መጽሐፈ መሳፍንት 6
6
እስራኤል ስለ በደሉ በምድያማውያን እጅ እንደ ወደቁ
1የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሥራ ሠሩ፤ እግዚአብሔርም በምድያም እጅ ሰባት ዓመት አሳልፎ ሰጣቸው። 2የምድያምም እጅ በእስራኤል ላይ ጠነከረች፤ ከምድያምም ፊት የተነሣ የእስራኤል ልጆች በተራሮችና በገደሎች ላይ ጕድጓድና ዋሻ፥ ምሽግም አበጁ። 3የእስራኤልም ልጆች ዘር በዘሩ ጊዜ ምድያማውያንና አማሌቃውያን ይዘምቱባቸው ነበር፥ በምሥራቅም የሚኖሩ ልጆች አብረው ይዘምቱባቸው ነበር፤ 4በእነርሱም ላይ ይሰፍሩ ነበር፤ ወደ ጋዛም እስከሚደርሱ የእርሻቸውን ፍሬ ያጠፉ ነበር፤ በእስራኤልም ምድር ለሕይወት የሚሆን ምንም አይተዉም ነበር፤ ከመንጋዎችም በሬ ወይም አህያ ቢሆን አይተዉም ነበር። 5እንስሶቻቸውንና ድንኳኖቻቸውን ይዘው በብዛት እንደ አንበጣ ሆነው ይመጡባቸው ነበር፤ ለእነርሱና ለግመሎቻቸው ቍጥር አልነበራቸውም፤ ምድሪቱንም ያጠፏት ዘንድ ይመጡ ነበር። 6ከምድያምም ፊት የተነሣ እስራኤል እጅግ ተቸገሩ፤ የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ።
እግዚአብሔር ጌዴዎንን ለእስራኤል እንደ አስነሣላቸው
7እንዲህም ሆነ፤ የእስራኤል ልጆች በምድያም ምክንያት ወደ እግዚአብሔር በጮኹ ጊዜ፥ 8እግዚአብሔር ወደ እስራኤል ልጆች ነቢይ ላከ፤ እርሱም አለ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ከግብፅ ምድር አወጣኋችሁ፤ ከባርነትም ቤት አስለቀቅኋችሁ፤ 9ከግብፃውያንም እጅ ከሚጋፉአችሁም ሁሉ እጅ አዳንኋችሁ፤ ከፊታችሁም አሳደድኋቸው፤ ሀገራቸውንም ሰጠኋችሁ፤ 10እናንተንም፦ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ በምድራቸው የተቀመጣችሁባቸውን የአሞሬዎናውያንን አማልክት አትፍሩ አልኋችሁ። እናንተ ግን ቃሌን አልሰማችሁም።”
11የእግዚአብሔርም መልአክ መጥቶ በኤፍራታ ባለችው ለኤዝሪ አባት ለኢዮአስ በነበረችው ዛፍ በታች ተቀመጠ፤ ልጁም ጌዴዎን ከምድያማውያን ለማሸሽ በወይን መጭመቂያው ውስጥ ስንዴ ይወቃ ነበር። 12የእግዚአብሔርም መልአክ ለእርሱ ተገልጦ፥ “አንተ ጽኑዕ ኀያል ሰው! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው” አለው። 13ጌዴዎንም፥ “ጌታዬ ሆይ! እሺ፥ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ይህ ነገር ሁሉ ለምን ደረሰብን? አባቶቻችንስ፦ እግዚአብሔር ከግብፅ አውጥቶናል ብለው ይነግሩን የነበረ ተአምራት ወዴት አለ? አሁን ግን እግዚአብሔር ትቶናል፤ በምድያም እጅም አሳልፎ ሰጥቶናል” አለው። 14የእግዚአብሔርም መልአክ ወደ እርሱ ተመለከተና፥ “በዚህ በጕልበትህ ሂድ፤ እስራኤልንም ከምድያም እጅ ታድናቸዋለህ፤ እነሆ፥ ልኬሃለሁ” አለው። 15እርሱም፥ “ጌታ ሆይ! እሺ፥ እስራኤልን በምን አድናለሁ? ወገኔ በምናሴ ነገድ ዘንድ ጥቂቶች ናቸው፤ እኔም በአባቴ ቤት የሁሉ ታናሽ ነኝ” አለው። 16የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነው፤ ምድያምንም እንደ አንድ ሰው አድርገህ ታጠፋለህ” አለው። 17ጌዴዎንም፥ “በፊትህ ሞገስን ካገኘሁ፥ የምትናገረኝም አንተ እንደ ሆንህ ምልክት አድርግልኝ፤ 18ወደ አንተም እስክመለስ ድረስ፥ መሥዋዕቴንም አምጥቼ እስካቀርብልህ ድረስ፥ እባክህ፥ ከዚህ አትሂድ” አለው። እርሱም፥ “እስክትመለስ ድረስ እቈያለሁ” አለው። 19ጌዴዎንም ሄደ፤ የፍየሉንም ጠቦት፥ የኢፍ መስፈሪያም ዱቄት የቂጣ እንጎቻ አዘጋጀ፤ ሥጋውንም በሌማት አኖረ፤ መረቁንም በምንቸት ውስጥ አደረገ፤ ሁሉንም ይዞ በዛፍ በታች አቀረበለት። ሰገደለትም። 20የእግዚአብሔርም መልአክ፥ “ሥጋውንና የቂጣውን እንጎቻ ወስደህ በዚህ ድንጋይ ላይ አኑር፤ መረቁንም አፍስስ” አለው። እንዲሁም አደረገ። 21የእግዚአብሔርም መልአክ በእጁ ያለውን በትሩን ዘርግቶ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ አስነካ፤ እሳትም ከድንጋዩ ውስጥ ወጥታ ሥጋዉንና የቂጣዉን እንጎቻ በላች። የእግዚአብሔርም መልአክ ከዐይኖቹ ተሰወረ። 22ጌዴዎንም የእግዚአብሔር መልአክ እንደ ሆነ ዐወቀ። ጌዴዎንም፥ “አቤቱ! አምላኬ ሆይ! ወዮልኝ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ ፊት ለፊት አይቻለሁና” አለ። 23እግዚአብሔርም፥ “ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አትፍራ፤ አትሞትም” አለው። 24ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም እስከ ዛሬ ድረስ “የእግዚአብሔር ሰላም”#ዕብ. “እግዚአብሔር ሰላም” ይላል። ብሎ ጠራው። እርሱም እስከ ዛሬ ድረስ ለኤዝሪ አባት በሆነችው በኤፍራታ አለ።
25እንዲህም ሆነ፤ በዚያች ሌሊት እግዚአብሔር፥ “የአባትህን በሬ፥ ሰባት ዓመት የሆነውን ሁለተኛውን በሬ ውሰድ፤ የአባትህ የሆነውንም የበዓል መሠዊያ አፍርስ፤ በእርሱም ዙሪያ ያለውን የማምለኪያ ዐጸድ ቍረጥ፤ 26በዚያም ተራራ አናት ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር መሠዊያ አሳምረህ ሥራ፤ ሁለተኛዉንም በሬ ውሰድ፤ በዚያም በቈረጥኸው በማምለኪያ ዐጸዱ እንጨት ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቅርብ” አለው። 27ጌዴዎንም ከባሪያዎቹ ዐሥራ ሦስት#ዕብ. እና አንዳንድ የግሪክ ሰባ. ሊ. ዘርዕ “ዐሥር” ይላል። ሰዎችን ወስዶ እግዚአብሔር እንዳለው አደረገ፤ የአባቱንም ቤተ ሰቦች፥ የከተማዉንም ሰዎች ስለፈራ ይህን በቀን ለማድረግ አልቻለም፤ ነገር ግን በሌሊት አደረገው።
28የከተማውም ሰዎች ማልደው ተነሡ፤ እነሆም፥ የበዓል መሠዊያ ፈርሶ፥ በዙሪያውም ያለው የማምለኪያ ዐጸድ ተቈርጦ፥ በተሠራውም መሠዊያ ላይ ሁለተኛው በሬ ተሠውቶ አገኙት። 29እርስ በርሳቸውም፥ “ይህን ነገር ያደረገ ማን ነው?” ተባባሉ። በጠየቁና በመረመሩም ጊዜ፥ “ይህን ነገር ያደረገ የኢዮአስ ልጅ ጌዴዎን ነው” አሉ። 30የከተማዉም ሰዎች ኢዮአስን፥ “የበዓልን መሠዊያ አፍርሶአልና፥ በዙሪያውም ያለውን የማምለኪያ ዐጸድ ቈርጦአልና ይገደል ዘንድ ልጅህን አምጣ” አሉት። 31ኢዮአስም በእርሱ ላይ የተነሡበትን ሁሉ፥ “ለበዓል እናንተ ዛሬ ትበቀሉለታላችሁን? ወይስ የበደለውን ትገድሉለት ዘንድ የምታድኑት እናንተ ናችሁን? እርሱ አምላክ ከሆነስ የበደለው እስከ ነገ ድረስ ይሙት። መሠዊያዉንም ያፈረሰውን እርሱ ይበቀለው” አላቸው። 32በዚያች ቀንም መሠዊያዉን አፍርሶአልና በዓል ከእርሱ ጋር ይሟገት ሲል ጌዴዎንን ይሩበኣል ብሎ ጠራው።
33ምድያምና አማሌቅም ሁሉ፥ የምሥራቅም ልጆች አንድ ሆነው ተሰበሰቡ፤ ተሻግረውም በኢይዝራኤል ሸለቆ ሰፈሩ። 34ጌዴዎንንም የእግዚአብሔር መንፈስ አጸናው፤ እርሱም ቀንደ መለከቱን ነፋ፤ አብዔዜርም በኋላው ጮኸ። 35ወደ ምናሴም ነገድ ሁሉ መልእክተኞችን ላከ፤ እርሱም ከኋላው ሆኖ ጮኸ፤#“እርሱም በኋላው ሁኖ ጮኸ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። መልእክተኞችንም ወደ አሴርና ወደ ዛብሎን ወደ ንፍታሌምም ላከ፤ እነርሱም ሊቀበሉአቸው ወጡ።
36ጌዴዎንም እግዚአብሔርን፥ “እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ ታድን እንደ ሆነ፥ 37እነሆ! በዐውድማዉ ላይ የተባዘተ የበግ ጠጕር አኖራለሁ፤ በጠጕሩ ብቻ ላይ ጠል ቢሆን በምድሩም ሁሉ ደረቅ ቢሆን፥ እንደ ተናገርህ የእስራኤልን ልጆች በእኔ እጅ እንደምታድናቸው አውቃለሁ” አለ። 38እንዲሁም ሆነ፤ በነጋው ማልዶ ተነሣ፤ ጠጕሩንም ጨመቀው፤ ከጠጕሩም የተጨመቀው ጠል አንድ መንቀል ሙሉ ውኃ ሆነ። 39ጌዴዎንም እግዚአብሔርን አለው፥ “በቍጣህ አትቈጣኝ፤ ደግሞ አንዲት ነገር ልናገር፤ ጠጕሩ ብቻውን ደረቅ ይሁን፤ በምድሩም ላይ ጠል ይውረድ።” 40እግዚአብሔርም በዚያች ሌሊት እንዲሁ አደረገ፤ ጠጕሩ ብቻ ደረቅ ሆነ፥ በምድሩም ሁሉ ላይ ጠል ወረደ።
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት 6: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ