የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 32

32
በጽ​ድቅ የሚ​ያ​ስ​ተ​ዳ​ድር ንጉሥ
1እነሆ፥ ጻድቅ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ መሳ​ፍ​ን​ትም በፍ​ርድ ይገ​ዛሉ። 2ሰውም ቃሉን ይሰ​ው​ራል፤ በውኃ እን​ደ​ሚ​ጠ​ል​ቅም ይሰ​ወ​ራል፤ ክብ​ሩም በደ​ረቅ ምድር እን​ደ​ሚ​ፈ​ስስ ውኃ በጽ​ዮን ይገ​ለ​ጣል። 3እን​ግ​ዲህ በሰው አይ​ታ​መ​ኑም፤ በጆ​ሮ​አ​ቸው ያዳ​ም​ጣሉ እንጂ። 4የደ​ካ​ሞች ሰዎች ልብ ዕው​ቀ​ትን ትሰ​ማ​ለች፤ የተ​ብ​ታ​ቦ​ችም ምላስ ፈጥና የሰ​ላ​ምን ነገር ትማ​ራ​ለች። 5ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ሰነ​ፍን አለቃ ይሆን ዘንድ ግድ አይ​ሉ​ትም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ሎሌህ ዝም በል አይ​ል​ህም።#ዕብ. “ሰነፍ ከበ​ርቴ ተብሎ አይ​ጠ​ራም፥ ንፉ​ግም ለጋስ አይ​ባ​ልም” ይላል። 6ሰነፍ ግን ስን​ፍ​ናን ይና​ገ​ራል፤ ልቡም ዐመ​ፅን ያደ​ርግ ዘንድ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ስሕ​ተ​ትን ይና​ገር ዘንድ፥ የተ​ራ​በ​ች​ው​ንም ሰው​ነት ይበ​ትን ዘንድ፥ የተ​ጠ​ማ​ች​ንም ነፍስ ባዶ ያደ​ርግ ዘንድ ከን​ቱን ያስ​ባል። 7በዐ​መ​ፃ​ቸው ነገር ድሃ​ውን ይገ​ድ​ሉት ዘንድ፥ የድ​ሆ​ች​ንም ፍርድ ይገ​ለ​ብጡ ዘንድ የክ​ፉ​ዎች ሕሊና ዐመ​ፅን ትመ​ክ​ራ​ለች። 8ጻድ​ቃን ግን ጥበ​ብን ይመ​ክ​ራሉ፤ ምክ​ራ​ቸ​ውም ትጸ​ና​ለች።#ዕብ. “ከበ​ርቴ ሰው ግን ለመ​ክ​በር ያስ​ባል ፤ በመ​ከ​በ​ርም ጸንቶ ይኖ​ራል” ይላል።
9እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ሴቶች ሆይ፥ ተነሡ፤ ድም​ፄ​ንም ስሙ፤ እና​ንተ ተማ​ም​ና​ችሁ የም​ት​ቀ​መጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ንግ​ግ​ሬን አድ​ምጡ። 10በየ​ዓ​መቱ የኀ​ዘን በዓል መታ​ሰ​ቢያ አድ​ርጉ፤ ወይን መቍ​ረጥ አል​ፎ​አል፤ ፍሬ ማከ​ማ​ች​ትም አል​ቆ​አል፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​መ​ጣም። 11እና​ንተ ተማ​ም​ና​ችሁ የም​ት​ቀ​መጡ ደን​ግጡ፤ ሴቶች ሆይ፥ እዘኑ፤ ልብ​ሳ​ች​ሁ​ንም አው​ልቁ፤ ዕራ​ቁ​ታ​ች​ሁ​ንም ሁኑ፤ ወገ​ባ​ች​ሁ​ንም በማቅ ታጠቁ። 12ስለ ተወ​ደ​ደ​ችዉ እርሻ ስለ​ሚ​ያ​ፈ​ራ​ውም ወይን ደረ​ታ​ች​ሁን ድቁ። 13በሕ​ዝቤ ምድር ላይ በእ​ር​ሻ​ቸ​ውም ላይ እሾ​ህና አሜ​ከላ ይበ​ቅ​ላሉ፤ ደስ​ታም ከቤ​ታ​ቸው ሁሉ ይጠ​ፋል። 14የበ​ለ​ጸ​ገች ከተ​ማና ቤቶ​ችዋ ምድረ በዳ ይሆ​ናሉ። የከ​ተ​ማ​ውን ሀብ​ትና ያማሩ ቤቶ​ችን ይተ​ዋሉ፤ አን​ባ​ዎ​ችም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ዋሻ፥ የም​ድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመ​ን​ጎ​ችም ማሰ​ማ​ሪያ ይሆ​ናሉ። 15ይህም፥ መን​ፈስ ከላይ እስ​ኪ​መ​ጣ​ላ​ችሁ፥ ምድረ በዳ​ውም ፍሬ​ያማ እርሻ እስ​ኪ​ሆን፥ ፍሬ​ያ​ማ​ውም እርሻ ዱር ተብሎ እስ​ኪ​ቈ​ጠር ድረስ ይሆ​ናል።
16ከዚያ በኋላ ፍርድ በም​ድረ በዳ ይኖ​ራል፤ ጽድ​ቅም በፍ​ሬ​ያ​ማው እርሻ ያድ​ራል። 17የጽ​ድ​ቅም ሥራ ሰላም ይሆ​ናል፤ ጽድ​ቅም የዕ​ረ​ፍት ቦታን ይይ​ዛል፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይታ​መ​ኑ​በ​ታል። 18ሕዝ​ቤም በሰ​ላም ከተማ ይኖ​ራል። ተዘ​ል​ሎም በው​ስ​ጥዋ ያድ​ራል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ናም ያር​ፋል። 19በረዶ ቢወ​ርድ አይ​ደ​ር​ስ​ባ​ች​ሁም፤ በዛፍ ሥር የሚ​ኖሩ ሰዎች በበ​ረሃ እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰዎች ታም​ነው ይኖ​ራሉ። 20ውኃ ባለ​በት፥ በሬና አህ​ያም በሚ​ረ​ግ​ጠው ቦታ የሚ​ዘሩ ብፁ​ዓን ናቸው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

YouVersion የእርስዎን ተሞክሮ ግላዊ ለማድረግ ኩኪዎችን ይጠቀማል። የእኛን ድረ ገጽ በመጠቀም፣ በግለሰብነት መመሪያችን ላይ እንደተገለጸው የእኛን የኩኪዎች አጠቃቀም ተቀብለዋል