የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 39

39
ከባ​ቢ​ሎን የመጡ መል​እ​ክ​ተ​ኞች
1በዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ የባ​ል​ዳን ልጅ መሮ​ዳክ ባል​ዳን ሕዝ​ቅ​ያስ ታምሞ እንደ ተፈ​ወሰ ሰምቶ ነበ​ርና ደብ​ዳ​ቤና እጅ መን​ሻን፥ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ች​ንም ላከ​ለት። 2ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ስለ እነ​ርሱ እጅግ ደስ አለው፤ ግምጃ ቤቱ​ንም፥ ወር​ቁ​ንና ብሩን፥ ከር​ቤ​ው​ንና ዕጣ​ኑን፥ ዘይ​ቱ​ንም፥ መሣ​ሪ​ያም ያለ​በ​ትን ቤት ሁሉ፥ ልብ​ሱ​ንና ዕን​ቍ​ውን ሁሉ፥ በቤተ መዛ​ግ​ብ​ቱም የተ​ገ​ኘ​ውን ሁሉ አሳ​ያ​ቸው፤ በቤ​ቱና በግ​ዛቱ ሁሉ ካለው ሕዝ​ቅ​ያስ ያላ​ሳ​ያ​ቸው የለም።
3ነቢ​ዩም ኢሳ​ይ​ያስ ወደ ንጉሡ ወደ ሕዝ​ቅ​ያስ መጥቶ፥ “እነ​ዚህ ሰዎች ምን አሉ? ከወ​ዴ​ትስ መጡ?” አለው። ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “ከሩቅ ሀገር ከባ​ቢ​ሎን መጡ” አለው። 4ኢሳ​ይ​ያ​ስም፥ “በቤ​ትህ ያዩት ምን​ድን ነው?” አለው፤ ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፥ “በቤቴ ያለ​ውን ሁሉ አይ​ተ​ዋል፤ በቤቴ፥ እን​ዲ​ሁም በቤተ መዛ​ግ​ብቴ ካለው ያላ​ሳ​የ​ኋ​ቸው የለም” አለው። 5ኢሳ​ይ​ያ​ስም ሕዝ​ቅ​ያ​ስን፥ “የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ። 6እነሆ፥ በቤ​ትህ ያለው ሁሉ፥ አባ​ቶ​ች​ህም እስከ ዛሬ ድረስ ያከ​ማ​ቹት ሁሉ ወደ ባቢ​ሎን የሚ​ፈ​ል​ስ​በት ወራት ይመ​ጣል፤ ምንም አያ​ስ​ቀ​ሩ​ል​ህም፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 7ከአ​ንተ ከሚ​ወ​ጡት ከም​ት​ወ​ል​ዳ​ቸው ልጆ​ችህ ማር​ከው ይወ​ስ​ዳሉ፤ በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቤት ውስጥ ጃን​ደ​ረ​ቦ​ችና የቤት አሽ​ከ​ሮች ይሆ​ናሉ” አለው። 8ሕዝ​ቅ​ያ​ስም ኢሳ​ይ​ያ​ስን፥ “እርሱ የተ​ና​ገ​ረው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል መል​ካም ነው፤ ነገር ግን፦ በዘ​መኔ ሰላ​ምና ጽድቅ ይሁን” አለው።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ