ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 60

60
የወ​ደ​ፊቱ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ክብር
1ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ብር​ሃ​ንሽ መጥ​ቶ​አ​ልና፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ብር​ሃን በአ​ንቺ ላይ ወጥ​ቶ​አ​ልና አብሪ፤ አብሪ።#ዕብ. “ተነሺ” ይላል። 2እነሆ፥ ጨለማ ምድ​ርን፥ ድቅ​ድቅ ጨለ​ማም አሕ​ዛ​ብን ይሸ​ፍ​ናል፤ ነገር ግን በአ​ንቺ ላይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ለ​ጣል፤ ክብ​ሩም በአ​ንቺ ላይ ይታ​ያል፤ 3ነገ​ሥ​ታት በብ​ር​ሃ​ንሽ፥ አሕ​ዛ​ብም በፀ​ዳ​ልሽ ይሄ​ዳሉ።
4ዐይ​ኖ​ች​ሽን አን​ሥ​ተሽ በዙ​ሪ​ያሽ ተመ​ል​ከቺ፤ ልጆ​ች​ሽም እንደ ተሰ​በ​ሰቡ እነሆ፥ እዪ፤ ወን​ዶች ልጆ​ችሽ ከሩቅ ይመ​ጣሉ፤ ሴቶች ልጆ​ች​ሽ​ንም በጫ​ንቃ ላይ ይሸ​ከ​ሙ​አ​ቸ​ዋል። 5በዚያ ጊዜ አይ​ተሽ ትፈ​ሪ​ያ​ለሽ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብና የሀ​ገ​ሮች ብል​ጽ​ግና ወደ አንቺ ይመ​ለ​ሳ​ልና፥#ዕብ. “የባ​ሕሩ በረ​ከት ወደ አንቺ ስለ​ሚ​መ​ለስ የአ​ሕ​ዛ​ብም ብል​ጥ​ግና ወደ አንቺ ስለ​ሚ​መጣ አይ​ተሽ ደስ ይል​ሻል” ይላል። ልብሽ ይደ​ነ​ግ​ጣል። 6የግ​መ​ሎች መንጋ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ የም​ድ​ያ​ምና የኤፋ ግመ​ሎች ይሸ​ፍ​ኑ​ሻል፤ ሁሉ ከሳባ ወር​ቅ​ንና ዕጣ​ንን ይዘው ይመ​ጣሉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማዳን ያበ​ሥ​ራሉ። 7የቄ​ዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ የነ​ባ​ዮ​ትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያዬ ላይም የተ​መ​ረ​ጠው መሥ​ዋ​ዕት ይቀ​ር​ባል፤ የጸ​ሎቴ#ዕብ. “የክ​ብ​ሬ​ንም ቤት አከ​ብ​ራ​ለሁ” ይላል። ቤትም ይከ​ብ​ራል። 8እንደ ደመና፥ ከጫ​ጩ​ቶ​ችዋ ጋር ወደ መስ​ኮቷ እን​ደ​ም​ት​ገባ ርግ​ብም የሚ​በ​ርሩ እነ​ዚህ እነ​ማን ናቸው? 9ደሴ​ቶች እኔን ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ የተ​ር​ሴ​ስም መር​ከ​ቦች አስ​ቀ​ድ​መው ይመ​ጣሉ፤ ልጆ​ችሽ ስለ ከበ​ረው ስለ እስ​ራ​ኤል ቅዱስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ወር​ቅና ብር ይዘው ከሩቅ ሀገር ይመ​ጣሉ።
10በቍ​ጣዬ ቀሥፌ በይ​ቅ​ር​ታዬ አቅ​ር​ቤ​ሻ​ለ​ሁና መጻ​ተ​ኞች ቅጥ​ር​ሽን ይሠ​ራሉ፤ ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በፊ​ትሽ ይቆ​ማሉ። 11በሮ​ች​ሽም ሁል​ጊዜ ይከ​ፈ​ታሉ፤ ሰዎች የአ​ሕ​ዛ​ብን ብል​ጽ​ግና፥ የተ​ማ​ረ​ኩ​ት​ንም ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ወደ አንቺ ያመጡ ዘንድ ሌሊ​ትና ቀን አይ​ዘ​ጉም። 12ለአ​ን​ቺም የማ​ይ​ገዙ ነገ​ሥ​ታት ይሞ​ታሉ፤ እነ​ዚ​ያም አሕ​ዛብ ፈጽ​መው ይጠ​ፋሉ። 13የመ​ቅ​ደ​ሴ​ንም ስፍራ ያከ​ብሩ ዘንድ የሊ​ባ​ኖስ ክብር፥ ጥዱና አስ​ታው፥ ባር​ሰ​ነ​ቱም ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፥ 14የአ​ስ​ጨ​ና​ቂ​ዎ​ች​ሽም ልጆች እየ​ተ​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ወደ አንቺ ይመ​ጣሉ፤ የና​ቁ​ሽም ሁሉ ወደ እግ​ርሽ ጫማ ይሰ​ግ​ዳሉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተማ፥ ጽዮን ተብ​ለ​ሽም ትጠ​ሪ​ያ​ለሽ።
15የተ​ተ​ው​ሽና የተ​ጠ​ላሽ ሆነ​ሻ​ልና የሚ​ረ​ዳሽ አጣሽ፤ ነገር ግን የዘ​ለ​ዓ​ለም ደስ​ታን ለልጅ ልጅ እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ። 16የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም ወተት ትጠ​ጫ​ለሽ፤ የነ​ገ​ሥ​ታ​ት​ንም ብል​ጽ​ግና ትበ​ያ​ለሽ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ፥ መድ​ኀ​ኒ​ት​ሽና ታዳ​ጊሽ እንደ ሆንሁ ታው​ቂ​ያ​ለሽ። 17በናስ ፋንታ ወር​ቅን፥ በብ​ረ​ትም ፋንታ ብርን፥ በእ​ን​ጨ​ትም ፋንታ ናስን፥ በድ​ን​ጋ​ይም ፋንታ ብረ​ትን እሰ​ጥ​ሻ​ለሁ። ለአ​ለ​ቆ​ች​ሽም ሰላ​ምን፥ ለመ​ኳ​ን​ን​ት​ሽም ፍር​ድን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ 18እን​ግ​ዲህ በም​ድ​ርሽ ውስጥ ግፍ፥ በዳ​ር​ቻ​ሽም ውስጥ ጕስ​ቍ​ል​ናና ቅጥ​ቃጤ አይ​ሰ​ማም፤ ቅጥ​ሮ​ችሽ ድኅ​ነት ይባ​ላሉ፤ በሮ​ች​ሽም በጥ​ርብ ድን​ጋይ ይሠ​ራሉ። 19ፀሐይ በቀን የሚ​ያ​በ​ራ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ በሌ​ሊ​ትም ጨረቃ የሚ​ወ​ጣ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ ለአ​ን​ቺስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃ​ንሽ፥ አም​ላ​ክ​ሽም ክብ​ርሽ ይሆ​ናል። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃ​ንሽ ይሆ​ና​ልና፥ የል​ቅ​ሶ​ሽም ወራት ያል​ፋ​ልና፤ ፀሐ​ይሽ ከዚህ በኋላ አት​ጠ​ል​ቅም፤ ጨረ​ቃ​ሽም አይ​ቋ​ረ​ጥም። 21ሕዝ​ብሽ ሁሉ ጻድ​ቃን ይሆ​ናሉ፤ ምድ​ር​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ይወ​ር​ሳሉ፤ እር​ሱ​ንም ለማ​መ​ስ​ገን የእ​ጆ​ቹን ሥራ ይጠ​ብ​ቃሉ። 22ታናሹ ሺህ፥ የሁ​ሉም ታናሽ ታላቅ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ