ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 61:1-3

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 61:1-3 አማ2000

የጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እሰ​ብክ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀብ​ቶ​ኛ​ልና፤ ልባ​ቸው የተ​ሰ​በ​ረ​ውን እጠ​ግን ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን፥ ለታ​ሰ​ሩ​ትም መፈ​ታ​ትን፥ ለዕ​ው​ራ​ንም ማየ​ትን እና​ገር ዘንድ ልኮ​ኛል። የተ​ወ​ደ​ደ​ች​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ዓመት የተ​መ​ረ​ጠች ብዬ እጠ​ራት ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ንም የሚ​በ​ቀ​ል​በ​ትን ቀን እና​ገር ዘንድ፥ የሚ​ያ​ለ​ቅ​ሱ​ት​ንም ሁሉ አጽ​ናና ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለክ​ብሩ የተ​ከ​ላ​ቸው የጽ​ድቅ ዛፎች እን​ዲ​ባሉ ለጽ​ዮን አል​ቃ​ሾች አደ​ር​ግ​ላ​ቸው ዘንድ፥ በአ​መ​ድም ፋንታ አክ​ሊ​ልን፥ በል​ቅ​ሶም ፋንታ የደ​ስ​ታን ዘይት፥ በኀ​ዘ​ንም መን​ፈስ ፋንታ የም​ስ​ጋ​ናን መጐ​ና​ጸ​ፊያ እሰ​ጣ​ቸው ዘንድ ልኮ​ኛል።