ትንቢተ ኢሳይያስ 7
7
ለንጉሡ ለአካዝ የመጣ መልእክት
1እንዲህም ሆነ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያን ልጅ በኢዮአታም ልጅ በአካዝ ዘመን የአራም#ዕብ. “የሶርያ” ይላል። ንጉሥ ረአሶን፥ የእስራኤልም ንጉሥ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ኢየሩሳሌምን ሊወጉ ወጡ፤ ሊይዙአትም አልቻሉም። 2ለዳዊት ቤትም፥ “አራም#ዕብ. “ሶርያ” ይላል። ከኤፍሬም ጋር ተባብረዋል” የሚል ወሬ ተነገረ፤ የእርሱም ልብ የሕዝቡም ልብ የዱር ዛፍ በነፋስ እንደሚናወጥ ተናወጠ።
3እግዚአብሔርም ኢሳይያስን አለው፥ “አንተና ልጅህ ያሱብ አካዝን ትገናኙት ዘንድ በልብስ አጣቢው እርሻ መንገድ ወዳለው ወደ ላይኛው መታጠቢያ ቦታ ውጡ፤ 4እንዲህም በለው፥ “ተጠበቅ፥ ዝምም በል፤ አትፍራ፤ ከእነዚህ ከሚጤሱ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፥#ዕብ. “ከሶርያና ከረኣሶን ከሮሜልዩ ልጅ ቍጣ” የሚል ይጨምራል። የተነሣ ልብህ አይደንግጥ፤ ከተቈጣሁ በኋላ ይቅር እላለሁና።#በዕብራይስጥ የለም። 5የአራም ልጅና የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ፦#ዕብ. “ሶርያና ኤፍሬም” ይላል። ክፉ ምክርን ተማከሩብህ እንዲህ ብለው፦ 6ወደ ይሁዳ እንውጣና እንነጋገራቸው፤ ወደ እኛም እንመልሳቸው፤ የጣብኤልንም ልጅ እናንግሥባቸው፤” 7የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ይህ ምክር አይጸናምና አይሆንም። 8የአራም ራስ ደማስቆ ነው፤ የደማስቆም ራስ ረአሶን ነው፤ በስድሳ አምስት ዓመት ውስጥ የኤፍሬም መንግሥት ከሕዝብ#ዕብ. “ኤፍሬም ይሰባበራልና ሕዝብ አይሆንም” ይላል። ይጠፋል፤ 9የኤፍሬምም ራስ ሳምሮን ነው፤ የሳምሮንም#ዕብ. “ሰማርያ” ይላል። ራስ የሮሜልዩ ልጅ ፋቁሔ ነው። ባታምኑ አትጸኑም።”
የአማኑኤል የልደቱ ትንቢት
10እግዚአብሔርም ደግሞ አካዝን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 11“ከጥልቁ ወይም ከከፍታው ቢሆን ከአምላክህ ከእግዚአብሔር ምልክትን ለአንተ ለምን።” 12አካዝም፥ “አልለምንም፤ አምላኬ እግዚአብሔርንም አልፈታተንም” አለ። 13እርሱም አለ፥ “እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፤ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን? እግዚአብሔርን ታደክማላችሁ፤ 14ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። 15ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት መልካሙንም ለመምረጥ ሳያውቅ ቅቤና ማር ይበላል። 16ሕፃኑ ክፉን ለመጥላት፥ መልካሙን ለመምረጥ ሳያውቅ፥ የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት ሀገር ባድማ ትሆናለች። 17እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።”
18በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ እግዚአብሔር በግብፅ ወንዝ ዳርቻ ያለውን ዝንብ፥ በአሦርም ሀገር ያለውን ንብ በፉጨት ይጠራል። 19ይመጡማል፤ እነርሱም ሁሉ በሸለቆ፥ በመንደሮች፥ በምድር ጕድጓድ፥ በድንጋይም ዋሻ ውስጥ በጫካ ሁሉ ላይ ይሰፍራሉ።
20በዚያም ቀን እግዚአብሔር ከወንዙ ማዶ ባመጣው ታላቅ ምላጭ በአሦር ንጉሥ የራሱንና የእግሩን ጠጕር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይላጫል።
21በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ሰው ከላሞቹ አንዲት ጊደርንና ሁለት በጎችን ያሳድጋል፤ የአንዲት በግ ወተትም ሁለት ሰዎችን ያጠግባል። 22ወተትም ይበዛል፤ በሀገሪቱ መካከል የቀረ ሁሉ ቅቤና ማር ይበላል።
23በዚያም ወራት እንዲህ ይሆናል፤ ወይን በሀገሩ ሁሉ የበጀ ይሆናል፤ የአንድ ሺህ የወይን ዳስ ዋጋ አንድ ሺህ የብር ሰቅል ይሆናል። ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤#“ዳግመኛ ምድር ሁሉ ትጠፋለች” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። እሾህንና ኵርንችትንም ትሞላለች፤ ፍርሀትም ይመጣል።#ምዕ. 7 ቍ. 23 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 24በፍላጻና በቀስት ይገቡባታል፤ ምድሪቱ ሁሉ ትጠፋለችና፥ እሾህንና ኵርንችትንም ትሞላለችና። 25በሚታረሰውም ተራራ ሁሉ ላይ ፍርሀት ይመጣል፤ የበጎች መሰማርያ ይሆናል፤ በሬዎችም ይረግጡታል፤ እሾህና ኵርንችትም ያጠፋዋል።#ምዕ. 7 ቍ. 25 በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 7: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapistaging.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ