የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 41

41
ለእ​ስ​ራ​ኤል የተ​ሰጠ ዋስ​ትና
1ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ አለ​ቆች ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት ቀር​በው ፍር​ድን ይና​ገሩ። 2ከም​ሥ​ራቅ ጽድ​ቅን ያስ​ነሣ፥ ይከ​ተ​ለ​ውም ዘንድ ወደ እግሩ የጠ​ራው ማን ነው? በአ​ሕ​ዛ​ብና በነ​ገ​ሥ​ታት ፊት ድን​ጋ​ጤን ያመ​ጣል። ጦሮ​ቻ​ቸ​ውን በም​ድር ያስ​ጥ​ላ​ቸ​ዋል፤ ቀስ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም እንደ ገለባ ይረ​ግ​ፋሉ። 3ያሳ​ድ​ዳ​ቸ​ዋ​ልም፤ እግ​ሮ​ቹም በሰ​ላም መን​ገድ ይሄ​ዳሉ። 4ይህን የሠ​ራና ያደ​ረገ፥ ትው​ል​ድ​ንም ከጥ​ንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊተ​ኛ​ውና ኋለ​ኛው እኔ ነኝ።
5አሕ​ዛብ አይ​ተው ፈሩ። የም​ድ​ርም ዳር​ቾች ቀረቡ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ቀረቡ፤ መጡም። 6ሁሉም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ይከ​ራ​ከ​ራል፤ ሁሉም እያ​ን​ዳ​ንዱ ወን​ድሙ ይረ​ዳው ነበር፤ ወን​ድ​ሙ​ንም፦ አይ​ዞህ ይለው ነበር። 7አና​ጢ​ውም አን​ጥ​ረ​ኛ​ውን፥ በመ​ዶ​ሻም የሚ​ያ​ሳ​ሳ​ውን መስፍ መች​ውን አጽ​ናና፤ ስለ ማጣ​በቅ ሥራ​ውም፥ “መል​ካም ነው” አለ፤ እን​ዳ​ይ​ን​ቀ​ሳ​ቀ​ስም በች​ን​ካር አጋ​ጠ​መው።
8ባሪ​ያዬ እስ​ራ​ኤል፥ የመ​ረ​ጥ​ሁህ ያዕ​ቆብ፥ የወ​ዳጄ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር ሆይ፥ 9አንተ ከም​ድር ዳርቻ የያ​ዝ​ሁህ፥ ከማ​ዕ​ዘ​ን​ዋም የጠ​ራ​ሁህ ነህና፦ አንተ ባሪ​ያዬ ነህ፤ መር​ጬ​ሃ​ለሁ፤ አል​ጥ​ል​ህም፤ ያል​ሁህ ሆይ፥ 10እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ። 11እነሆ፥ የሚ​ቃ​ወ​ሙህ ሁሉ ያፍ​ራሉ፤ ይዋ​ረ​ዱ​ማል፤ እን​ዳ​ል​ነ​በ​ሩም ይሆ​ናሉ፤ ጠላ​ቶ​ች​ህም ይጠ​ፋሉ። 12የሚ​ያ​ሠ​ቃ​ዩ​ህ​ንም ሰዎች ትሻ​ቸ​ዋ​ለህ፤ አታ​ገ​ኛ​ቸ​ው​ምም፤ እን​ዳ​ል​ነ​በሩ ይሆ​ና​ሉና፤ የሚ​ዋ​ጋ​ህም የለም። 13ቀኝ እጅ​ህን የያ​ዝ​ሁህ፥ እን​ዲ​ህም የም​ልህ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና። 14#ዕብ. “ትል ያዕ​ቆብ ሆይ” ይላል።ያዕ​ቆብ ሆይ፥ አት​ፍራ፤ በቍ​ጥር ጥቂት የነ​በ​ርህ እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ እኔ እረ​ዳ​ሃ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ የሚ​ቤ​ዥ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ነው። 15እነሆ፥ እንደ ተሳ​ለች እንደ አዲስ ባለ ጥርስ ማሄጃ አድ​ር​ጌ​ሃ​ለሁ፤ ተራ​ሮ​ች​ንም ታሄ​ዳ​ለህ፤ ኮረ​ብ​ቶ​ች​ንም ታደ​ቅ​ቃ​ቸ​ዋ​ለህ እንደ ገለ​ባም ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ። 16ታበ​ጥ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ፤ ነፋ​ስም ይጠ​ር​ጋ​ቸ​ዋል፤ ዐውሎ ነፋ​ስም ይበ​ት​ና​ቸ​ዋል፤ አን​ተም በእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ ደስ ይል​ሃል።
17ድሆ​ችና ምስ​ኪ​ኖች ውኃ ይሻሉ፤ አያ​ገ​ኙ​ምም፤ ምላ​ሳ​ቸ​ውም በጥ​ማት ደር​ቋል፤ እኔ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እሰ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እኔ አል​ተ​ዋ​ቸ​ውም። 18በተ​ራ​ሮች ላይ ወን​ዞ​ችን፥ በሸ​ለ​ቆ​ችም መካ​ከል ምን​ጮ​ችን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ምድረ በዳ​ውን ለውኃ መቆ​ሚያ፥ የተ​ጠ​ማ​ች​ው​ንም ምድር ለውኃ መፍ​ለ​ቂያ አደ​ር​ጋ​ለሁ። 19በም​ድረ በዳ ዝግ​ባ​ው​ንና ግራ​ሩን፥ ባር​ሰ​ነ​ቱ​ንና የዘ​ይ​ቱን ዛፍ አበ​ቅ​ላ​ለሁ፤ 20ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ይህን ሁሉ እንደ ሠራ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቅዱስ ይህን እንደ አሳየ ያውቁ ዘንድ፥ ያስ​ተ​ው​ሉም ዘንድ፥ ይረ​ዱም ዘንድ፥ ያም​ኑም ዘንድ ነው።
21ፍር​ዳ​ችሁ ቀረ​በች፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ፤ ምክ​ራ​ች​ሁም ቀረበ፥ ይላል የያ​ዕ​ቆብ ንጉሥ። 22ይምጡ፤ የሚ​ደ​ር​ስ​ባ​ች​ሁ​ንም ይን​ገ​ሩን፤ ልብም እና​ደ​ርግ ዘንድ፤ ፍጻ​ሜ​አ​ቸ​ው​ንም እና​ውቅ ዘንድ፥ የቀ​ደ​ሙት ነገ​ሮች ምን እንደ ሆኑ ንገ​ሩን፤ የሚ​መ​ጡ​ት​ንም አሳ​ዩን። 23አማ​ል​ክ​ትም መሆ​ና​ች​ሁን እና​ውቅ ዘንድ በኋላ የሚ​መ​ጡ​ትን ተና​ገሩ፤ እና​ደ​ን​ቃ​ች​ሁም ዘንድ፥ በአ​ን​ድ​ነ​ትም እናይ ዘንድ መል​ካ​ሙን ወይም ክፉ​ውን አድ​ርጉ። 24እና​ንተ ከየት ናችሁ? ከየ​ትስ ሠሯ​ችሁ? ከም​ድር የሚ​መ​ር​ጧ​ች​ሁም የረ​ከሱ አይ​ደ​ሉ​ምን?
25ከሰ​ሜ​ንና ከፀ​ሐይ መውጫ የሚ​መ​ጡ​ትን አስ​ነ​ሣሁ፤ በስ​ሜም ይጠ​ራሉ፤ አለ​ቆች ይምጡ፤ እንደ ሸክላ ሠሪ ጭቃና ጭቃን እን​ደ​ሚ​ረ​ግጥ ሸክላ ሠሪ እን​ዲሁ ይረ​ግ​ጡ​አ​ቸ​ዋል። 26እና​ውቅ ዘንድ፥ ከጥ​ንት የተ​ነ​ገ​ረው፦ እው​ነት ነው እን​ልም ዘንድ ቀድሞ የተ​ና​ገ​ረው ማን ነው? ከመ​ሆኑ በፊት የሚ​ና​ገር የለም፤ የሚ​ገ​ል​ጥም የለም፤ ቃላ​ች​ሁን የሚ​ሰማ የለም። 27በመ​ጀ​መ​ሪያ ለጽ​ዮን፦ ግዛ​ትን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ወደ መን​ገ​ድዋ እመ​ል​ሳ​ታ​ለሁ።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አጽ​ና​ና​ታ​ለሁ” ይላል። 28ከአ​ሕ​ዛ​ብና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው የሚ​ና​ገር የለ​ምና፥ ከየ​ትም እንደ ሆኑ ብጠ​ይ​ቃ​ቸው አይ​መ​ል​ሱ​ል​ኝም። 29የሚ​ሠ​ሩ​አ​ቸ​ውም በከ​ንቱ ይሠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ