ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 52

52
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እን​ደ​ታ​ደ​ጋት
1ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይ​ል​ሽን ልበሺ፤ አን​ቺም ቅድ​ስ​ቲቱ ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘና ርኩስ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያ​ል​ፍ​ምና ክብ​ር​ሽን ልበሺ። 2ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ትቢ​ያን አራ​ግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀ​መጪ፤ ምር​ኮ​ኛ​ዪቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ገ​ት​ሽን እስ​ራት ፍቺ።
3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በከ​ንቱ ተሸ​ጣ​ችሁ ነበር፤ ያለ ወር​ቅም እቤ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።” 4ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሕዝቤ አስ​ቀ​ድሞ ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም በስ​ደት ኖሩ፤ ከዚ​ያም ወደ አሦር በግድ ተወ​ሰዱ። 5ሕዝቤ በከ​ንቱ ተወ​ስ​ዶ​አ​ልና አሁን ከዚህ ምን አቆ​ማ​ችሁ?” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ታደ​ን​ቃ​ላ​ችሁ፤ ትጮ​ሃ​ላ​ች​ሁም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ስሜም በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ሁል​ጊዜ ይሰ​ደ​ባል። 6ስለ​ዚህ ሕዝቤ ስሜን ያው​ቃል፤ የም​ና​ገ​ርና ያለሁ እኔ እንደ ሆንሁ በዚያ ቀን ያው​ቃሉ።”
7ሰላ​ምን የሚ​ያ​ወራ፥ መል​ካም የም​ሥ​ራ​ች​ንም የሚ​ና​ገር፥ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም የሚ​ያ​ወራ፥ ጽዮ​ን​ንም፥ “አም​ላ​ክሽ ነግ​ሦ​አል” የሚል ሰው እግሩ በተ​ራ​ሮች ላይ እጅግ ያማረ ነው።
8እነሆ፥ የሚ​ጠ​ብ​ቁሽ ሰዎች ድምፅ ከፍ ከፍ ይላ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጽዮ​ንን ይቅር ባላት ጊዜ ዐይን በዐ​ይን ይተ​ያ​ያ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት በቃ​ላ​ቸው ደስ ይላ​ቸ​ዋል። 9የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ፍር​ስ​ራ​ሾች ደስ ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ብሎ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን አድ​ኖ​አ​ታ​ልና።#ዕብ. “ሕዝ​ቡን አጽ​ን​ት​ዋ​ልና” ይላል። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ክን​ዱን በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ፊት ገል​ጦ​አል፤ በም​ድር ዳርቻ የሚ​ኖ​ሩ​ትም ሁሉ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ማዳን ያያሉ።
11እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕቃ የም​ት​ሸ​ከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩ​ስን ነገር አት​ንኩ፤ ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ ራሳ​ች​ሁን ለዩ። 12እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ይሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና በች​ኮላ አት​ወ​ጡም፤ በመ​ኮ​ብ​ለ​ልም አት​ሄ​ዱም።
መከራ የሚ​ቀ​በ​ለው አገ​ል​ጋይ
13እነሆ፥ አገ​ል​ጋዬ ያስ​ተ​ው​ላል፤ ከፍ ከፍ ይላል፥ ይከ​ብ​ራ​ልም፤ እጅ​ግም ደስ ይለ​ዋል።#ዕብ. “እጅግ ታላቅ ይሆ​ናል” ይላል። 14ፊቱ ከሰ​ዎች ሁሉ ይልቅ፥ መል​ኩም ከሰ​ዎች ልጆች ይልቅ ያለ ክብር ነውና ብዙ ሰዎች ስለ እርሱ ያደ​ን​ቃሉ፤ 15ብዙ​ዎች አሕ​ዛብ እር​ሱን ያደ​ን​ቃሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ትም አፋ​ቸ​ውን ይዘ​ጋሉ፤ ስለ እርሱ ያል​ተ​ወ​ራ​ላ​ቸው ያው​ቁ​ታ​ልና፥ ያል​ሰ​ሙ​ትም ያስ​ተ​ው​ሉ​ታ​ልና።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ