የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 1

1
የይ​ሁ​ዳና የስ​ም​ዖን ነገድ አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅን እንደ ማረኩ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ኢያሱ ከሞተ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች፥ “ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን የሚ​ወ​ጋ​ልን ማን አለቃ ይወ​ጣ​ል​ናል?” ብለው ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠየቁ። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይሁዳ ይውጣ፤ እነሆ፥ ምድ​ሪ​ቱን በእጁ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ታ​ለሁ” አለ። 3ይሁ​ዳም ወን​ድ​ሙን ስም​ዖ​ንን፥ “ከእኔ ጋር ወደ ዕጣዬ ውጣ፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም እን​ው​ጋ​ቸው፤ እኔም ደግሞ ከአ​ንተ ጋር ወደ ዕጣህ እሄ​ዳ​ለሁ” አለው። ስም​ዖ​ንም ከእ​ርሱ ጋር ሄደ። 4ይሁ​ዳም ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንና ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን በእጁ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም በቤ​ዜቅ ውስጥ ዐሥር ሺህ ሰዎ​ችን ገደ​ለ​ባ​ቸው። 5አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅ​ንም በቤ​ዜቅ አገ​ኙ​ትና ተዋ​ጉት፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንና ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው። 6አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም ሸሸ፤ ተከ​ታ​ት​ለ​ውም ያዙት፤ የእ​ጁ​ንና የእ​ግ​ሩ​ንም አውራ ጣቶች ቈረጡ። 7አዶ​ኒ​ቤ​ዜ​ቅም፥ “የእ​ጆ​ቻ​ቸ​ውና የእ​ግ​ሮ​ቻ​ቸው አውራ ጣቶች የተ​ቈ​ረጡ ሰባ ነገ​ሥ​ታት ከገ​በ​ታዬ በታች ፍር​ፋሪ ይለ​ቅሙ ነበሩ፤ እኔ እን​ዳ​ደ​ረ​ግሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲሁ መለ​ሰ​ልኝ” አለ። ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ወሰ​ዱት፥ በዚ​ያም ሞተ።
ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ኬብ​ሮን በይ​ሁዳ ነገድ እንደ ተያዙ
8የይ​ሁ​ዳም ልጆች ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ተዋ​ግ​ተው ያዙ​አት፤ በሰ​ይፍ ስለ​ትም መቱ​አት፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በእ​ሳት አቃ​ጠ​ሉ​አት። 9ከዚ​ያም በኋላ የይ​ሁዳ ልጆች በተ​ራ​ራ​ማው ሀገ​ርና በደ​ቡብ በኩል በቈ​ላው ውስጥ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ሊወጉ ወረዱ። 10ይሁ​ዳም በኬ​ብ​ሮን ወደ​ሚ​ኖሩ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን ሄደ። የኬ​ብ​ሮ​ንም ሰዎች ወጥ​ተው ተቀ​በ​ሉት፤ የኬ​ብ​ሮ​ንም ስም አስ​ቀ​ድሞ ቂር​ያ​ታ​ር​ቦ​ቅ​ሴ​ፌር ነበረ። የኤ​ና​ቅ​ንም ትው​ልድ ሴሲ​ንና አኪ​ማ​ምን፥ ተለ​ሜ​ን​ንም ገደ​ሉ​አ​ቸው።
ጎቶ​ን​ያል ዳቤ​ርን መያዙ
(ኢያ. 15፥13-19)
11ከዚ​ያም ወደ ዳቤር ሰዎች ሄዱ፤ አስ​ቀ​ድ​ሞም የዳ​ቤር ስም ሀገረ መጻ​ሕ​ፍት ነበረ። 12ካሌ​ብም፥ “ሀገረ መጻ​ሕ​ፍ​ትን ለሚ​መ​ታና ለሚ​ይዝ ልጄን ዓስ​ካን ሚስት ትሆ​ነው ዘንድ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ” አለ። 13የካ​ሌ​ብም ትንሽ ወን​ድም የቄ​ኔዝ ልጅ ጎቶ​ን​ያል ያዛት፤ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ ልጁን ዓስ​ካን ሰጠው። 14እር​ስ​ዋም ወደ እርሱ በመ​ጣች ጊዜ የእ​ርሻ ቦታ ይሰ​ጣት ዘንድ አባ​ቷን እን​ድ​ት​ለ​ም​ነው ጎቶ​ን​ያል መከ​ራት። እር​ስ​ዋም በአ​ህ​ያዋ ላይ ሆና አን​ጐ​ራ​ጐ​ረች፤ “ወደ ደቡብ ሰድ​ደ​ኸ​ኛል” ብላም ጮኸች። ካሌ​ብም፥ “ምን ሆነ​ሻል?” አላት። 15ዓስ​ካም፥ “በረ​ከ​ትን ስጠኝ፤ ወደ ደቡብ በረሃ ሰድ​ደ​ኸ​ኛ​ልና ውኃ የማ​ጣ​ቴን ዋጋ ደግሞ ስጠኝ”#ዕብ. “የውኃ ምንጭ ስጠኝ” ይላል። አለ​ችው። ካሌ​ብም በል​ብዋ እንደ ተመ​ኘ​ችው የመ​ከ​ራ​ዋ​ንና የኀ​ዘ​ኗን ዋጋ ሰጣት።#ዕብ. “ላይ​ኛ​ው​ንና ታች​ኛ​ውን ምን​ጮች ሰጣት” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “የላ​ይ​ኛ​ው​ንና የታ​ች​ኛ​ውን ምን​ጮች ዋጋ ሰጣት” ይላል።
የይ​ሁ​ዳና የብ​ን​ያም ነገድ ድል እንደ ተቀ​ዳጁ
16የቄ​ና​ዊው የሙሴ አማት የዮ​ባብ ልጆ​ችም ከዘ​ን​ባባ ከተማ ተነ​ሥ​ተው ከዓ​ራድ በአ​ዜብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕ​ዝቡ ጋር ተቀ​መጡ። 17ይሁ​ዳም ከወ​ን​ድሙ ከስ​ም​ዖን ጋር ሄደ፤ በሴ​ፌት የተ​ቀ​መ​ጡ​ት​ንም ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን መቱ፤ ፈጽ​መ​ውም አጠ​ፉ​አት፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ስም ሕርም ብለው ጠሩ​አት። 18ይሁ​ዳም ጋዛ​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አስ​ቀ​ሎ​ና​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አቃ​ሮ​ን​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን፥ አዛ​ጦ​ን​ንና አው​ራ​ጃ​ዋን አል​ወ​ረ​ሳ​ትም።#ዕብ. “ያዘ” ይላል። 19እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከይ​ሁዳ ጋር ነበረ፤ ይሁ​ዳም ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር ወረሰ፤ በሸ​ለ​ቆው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ግን የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ነበ​ሩ​አ​ቸ​ውና ሊወ​ር​ሳ​ቸው አል​ቻ​ለም። 20ሙሴም እንደ ተና​ገረ ለካ​ሌብ ኬብ​ሮ​ንን ሰጡት፤ ከዚ​ያም ሠላሳ ከተ​ሞ​ችን ወረሰ፤ ከዚ​ያም ሦስ​ቱን የዔ​ናቅ ልጆች አስ​ወ​ገ​ዳ​ቸው። 21ነገር ግን በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን የብ​ን​ያም ልጆች አላ​ወ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ከብ​ን​ያም ልጆች ጋር እስከ ዛሬ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ተቀ​ም​ጠ​ዋል።
ቤቴል በኤ​ፍ​ሬ​ምና በም​ናሴ መያ​ዝዋ
22የዮ​ሴ​ፍም ልጆች ደግሞ ወደ ቤቴል ወጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ነበረ። 23እነ​ር​ሱም ሰፍ​ረው ቤቴ​ልን ሰለ​ሉ​አት። አስ​ቀ​ድ​ሞም የዚ​ያች ከተማ ስም ሎዛ ይባል ነበር። 24ጠባ​ቂ​ዎ​ቹም አንድ ሰው ከከ​ተማ ሲወጣ አይ​ተው ያዙ​ትና፥ “የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱን መግ​ቢያ አሳ​የን፤ እኛም ምሕ​ረት እና​ደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለን” አሉት። 25የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም መግ​ቢያ አሳ​ያ​ቸው፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አት፤ ያን ሰውና ዘመ​ዶ​ቹን ግን ለቀ​ቁ​አ​ቸው። 26ሰው​የ​ውም ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን ምድር ሄደ፤ በዚ​ያም ከተ​ማን ሠራ፤ ስም​ዋ​ንም ሎዛ ብሎ ጠራት። እስከ ዛሬም ድረስ ስምዋ ያው ነው።
እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ያላ​ባ​ረ​ሩት ሕዝብ
27ምና​ሴም የሰ​ቂ​ቶን ከተማ ቤት​ሶ​ን​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንም፥ ኢቀ​ጸ​አ​ድ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የዶ​ርን ነዋ​ሪ​ዎ​ችና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የዮ​በ​ለ​ዓ​ምን ነዋ​ሪ​ዎች፥ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን፥ የመ​ጊ​ዶን ነዋ​ሪ​ዎች መሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ች​ዋ​ንና መን​ደ​ሮ​ች​ዋን አል​ወ​ረ​ሳ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በዚ​ያች ሀገር ይቀ​መጡ ዘንድ ጸኑ። 28እስ​ራ​ኤ​ልም በበ​ረቱ ጊዜ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን ገባ​ሮች አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው፤ ነገር ግን ፈጽ​መው አላ​ጠ​ፏ​ቸ​ውም።
29ኤፍ​ሬ​ምም በጋ​ዜር የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንን አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው በጋ​ዜር ተቀ​መጡ፤ ገባ​ሮ​ችም ሆኑ​ላ​ቸው።
30ዛብ​ሎ​ንም በቄ​ድ​ሮ​ንና በአ​ማን የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሰዎች አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ከነ​ዓ​ና​ው​ያን በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተቀ​መጡ፤ ግብ​ርም የሚ​ገ​ብ​ሩ​ላ​ቸው ሆኑ።
31አሴ​ርም የዓኮ ነዋ​ሪ​ዎ​ችን አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ ነገር ግን ገባ​ሮች ሆኑ​ላ​ቸው፤ የዶር ነዋ​ሪ​ዎ​ች​ንና የሲ​ዶን ነዋ​ሪ​ዎ​ችን፥ የደ​ላ​ፍ​ንም ነዋ​ሪ​ዎች፥ የአ​ክ​ሶ​ዚ​ብ​ንና የሄ​ል​ባን፥ የአ​ፌ​ቅ​ንና የረ​ዓ​ብ​ንም ሰዎች አላ​ጠ​ፉ​አ​ቸ​ውም። 32አሴ​ርም በዚ​ያች ምድር በተ​ቀ​መ​ጡት ከነ​ዓ​ና​ው​ያን መካ​ከል ተቀ​መጠ፤ ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው አል​ቻ​ለ​ምና።
33ንፍ​ታ​ሌ​ምም የቤ​ት​ሳ​ሚ​ስ​ንና የቤ​ቴ​ኔ​ስን ሰዎች አላ​ጠ​ፋ​ቸ​ውም፤ በም​ድ​ሩም በተ​ቀ​መ​ጡት በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያን መካ​ከል ተቀ​መጡ፤ ነገር ግን በቤ​ት​ሳ​ሚ​ስና በቤ​ቴ​ኔስ የሚ​ኖሩ ሰዎች ገባ​ሮች ሁኑ​ላ​ቸው።
34አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም የዳ​ንን ልጆች በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር አስ​ጨ​ነ​ቁ​አ​ቸው፤ ወደ ሸለ​ቆው እን​ዲ​ወ​ርዱ አይ​ፈ​ቅ​ዱ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና። 35አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ድብና ቀበ​ሮ​ዎች በሚ​ኖ​ሩ​በት በመ​ር​ስ​ኖ​ኖስ ተራራ መቀ​መጥ ጀመሩ፤ ነገር ግን የዮ​ሴፍ ወገን እጅ በአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ላይ ጸናች፤ ገባ​ርም አደ​ረ​ጉ​አ​ቸው። 36የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ንም ድን​በር ከአ​ቅ​ራ​ቢም ዐቀ​በት ከጭ​ን​ጫው ጀምሮ እስከ ላይ​ኛው ድረስ ነበረ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ