ትንቢተ ኢሳይያስ 33
33
ከጠላት ስለ መዳን የተነገረ ትንቢት
1ለሚያዋርዱአችሁ ወዮላቸው! እናንተን ግን የሚያዋርዳችሁ የለም፤ የሚወነጅላችሁ እናንተን የሚወነጅል አይደለም፤ ወንጀለኞች ይጠመዳሉ፤ ይያዛሉም፤ ብል እንደበላው ልብስም ያልቃሉ።#ምዕ. 33 ቍ. 1 የዕብ. ልዩ ነው። 2አቤቱ፥ ማረን፤ አንተን ተማምነናልና፤ የዐላውያን ዘራቸው ለጥፋት ነው፤#ዕብ. “ጥዋት ጥዋት ክንድ ሁነን፥” ይላል። በመከራም ጊዜ መድኀኒታችን አንተ ነህ። 3ከቃልህ ግርማ የተነሣ አሕዛብ ፈርተው ሸሹ፤ አሕዛብም ተበተኑ።
4አንበጣ እንደሚሰበሰብ ትንሹም ትልቁም ምርኮአችሁ እንዲሁ ይሰበሰብላችኋል።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “እንዲሁ ያፌዙባችኋል” ይላል። 5በአርያም የሚኖር ቅዱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ይኖራል፤ ጽዮንም ፍርድንና ጽድቅን ተሞላች። 6በድኅነታችን መዝገብ በሕግ ይሰበስቡአቸዋል፤ ጥበብና ምክር፥ ጽድቅም ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ እነዚህም የጽድቅ መዝገቦች ናቸው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ከግእዙ ይለያል።
7እነሆ እናንተ ቀድሞ ትፈሩአቸው የነበሩ በግርማችሁ ይፈሩአችኋል፤ ከእናንተም የተነሣ ይንቀጠቀጣሉ። መልእክተኞች መራራ ልቅሶን እያለቀሱ ይላካሉ፤ ሰላምንም ይለምናሉ። 8መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ የአሕዛብም መፈራት ቀረ፤ ቃል ኪዳናቸውም ፈረሰ፤ እንደ ሰውም አልተመለከታቸውም። 9ምድር አለቀሰች፤ ሊባኖስ አፈረ፤ ሳሮንም እንደ ምድረ በዳ ሆነ፤ ገሊላና ቀርሜሎስ ታወቁ።
10እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “አሁን እነሣለሁ፤ አሁን እከብራለሁ፤ አሁን ከፍ ከፍ እላለሁ። 11ዛሬ ታያላችሁ፤ ዛሬ ታደንቃላችሁ፤ የመንፈሳችሁም ኀይል ከንቱ ይሆናል፤ እሳትም ትበላችኋለች።#ዕብ. “ገለባን ትጸንሳላችሁ ፤ እብቅንም ትወልዳላችሁ ፤ እስትንፋሳችሁ የምትበላችሁ እሳት ናት” ይላል። 12አሕዛብም በእርሻ ውስጥ ተቈርጦ እንደ ተጣለና በእሳት እንደ ተቃጠለ እሾህ የተቃጠሉ ይሆናሉ።”
13በሩቅ ያሉ የሠራሁትን ይሰማሉ፤ በቅርብም ያሉ ኀይሌን ያውቃሉ። 14በጽዮን ያሉ ኀጢአተኞች ፈሩ፤ መንቀጥቀጥ ዝንጉዎችን ያዘ፤ እሳት እንደሚነድድ የሚነግራችሁ ማን ነው? የዘለዓለም ሀገርንስ የሚነግራችሁ ማን ነው? 15በጽድቅ የሚሄድ፥ ቅን ነገርንም የሚናገር፥ በደልንና ኀጢአትን የሚጠላ፥ መማለጃን ከመጨበጥ እጁን የሚያራግፍ፥ ደም ማፍሰስን ከመስማት ጆሮቹን የሚደፍን፥ ክፋትንም ከማየት ዐይኖቹን የሚጨፍን ነው። 16እርሱ ከፍ ባለ በጽኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖራል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፤ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።
ስለሚመጣው የክብር ዘመን
17ንጉሥን በክብሩ ታዩታላችሁ፤ ዐይኖቻችሁም በሩቅ ያለች ምድርን ያዩአታል። 18ልባችሁም፥ “ጸሓፊዎች ወዴት አሉ? መማክርትስ ወዴት አሉ? የትንሹና የትልቁ ዐማፅያን ብዛትስ ወዴት አለ?” ብሎ ፍርሀትን ያስባል። 19የማታውቋቸውን አሕዛብ አመጣባችኋለሁ፤ እናንት ዐማፅያን ሕዝብ፥ ጥልቅ ነገርን ትሰማላችሁ። የሚሰማም ማስተዋል እንደሌለው ይሆናል።
20እነሆ፥ የመድኀኒታችንን ከተማ ጽዮንን ተመልከት፤ ዐይኖችህም ድንኳኖችዋ የማይናወጡ፥ ካስማዎችዋ ለዘለዓለም የማይነቀሉ፥ አውታሮችዋም ሁሉ የማይበጠሱ፥ የበለጸገች ከተማ ኢየሩሳሌምን ያያሉ። 21የእግዚአብሔር ስም ለእናንተ ታላቅ ነው፤ ሀገራችሁም የሰፉ ወንዞችና ታላቅ የመስኖ ስፍራ ይሆናል፤ በዚህች መንገድ አትሄድም፤ መርከቦችም አይሄዱም። 22አምላካችን እግዚአብሔር ታላቅ ነውና ቸል አይለንም፤ እግዚአብሔር ፈራጃችን ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችን#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አለቃችን” ይላል። ነው። እግዚአብሔር ንጉሣችን ነው፤ እርሱ እግዚአብሔር ያድነናል።
23ገመዶችሽ ተበጥሰዋል፤ ጥንካሬ የላቸውምና፤ ደቀልሽ ዘመመ፤ ሸራውንም መዘርጋት አልቻለም፤ እስከሚያዝም ድረስ አላማውን አልተሸከመም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ተከፈለ፤ ብዙ አንካሶች እንኳ ምርኮውን ማረኩ። 24በውስጣቸውም የሚቀመጥ ሕዝብ፦ ደክሜአለሁ አይልም፥ በደላቸው ይቅር ይባልላቸዋልና።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 33: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ