ ዐወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቁኝም፤ ሕዝቤም አላስተዋሉኝም።”
4ኀጢአተኛ ወገንና ዐመፅ የተሞላበት ሕዝብ፥ የክፉዎች ዘር፥ በደለኞች ልጆች ሆይ፥ ወዮላችሁ! እግዚአብሔርን ተዋችሁት፤ የእስራኤልንም ቅዱስ አስቈጣችሁት። 5እንግዲህ በበደል ላይ በደል እየጨመራችሁ ለምን ትቀሠፋላችሁ? ራስ ሁሉ ለሕማም፥ ልብም ሁሉ ለኀዘን ሆኖአል። 6ከእግር ጫማ አንሥቶ እስከ ራስ ድረስ ጤና የለውም፤ ቍስልና እበጥ የሚመግልም ነው፤ አልፈረጠም፤ አልተጠገነምም፤ በዘይትም አልለዘበም። 7ምድራችሁ ባድማ ናት፤ ከተሞቻችሁ በእሳት ተቃጠሉ፤ እርሻችሁንም በፊታችሁ ባዕዳን ይበሉታል፤ ጠላትም ያጠፋዋል፤ ባድማም ያደርገዋል። 8የጽዮንም ሴት ልጅ በወይን ቦታ እንዳለ ዳስ፥ እንደ አዝመራ ጠባቂም ጎጆ፥#ዕብ. እና ግሪክ “በዱባ ተክል ውስጥም እንደ ጎጆ” ይላል። እንደ ተከበበችም ከተማ ሆና ቀረች። 9የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዘርን ባያስቀርልን ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን፥ እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር።
10እናንተ የሰዶም አለቆች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እናንተ የገሞራ ሕዝብ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ሕግ አድምጡ። 11“የመሥዋዕታችሁ ብዛት ለእኔ ምንድን ነው?”#ዕብ. “ምን ይጠቅመኛል?” ይላል። ይላል እግዚአብሔር፤ “የሚቃጠለውን የአውራ በግ መሥዋዕትንና የፍሪዳን ስብ ጠግቤአለሁ፤ የበሬና#ዕብ. “የበግ ጠቦት” የሚል ይጨምራል። የአውራ ፍየልም ደም ደስ አያሰኘኝም። 12በእኔ ፊት ልትታዩ ብትመጡ፥ ይህን ከእጃችሁ የሚሻ ማን ነው? እንግዲህ አደባባዬን ደግማችሁ አትረግጡም። 13መልካሙን የስንዴ ዱቄት ብታመጡ እንኳ ከንቱ ነው፤ ዕጣናችሁ በእኔ ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ መባቻዎቻችሁንና ሰንበቶቻችሁን፥ ታላቋን፥ ቀናችሁን፥ ጾማችሁንና ሥራ መፍታታችሁን#ዕብ. “በጉባኤ መሰብሰባችሁን አልወድድም ፤ በደልንም የተቀደሰውንም ጉባኤ አልታገሥም”ይላል። አልወድም። 14መባቻችሁንና በዓላቶቻችሁን ነፍሴ ጠልታለች፤ አስጸያፊ ሆናችሁብኛል፤ ኀጢአታችሁንም ይቅር አልልም። 15እጃችሁን ወደ እኔ ብትዘረጉ፥ ዐይኖችን ከእናንተ እመልሳለሁ፤ ምህላንም ብታበዙ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ ደምን ተሞልተዋልና። 16ታጠቡ፤ ንጹሓንም ሁኑ፤ የሰውነታችሁን ክፋት ከዐይኖች ፊት አስወግዱ፤ ክፉ ማድረግንም ተዉ፤ 17መልካም መሥራትን ተማሩ፤ ፍርድን ፈልጉ፤ የተገፋውን አድኑ፤ ለድሃአደጉ ፍረዱለት፤ ስለ መበለቲቱም ተሙአገቱ።”
18“ኑና እንዋቀስ” ይላል እግዚአብሔር፤ ኀጢአታችሁ እንደ አለላ ቢሆን እንደ በረዶ አነጻዋለሁ፤ እንደ ደምም ቢቀላ እንደ ባዘቶ አጠራዋለሁ። 19እሽ ብትሉና ብትሰሙኝ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ 20እንቢ ብትሉና ባትሰሙኝ ግን ሰይፍ ትበላችኋለች፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።
ኀጢአት የሞላባት ከተማ
21ፍርድ መልቶባት የነበረ የታመነችይቱ የጽዮን#በዕብራይስጥ የለም። ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ አድሮባት ነበር፤ አሁን ግን ወንበዴዎችና ነፍሰ ገዳዮች አሉባት። 22ወርቅሽና ብርሽ ዛገ፥#ግሪኩ “ብራችሁ ዛገ” ይላል። የወይን ጠጅ አሳላፊዎችሽም በወይን ጠጅሽ ላይ ውኃን ይደባልቃሉ። 23አለቆችሽ ዐመፀኞችና የሌቦች ባልንጀሮች ሆኑ፤ ሁሉ ጉቦ ይወድዳሉ፤ ፍርድንም ሊያጣምሙ ይፈልጋሉ፤ ለሙት ልጅ አይፈርዱም፤ የመበለቲቱንም አቤቱታ አያዳምጡም።
24ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ለእስራኤል ኀያላን ወዮላቸው! በጠላቶች ላይ ቍጣዬ አይበርድም፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ። 25እጄንም በአንቺ ላይ አመጣለሁ፤ አግልሻለሁ፤ ዝገትሽንም አነጻለሁ፤ ቆርቆሮሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ፤#“ቆርቆሮሽንም ሁሉ አስወግዳለሁ” የሚለው በግሪኩ የለም። ዐመፀኞችን አጠፋለሁ፤ ሕገ ወጦችንም ከአንቺ አስወግዳለሁ፤ ትዕቢተኞችንም አዋርዳለሁ። 26ፈራጆችሽንም እንደ ቀድሞ፥ አማካሪዎችሽንም እንደ መጀመሪያ ጊዜ አስነሣለሁ፤ ከዚያም በኋላ የጽድቅ ከተማ፥ የታመነችም ጽዮን ርእሰ ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ። 27ምርኮኞችሽ በእውነትና በምጽዋት ይድናሉ። 28በደለኞችና ኀጢአተኞች ግን በአንድነት ይቀጠቀጣሉ፤ እግዚአብሔርንም የሚተዉት ሁሉ ይጠፋሉ። 29በወደዱአቸው ጣዖታት ያፍራሉና፥ በፈለጉአቸውም የአድባር ዛፎች ዕፍረት ይይዛቸዋልና፤ 30ቅጠልዋ እንደ ረገፈ የጠርቤንቶስ ዛፍ፥ ውኃም እንደሌለበት የአትክልት ቦታ ይሆናሉና። 31ኀይላቸውም እንደ መቃ መስዬ፥ ሥራቸውም እንደ ጠለሸት ይሆናል፤ ኃጥአንና ዐማፅያንም አብረው ይቃጠላሉ፤ እሳቱንም የሚያጠፋላቸው ያጣሉ።”
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 1: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ