የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 4

4
ዲቦ​ራና ባርቅ
1የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እንደ ገና ክፉ ሥራ ሠሩ፤ ናዖድ ግን ሞቶ ነበር። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በአ​ሦር በነ​ገ​ሠው በከ​ነ​ዓን ንጉሥ በኢ​ያ​ቢን እጅ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ የሠ​ራ​ዊ​ቱም አለቃ ሲሣራ ነበረ፤ እር​ሱም በአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ይቀ​መጥ ነበረ። 3የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች ነበ​ሩ​ትና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ሃያ ዓመት እጅግ ያስ​ጨ​ን​ቃ​ቸው ነበር።
4በዚ​ያም ወራት ነቢ​ይቱ የለ​ፊ​ዶት ሚስት ዲቦራ እስ​ራ​ኤ​ልን ትገ​ዛ​ቸው ነበ​ረች። 5እር​ስ​ዋም በኤ​ፍ​ሬም ተራራ በቤ​ቴ​ልና በኢ​ያማ መካ​ከል “የዲ​ቦራ ዘን​ባባ” ተብሎ በሚ​ጠ​ራው ዛፍ ሥር ተቀ​ምጣ ነበር፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ወደ እር​ስዋ ለፍ​ርድ ይወጡ ነበር። 6ዲቦ​ራም ልካ ከቃ​ዴስ ንፍ​ታ​ሌም የአ​ቢኒ​ሔ​ምን ልጅ ባር​ቅን ጠርታ እን​ዲህ አለ​ችው፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ብሎ ያዘ​ዘህ አይ​ደ​ለ​ምን? ሄደህ ወደ ታቦር ተራራ ውጣ፤ ከአ​ን​ተም ጋር ከን​ፍ​ታ​ሌ​ምና ከዛ​ብ​ሎን ልጆች ዐሥር ሺህ ሰዎች ውሰድ፤ 7እኔም የኢ​ያ​ቢ​ንን ሠራ​ዊት አለቃ ሲሣ​ራን፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም፥ ሕዝ​ቡ​ንም ሁሉ ወደ አንተ ወደ ቂሶን ወንዝ እስ​ባ​ለሁ፤ በእ​ጅ​ህም አሳ​ልፌ እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ።” 8ባር​ቅም፥ “አንቺ ከእኔ ጋር ብት​ሄጂ እኔ እሄ​ዳ​ለሁ፤ አንቺ ግን ከእኔ ጋር ባት​ሄጂ እኔ አል​ሄ​ድም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አ​ኩን ከእኔ ጋር የሚ​ል​ክ​በ​ትን ዕለት አላ​ው​ቃ​ት​ምና” አላት። 9ዲቦ​ራም፥ “በእ​ው​ነት ከአ​ንተ ጋር እሄ​ዳ​ለሁ፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲሣ​ራን በሴት እጅ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና በዚህ በም​ት​ሄ​ድ​በት መን​ገድ ለአ​ንተ ክብር አይ​ሆ​ንም” አለ​ችው። ዲቦ​ራም ተነ​ሥታ ከባ​ርቅ ጋር ወደ ቃዴስ ሄደች። 10ባር​ቅም ዛብ​ሎ​ን​ንና ንፍ​ታ​ሌ​ምን ወደ ቃዴስ ጠራ​ቸው፤ ዐሥር ሺህም ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ወጡ፤ ዲቦ​ራም ከእ​ርሱ ጋር ወጣች።
11ቄና​ዊ​ውም ሔቤር ከሙሴ አማት ከኢ​ዮ​ባብ ልጆች ከቄ​ና​ው​ያን ተለ​ይቶ ድን​ኳ​ኑን በቃ​ዴስ አጠ​ገብ እስከ ነበ​ረው ታላቅ ዛፍ ድረስ ተከለ።
12የአ​ቢ​ኒ​ሔ​ምም ልጅ ባርቅ ወደ ታቦር ተራራ እንደ ወጣ ለሲ​ሣራ ነገ​ሩት። 13ሲሣ​ራም ሰረ​ገ​ሎ​ቹን ሁሉ፥ ዘጠኝ መቶ የብ​ረት ሰረ​ገ​ሎች፥ ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በ​ሩ​ትን ሕዝ​ቡን ሁሉ ከአ​ሕ​ዛብ አሪ​ሶት ወደ ቂሶን ወንዝ ሰበ​ሰ​ባ​ቸው። 14ዲቦ​ራም ባር​ቅን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሲሣ​ራን በእ​ጅህ አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጥ​በት ቀን ዛሬ ነውና ተነሣ፤ እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ ይሄ​ዳል” አለ​ችው። ባር​ቅም ዐሥር ሺህ ሰዎች ተከ​ት​ለ​ውት ከታ​ቦር ተራራ ወረደ። 15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሲሣ​ራን፥ ሰረ​ገ​ሎ​ቹ​ንም ሁሉ፥ ሠራ​ዊ​ቱ​ንም ሁሉ ከባ​ርቅ ፊት በሰ​ይፍ ስለት አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው፤ ሲሣ​ራም ከሰ​ረ​ገ​ላው ወርዶ በእ​ግሩ ሸሸ። 16ባር​ቅም ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንና ሠራ​ዊ​ቱን እስከ አሕ​ዛብ አሪ​ሶት ድረስ አባ​ረረ፤ የሲ​ሣ​ራም ሠራ​ዊት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት ወደቀ፤ አንድ እንኳ አል​ቀ​ረም።
17ሲሣ​ራም ወደ ጓደ​ኛው ወደ ቄና​ዊው ወደ ሔቤር ሚስት ወደ ኢያ​ዔል ድን​ኳን በእ​ግሩ ሸሸ፤ በአ​ሶር ንጉሥ በኢ​ያ​ቢ​ንና በቄ​ና​ዊው በሔ​ቤር ቤት መካ​ከል ሰላም ነበ​ርና። 18ኢያ​ዔ​ልም ሲሣ​ራን ለመ​ቀ​በል ወጥታ፥ “ግባ፥ ጌታዬ ሆይ፥ ወደ እኔ ግባ፤ አት​ፍ​ራም” አለ​ችው። ወደ እር​ስ​ዋም ወደ ድን​ኳ​ንዋ ገባ፤ በም​ን​ጣ​ፍም ሸፈ​ነ​ችው። 19ሲሣ​ራም፥ “ጠም​ቶ​ኛ​ልና እባ​ክሽ የም​ጠ​ጣው ጥቂት ውኃ ስጪኝ” አላት፤ እር​ስ​ዋም የወ​ተ​ቱን ዕቃ ፈትታ አጠ​ጣ​ችው፤ ፊቱ​ንም ሸፈ​ነ​ችው። 20እር​ሱም፥ “ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ቁሚ፤ ሰውም መጥቶ፦ ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠ​ይ​ቅሽ አንቺ፦ ‘የለም’ ትዪ​ዋ​ለሽ” አላት። 21የሔ​ቤ​ርም ሚስት ኢያ​ዔል የድ​ን​ኳ​ኑን ካስማ ወሰ​ደች፤ በሁ​ለ​ተኛ እጅ​ዋም መዶሻ ያዘች፤ ቀስ ብላም ወደ እርሱ ቀረ​በች፤ በጆሮ ግን​ዱም ካስ​ማ​ውን ቸነ​ከ​ረ​ች​በት፤ እር​ሱም ደክሞ አን​ቀ​ላ​ፍቶ ነበ​ርና ካስ​ማው ወደ መሬት ጠለቀ፤ እር​ሱም ከእ​ግ​ርዋ በታች ተን​ፈ​ራ​ፈረ፤ ተዘ​ር​ሮም ሞተ። 22እነ​ሆም፥ ባርቅ ሲሣ​ራን ሲያ​ባ​ርር ኢያ​ዔል ልት​ገ​ና​ኘው ወጥታ፥ “ና፤ የም​ት​ሻ​ውን ሰው አሳ​ይ​ሃ​ለሁ” አለ​ችው። ወደ እር​ስ​ዋም ገባ፤ እነ​ሆም፥ ሲሣ​ራን ወድቆ፥ ሞቶም አገ​ኘው፤ ካስ​ማ​ውም በጆሮ ግንዱ ውስጥ ነበረ።
23በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የከ​ነ​ዓ​ንን ንጉሥ ኢያ​ቢ​ንን በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት አዋ​ረ​ደው። 24የከ​ነ​ዓ​ንን ንጉሥ ኢያ​ቢ​ን​ንም እስ​ኪ​ያ​ጠፉ ድረስ በከ​ነ​ዓን ንጉሥ በኢ​ያ​ቢን ላይ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እጅ እየ​በ​ረ​ታች ሄደች።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ