መጽሐፈ መሳፍንት 3
3
ሳይባረሩ በምድሪቱ ስለ ቀሩት ሕዝብ
1የከነዓናውያንንም ጦርነት ሁሉ ያላወቁትን እስራኤልን በእነርሱ ይፈትናቸው ዘንድ እግዚአብሔር እነዚህን አሕዛብ ተዋቸው። 2ይህም ጦርነትን ያስተምሩአቸው ዘንድ ስለ እስራኤል ልጆች ትውልድ ብቻ ነው፤ ነገር ግን ከእነርሱ በፊት የነበሩት እነዚህን አላወቋቸውም ነበር፤ 3እነርሱም አምስቱ የፍልስጥኤማውያን መኳንንት፥ ከነዓናውያንም ሁሉ ፥ ሲዶናውያንም፥ ከበዓልሄርሞን ተራራ ጀምሮ እስከ ኤማት መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ተራራ የሚኖሩትም ኤዌዎናውያን፤ 4እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ለአባቶቻቸው ያዘዘውን ትእዛዝ መስማታቸው እንዲታወቅ እስራኤል ይፈተኑባቸው ዘንድ እነዚህ ቀሩ። 5የእስራኤልም ልጆች በከነዓናውያን፥ በኬጤዎናውያን፥ በአሞሬዎናውያን፥ በፌርዜዎናውያን፥ በኤዌዎናውያን፥ በኢያቡሴዎናውያንም መካከል ተቀመጡ። 6ሴቶች ልጆቻቸውንም አገቡአቸው፤ እነርሱም ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንዶች ልጆቻቸው ሰጡ፤ አማልክቶቻቸውንም አመለኩ።
ጎቶንያል
7የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረጉ፤ አምላካቸውንም እግዚአብሔርን ረስተው በዓሊምንና አስታሮትን አመለኩ። 8ስለዚህ እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ በወንዞችም መካከል ባለች በሶርያ ንጉሥ በኩሳርሳቴም እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ የእስራኤልም ልጆች ለኩሳርሳቴም ስምንት ዓመት ተገዙለት። 9የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ። እግዚአብሔርም ለእስራኤል መድኀኒትን አስነሣላቸው። የካሌብ የታናሽ ወንድሙ የቄኔዝ ልጅ ጎቶንያልም አዳናቸው፤ ለእርሱም ታዘዙለት። 10የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ በእስራኤልም ላይ ይፈርድ ነበር፤ ለጦርነትም ወጣ፤ እግዚአብሔርም በወንዞች መካከል ያለች የሶርያ ንጉሥ ኩሳርሳቴምን በእጁ አሳልፎ ሰጠው፤ እጁም በኩሳርሳቴም ላይ በረታች። 11ምድሪቱም አርባ ዓመት ዐረፈች፤ የቄኔዝም ልጅ ጎቶንያል ሞተ።
ናዖድ
12የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ክፉ ስለ ሠሩ እግዚአብሔር የሞዓብን ንጉሥ ዔግሎምን በእስራኤል ላይ አበረታባቸው። 13የአሞንን ልጆችና አማሌቅን ወደ እርሱ ሰበሰበ፤ ሄዶም እስራኤልን መታ፤ ዘንባባ ያለባትንም ከተማ ያዘ። 14የእስራኤልም ልጆች ለሞዓብ ንጉሥ ለዔግሎም ዐሥራ ስምንት ዓመት ተገዙ።
15የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ እግዚአብሔርም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ናዖድን#ዕብ. “ኤሁድ” ሲል ግሪክ ሰባ. ሊ. “አወድ” ይለዋል። ሁለቱ እጆቹ ቀኝ የሆኑለትን ሰው አዳኝ አስነሣላቸው፤ የእስራኤልም ልጆች በእርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎም እጅ መንሻ ላኩ። 16ናዖድም ሁለት አፍ ያላት ርዝመቷ አንድ ስንዝር የሆነች ሰይፍ አበጀ፤ ከልብሱም በታች በቀኝ በኩል በወገቡ ታጠቃት። 17ለሞዓብም ንጉሥ ለዔግሎም እጅ መንሻውን አቀረበ፤ ዔግሎምም እጅግ ወፍራም ሰው ነበረ። 18እጅ መንሻውንም ማቅረብ በጨረሰ ጊዜ፥ እጅ መንሻ የተሸከሙትን ሰዎች አሰናበታቸው። 19ዔግሎምም ከገልገል ከጣዖታቱ ቤት ተመለሰ። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ፥ ለብቻህ የምነግርህ የምሥጢር ነገር አለኝ” አለ፤ ዔግሎምም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ እንዲወጣ አዘዘ፤ በእርሱም ዘንድ የቆሙት ሁሉ ወጡ ። 20ናዖድም ወደ እርሱ ገባ፤ እርሱም በበጋ ቤቱ ሰገነት ለብቻው ተቀምጦ ነበር። ናዖድም፥ “ንጉሥ ሆይ! የእግዚአብሔር መልእክት ለአንተ አለኝ” አለው። ዔግሎምም ከዙፋኑ ተነሣ፥ ቀረበውም። 21ናዖድም በተነሣ ጊዜ ግራ እጁን ዘርግቶ ከቀኝ ጎኑ ሰይፉን መዘዘ፤ ዔግሎምንም ሆዱን ወጋው፤ 22እስከ ውላጋዋም አስገባት፤ እስከ ጀርባውም በረበረው፥ ሰይፉንም ከሆዱ መልሶ አላወጣትም። 23ናዖድም የእልፍኙን ደጅ ዘግቶና ቈልፎ ወደ ውጭ ወጣ።
24ናዖድም ከሄደ በኋላ አገልጋዮቹ መጡ፤ የሰገነቱም ደጅ ተቈልፎ ባዩ ጊዜ፥ “ምናልባት በበጋ ሰገነቱ ውስጥ ወገቡን ይሞክር ይሆናል” አሉ። 25እስኪያፍሩም ድረስ ቈዩ፤ የሰገነቱንም ደጅ እንዳልከፈተ ባዩ ጊዜ መክፈቻውን ወስደው ከፈቱ፤ እነሆም፥ ጌታቸው በምድር ላይ ወድቆ ሞቶም አገኙት።
26እስከሚታወኩም ድረስ ናዖድ አመለጠ፤ ያወቀውም የለም፤ ከጣዖቶቻቸውም አልፎ ወደ ሴይሮታ አመለጠ። 27ከዚህም በኋላ ወደ እስራኤል ምድር በደረሰ ጊዜ በተራራማው በኤፍራም ሀገር ቀንደ መለከት ነፋ፤ የእስራኤልም ልጆች ከእርሱ ጋር ከተራራማው ሀገር ወረዱ፤ እርሱም በፊታቸው ሄደ። 28እርሱም፥ “እግዚአብሔር አምላክ ጠላቶቻችንን ሞዓባውያንን በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናልና ተከተሉኝ” አላቸው። ተከትለውትም ወረዱ፤ ወደ ሞዓብም የሚያሻግረውን የዮርዳኖስን መሻገርያ ያዙ፤ ማንም ሰው እንዲያልፍ አልፈቀዱም። 29በዚያም ወራት ከሞዓብ ዐሥር ሺህ የሚያህሉትን፥ ጐልማሶችና ጽኑዓን ሁሉ ገደሉ፤ ከእነርሱም አንድ ሰው እንኳ አላመለጠም። 30በዚያም ወራት ሞዓባውያን በእስራኤል እጅ ገቡ፤ ምድሪቱም ሰማንያ ዓመት ዐረፈች። ናዖድም እስኪሞት ድረስ ገዛቸው።
ሴሜጋር
31ከእርሱም በኋላ የሐናት ልጅ ሴሜጋር ተነሣ፤ ከፍልስጥኤማውያንም ስድስት መቶ ሰው በበሬ መውጊያ ገደለ፤ እርሱም ደግሞ እስራኤልን አዳነ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 3: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ