መጽሐፈ መሳፍንት 11
11
ዮፍታሔ
1ገለዓዳዊዉም ዮፍታሔ ጽኑዕ ኀያል ሰው የጋለሞታ ሴትም ልጅ ነበረ። ለገለዓድም ዮፍታሔን ወለደችለት። 2የገለዓድም ሚስት ወንዶች ልጆችን ወለደችለት፤ ልጆችዋም ባደጉ ጊዜ ዮፍታሔን፥ “የሌላ ሴት ልጅ ነህና በአባታችን ቤት አትወርስም” ብለው አስወጡት። 3ዮፍታሔም ከወንድሞቹ ፊት ሸሽቶ በጦብ ምድር ተቀመጠ፤ ድሆች ሰዎችም ተሰብስበው ዮፍታሔን ተከተሉት።
4ከዚያም ወራት በኋላ የአሞን ልጆች እስራኤልን ተዋጉአቸው። 5የገለዓድ ሽማግሌዎችም ዮፍታሔን ከጦብ ምድር ለማምጣት ሄዱ። 6ዮፍታሔንም፥ “ና፥ ከአሞን ልጆች ጋር እንድንዋጋ መስፍን ሁነን” አሉት። 7ዮፍታሔም የገለዓድን ሽማግሌዎች፥ “የጠላችሁኝ፥ ከአባቴም ቤት ያስወጣችሁኝ እናንተ አይደላችሁምን? አሁን በተጨነቃችሁ ጊዜ ለምን ወደ እኔ መጣችሁ?” አላቸው። 8የገለዓድም ሽማግሌዎች ዮፍታሔን፥ “እንዲህ አይደለም፤ ከእኛ ጋር እንድትወጣ፥ ከአሞንም ልጆች ጋር እንድቷጋ፥ ስለዚህ አሁን ወደ አንተ ተመልሰን መጣን፤ በገለዓድም ሰዎች ሁሉ ላይ አለቃችን ትሆናለህ” አሉት። 9ዮፍታሔም የገለዓድን ሽማግሌዎች፥ “ከአሞን ልጆች ጋር ለመዋጋት ብትወስዱኝ፥ እግዚአብሔርም በእጄ አሳልፎ ቢሰጣቸው፥ እኔ አለቃችሁ እሆናለሁን?” አላቸው። 10የገለዓድም ሽማግሌዎች ዮፍታሔን፥ “እግዚአብሔር በመካከላችን ምስክር ይሁን፤ በርግጥ እንደ ቃልህ እናደርጋለን” አሉት። 11ዮፍታሔም ከገለዓድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም መስፍን ይሆናቸው ዘንድ በላያቸው አለቃ አድርገው ሾሙት፤ ዮፍታሔም ቃሉን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በመሴፋ ተናገረ።
12ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ፥ “ሀገሬን ለመውጋት ወደ እኔ የምትመጣ አንተ ከእኔ ጋር ምን አለህ?” ብሎ መልእክተኞችን ላከ። 13የአሞንም ልጆች ንጉሥ የዮፍታሔን መልእክተኞች፥ “እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ስለ ወሰደ ነው፤ አሁንም በሰላም መልሱልኝ” ብሎ መለሰላቸው። 14ዮፍታሔም የላካቸው ወደ ዮፍታሔ ተመለሱ፤ ዮፍታሔም ወደ አሞን ልጆች ንጉሥ መልእክተኞችን እንደ ገና ላከ፤ እንዲህም አለው፦ 15ዮፍታሔ እንዲህ ይላል፥ “እስራኤል ከግብፅ በወጡ ጊዜ የሞዓብን ምድር፥ የአሞንንም ልጆች ምድር አልወሰዱም፤ 16ነገር ግን እስራኤል በምድረ በዳ እስከ ኤርትራ ባሕር ሄዱ፤ ወደ ቃዴስም ደረሱ፤ 17እስራኤል ወደ ኤዶምያስ ንጉሥ፦ ‘በምድርህ እንዳልፍ፥ እባክህ፥ ፍቀድልኝ’ ብሎ መልእክተኞችን ላከ፤ የኤዶምያስም ንጉሥ እንቢ አለ። እንዲሁም ወደ ሞዓብ ንጉሥ ላከ፤ እርሱም እንቢ አለ። 18እስራኤልም በቃዴስ ተቀመጠ። በምድረ በዳም በኩል አለፈ፤ የኤዶምያስንና የሞዓብንም ምድር ዞሩ፤ ከሞዓብ ምድርም በምሥራቅ በኩል መጡ፤ በአርኖንም ማዶ ሰፈሩ፤ አርኖንም የሞዓብ ድንበር ነበረና ወደ ሞዓብ ድንበር አልገቡም። 19እስራኤልም ወደ አሞራዊው ወደ ሐሴቦን ንጉሥ ወደ ሴዎን መልእክተኞችን ላከ፤ እስራኤልም፦ ‘በምድርህ በኩል ወደ ስፍራችን፥ እባክህ፥ አሳልፈን’ አለው። 20ሴዎንም እስራኤል በድንበሩ እንዲያልፍ እንቢ አለ፤ ነገር ግን ሴዎን ሕዝቡን ሁሉ ሰበሰበ፤ በኢያሴርም ሰፈረ፤ ከእስራኤልም ጋር ተዋጋ። 21የእስራኤልም አምላክ እግዚአብሔር ሴዎንንና ሕዝቡን ሁሉ በእስራኤል እጅ አሳልፎ ሰጠ፤ ገደሉአቸውም፤ እስራኤልም በዚያ ምድር ተቀምጠው የነበሩትን የአሞሬዎናውያንን ምድር ሁሉ ወረሱ። 22ከአርኖንም እስከ ያቦቅ ድረስ፥ ከምድረ በዳውም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ የአሞሬዎናውያንን አውራጃ ሁሉ ወረሱ። 23አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ከእስራኤል ፊት አሞሬዎናውያንን አስወገደ፤ አንተም በተራህ ትወርሳለህን? 24አምላክህ ኮሞስ የሚሰጥህን የምትወርስ አይደለህምን? እኛም አምላካችን እግዚአብሔር ከፊታችን ያስወጣቸውን የእነርሱን ምድር የምንወርስ አይደለንምን? 25ወይስ ዛሬ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ አንተ ትሻላለህን? ወይስ እርሱ ከእስራኤል ጋር ተጣላን? ወይስ ተዋጋውን? 26እስራኤልም በሐሴቦንና በመንደሮችዋ፥ በአሮዔርና በመንደሮችዋ፥ በአርኖንም አቅራቢያ ባሉት ከተሞች ሁሉ ሦስት መቶ ዓመት ተቀምጦ በነበረ ጊዜ፥ በዚያ ዘመን ስለ ምን አላዳንሃቸውም ነበር? 27እኔ አልበደልሁህም፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ትዋጋ ዘንድ ክፉ አታድርግብኝ፤ ፈራጁ እግዚአብሔር በእስራኤል ልጆችና በአሞን ልጆች መካከል ዛሬ ይፍረድ።” 28ነገር ግን ዮፍታሔ የላከበትን ቃል የአሞን ልጆች ንጉሥ አልሰማም፤ እንቢም አላቸው።
29የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፤ እርሱም የምናሴ ዕጣ ከምትሆን ከገለዓድ ምድርና ከገለዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻገረ። 30ዮፍታሔም፥ “በእውነት የአሞንን ልጆች በእጄ አሳልፈህ ብትሰጠኝ፥ 31ከአሞን ልጆች ዘንድ በደኅና በተመለስሁ ጊዜ፥ ከቤቴ ደጅ ወጥቶ የሚቀበለኝን ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አደርገዋለሁ” ብሎ ለእግዚአብሔር ስእለት ተሳለ። 32ዮፍታሔም ሊዋጋቸው ወደ አሞን ልጆች ተሻገረ፤ እግዚአብሔርም በእጁ አሳልፎ ሰጣቸው። 33ከአሮዔርም እስከ ሚኒትና እስከ አቤልክራሚም ድረስ ሃያ ከተሞችን በታላቅ ሰልፍ አጠፋቸው። የአሞንም ልጆች በእስራኤል ልጆች ፊት ተዋረዱ።
ስለ ዮፍታሔ ሴት ልጅ
34ዮፍታሔም ወደ መሴፋ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ እነሆም፥ ልጁ ከበሮ ይዛ እየዘፈነች ልትቀበለው ወጣች፤ ለእርሱም የሚወድዳት አንዲት ብቻ ነበረች። ከእርስዋም በቀር ወንድ ወይም ሴት ሌላ ልጅ አልነበረውም። 35እርስዋንም ባየ ጊዜ ልብሱን ቀድዶ፥ “ወዮልኝ ልጄ ሆይ! ወደ እግዚአብሔር አፌን ከፍቻለሁና፥ ከዚያውም እመለስ ዘንድ አልችልምና አሰናከልሽኝ፤ አስጨነቅሽኝም” አላት። 36እርስዋም፥ “አባቴ ሆይ፥ አፍህን ወደ እግዚአብሔር ከከፈትህ፥ እግዚአብሔር በጠላቶችህ በአሞን ልጆች ላይ ተበቅሎልሃልና በአፍህ እንደ ተናገርህ አድርግብኝ” አለችው። 37አባቷንም፥ “ይህ ነገር ይደረግልኝ፤ ከዚህ ሄጄ በተራሮች ላይ እንድወጣና እንድወርድ፥ ከባልንጀሮቼም ጋር ለድንግልናዬ እንዳለቅስ ሁለት ወር አሰናብተኝ” አለችው። 38እርሱም፥ “ሂጂ” አለ። ሁለት ወርም አሰናበታት፤ ከባልንጀሮችዋም ጋር ሄደች፤ በተራሮችም ላይ ለድንግልናዋ አለቀሰች። 39ሁለት ወርም ከተፈጸመ በኋላ ወደ አባቷ ተመለሰች፤ ዮፍታሔም የተሳለውን ስእለት አደረገ፤ እርስዋም ወንድ አላወቀችም ነበር። 40የእስራኤልም ሴቶች ልጆች ለገለዓዳዊዉ ለዮፍታሔ ልጅ በዓመት አራት ቀን ያለቅሱላት ዘንድ በዓመት በዓመት ይሄዱ ነበር። ይህችም በእስራኤል ዘንድ ሥርዐት ሆነች።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 11: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ