የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 8

8
የጌ​ዴ​ዎን የመ​ጨ​ረ​ሻው ድል
1የኤ​ፍ​ሬም ሰዎ​ችም፥ “ይህ ያደ​ረ​ግ​ህ​ብን ምን​ድን ነው? ምድ​ያ​ምን ለመ​ዋ​ጋት በወ​ጣህ ጊዜ ለምን አል​ጠ​ራ​ኸ​ንም?” አሉት። ጽኑ ጥልም ተጣ​ሉት። 2እር​ሱም፥ “እኔ ዛሬ እና​ንተ እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ሁት ምን አደ​ረ​ግሁ? የኤ​ፍ​ሬም ወይን ቃር​ሚያ ከአ​ቢ​ዔ​ዜር ወይን መከር አይ​ሻ​ል​ምን? 3እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ድ​ያ​ምን አለ​ቆች ሔሬ​ብ​ንና ዜብን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋል እና​ንተ ያደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ትን የሚ​መ​ስል እኔ ምን ማድ​ረግ እችል ኖር​አል?” አላ​ቸው። ከዚህ በኋላ ተዉት፤ ይህን ቃል በተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውም ጊዜ መን​ፈ​ሳ​ቸው ዐረ​ፈች።
4ጌዴ​ዎ​ንም ወደ ዮር​ዳ​ኖስ መጥቶ ተሻ​ገረ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ያሉት ሦስት መቶ ሰዎች ተሻ​ገሩ፤ ምንም እንኳ ቢራ​ቡም ያሳ​ድዱ ነበር። 5የሱ​ኮ​ት​ንም ሰዎች፥ “ተር​በ​ዋ​ልና እኔን ለተ​ከ​ተሉ ሰዎች እባ​ካ​ችሁ እህል ስጡ​አ​ቸው፤ እኔም የም​ድ​ያ​ምን ነገ​ሥ​ታት ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን አሳ​ድ​ዳ​ለሁ” አላ​ቸው። 6የሱ​ኮ​ትም አለ​ቆች፥ “እኛ ለሠ​ራ​ዊ​ትህ እህል እን​ድ​ን​ሰጥ የዛ​ብ​ሄ​ልና የስ​ል​ማና እጅ አሁን በእ​ጅህ ነውን?” አሉ። 7ጌዴ​ዎ​ንም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን በእጄ አሳ​ልፎ ቢሰ​ጠኝ እኔ በም​ድረ በዳ እሾ​ህና በኩ​ር​ን​ችት ሥጋ​ች​ሁን እገ​ር​ፋ​ለሁ” አለ። 8ከዚ​ያም ወደ ፋኑ​ሄል ወጣ፤ ለፋ​ኑ​ሄ​ልም ሰዎች እን​ዲሁ አላ​ቸው፤ የፋ​ኑ​ሄ​ልም ሰዎች የሱ​ኮት ሰዎች እንደ መለሱ መለ​ሱ​ለት። 9እር​ሱም የፋ​ኑ​ሄ​ልን ሰዎች፥ “በደ​ኅና በተ​መ​ለ​ስሁ ጊዜ ይህን ግንብ አፈ​ር​ሰ​ዋ​ለሁ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።
10ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር በቀ​ር​ቀር ነበሩ፤ ሰይፍ የሚ​መ​ዝዙ መቶ ሃያ ሺህ ሰዎች ወድ​ቀው ነበ​ርና ከም​ሥ​ራቅ ሰዎች ሠራ​ዊት ሁሉ የቀሩ ዐሥራ አም​ስት ሺህ ያህል ሰዎች ነበሩ። 11ጌዴ​ዎ​ንም በድ​ን​ኳን የሚ​ኖሩ ሰዎች ባሉ​በት መን​ገድ በኖ​ቤ​ትና በዮ​ግ​ቤል#“በዮ​ግ​ቤል” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ። በም​ሥ​ራቅ በኩል ወጣ፤ ሠራ​ዊ​ቱም ተዘ​ልሎ ሳለ አጠ​ፋ​ቸው። 12ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም ሸሹ፤ እር​ሱም አሳ​ደ​ዳ​ቸው፤ ሁለ​ቱ​ንም የም​ድ​ያም ነገ​ሥ​ታት ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን ያዘ፤ ጌዴ​ዎ​ንም ሠራ​ዊ​ቱን ሁሉ አጠፋ።
13የኢ​ዮ​አስ ልጅ ጌዴ​ዎ​ንም ከአ​ሬስ ዳገት ከጦ​ር​ነት ተመ​ለሰ። 14ከሱ​ኮ​ትም ሰዎች አንድ ብላ​ቴና ይዞ መረ​መ​ረው፤ እር​ሱም ሰባ ሰባ​ቱን የሱ​ኮ​ትን አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችን አስ​ቈ​ጠ​ራ​ቸው። 15ጌዴ​ዎ​ንም ወደ ሱኮት አለ​ቆች መጥቶ፥ “ለደ​ከ​ሙት ሰዎ​ችህ እህል እን​ሰጥ ዘንድ የዛ​ብ​ሄ​ልና የስ​ል​ማና እጅ አሁን በእ​ጅህ ነውን? ብላ​ችሁ የተ​ላ​ገ​ዳ​ች​ሁ​ብኝ፥ ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማና እነሆ፥” አለ። 16የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ችና አለ​ቆች ያዘ፥ የም​ድረ በዳ​ንም እሾ​ህና ኩር​ን​ችት ወስዶ የሱ​ኮ​ትን ሰዎች ገረ​ፋ​ቸው። 17የፋ​ኑ​ሄ​ል​ንም ግንብ አፈ​ረሰ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሰዎች ገደ​ላ​ቸው።
18ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን፥ “በታ​ቦር የገ​ደ​ላ​ች​ኋ​ቸው ሰዎች እን​ዴት ያሉ ነበሩ?” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እን​ዳ​ንተ ያሉ ነበሩ፤ አን​ተ​ንም ይመ​ስሉ ነበር፤ መል​ካ​ቸ​ውም እንደ ነገ​ሥት ልጆች መልክ ነበረ” ብለው መለ​ሱ​ለት። 19ጌዴ​ዎ​ንም፥ “የእ​ናቴ ልጆች ወን​ድ​ሞቼ ነበሩ፤ አድ​ና​ች​ኋ​ቸው ቢሆን ኖሮ፥ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! እኔ አል​ገ​ድ​ላ​ች​ሁም ነበር” አለ። 20በኵ​ሩ​ንም ዮቶ​ርን፥ “ተነ​ሥ​ተህ ግደ​ላ​ቸው” አለው፤ ብላ​ቴ​ናው ግን ገና ትንሽ ነበ​ረና ስለ ፈራ ሰይ​ፉን አል​መ​ዘ​ዘም። 21ዛብ​ሄ​ልና ስል​ማ​ናም፥ “ኀይ​ልህ እንደ ጐል​ማሳ ኀይል ነውና አንተ ተነ​ሥ​ተህ ውደ​ቅ​ብን” አሉት። ጌዴ​ዎ​ንም ተነ​ሥቶ ዛብ​ሄ​ል​ንና ስል​ማ​ናን ገደለ፤ በግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አን​ገት የነ​በ​ሩ​ትን ሥሉ​ሴ​ዎች ማረከ።
22የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ጌዴ​ዎ​ንን፥ “ከም​ድ​ያም እጅ አድ​ነ​ኸ​ና​ልና አንተ፥ ልጅ​ህም፥ የልጅ ልጅ​ህም#“የልጅ ልጅ​ህም” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ። ደግሞ ግዙን” አሉት። 23ጌዴ​ዎ​ንም፥ “እኔ አል​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ ልጄም አይ​ገ​ዛ​ች​ሁም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይገ​ዛ​ች​ኋል እንጂ” አላ​ቸው። 24እስ​ማ​ኤ​ላ​ው​ያ​ንም ስለ ነበሩ የወ​ርቅ ጕትቻ ነበ​ራ​ቸ​ውና ጌዴ​ዎን፥ “ሁላ​ች​ሁም ከም​ር​ኮ​አ​ችሁ ጕት​ቻ​ች​ሁን እን​ድ​ት​ሰ​ጡኝ እለ​ም​ና​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው። 25እነ​ር​ሱም፥ “መስ​ጠ​ትን ፈቅ​ደን እን​ሰ​ጥ​ሃ​ለን” ብለው መለ​ሱ​ለት። መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም አነ​ጠፉ፤ ሰውም ሁሉ የም​ር​ኮ​ውን ጕትቻ በዚያ ላይ ጣለ። 26የለ​መ​ነ​ውም የወ​ርቅ ጕትቻ ሚዛኑ ከአ​ም​ባሩ፥ ከድ​ሪ​ውም፥ የም​ድ​ያ​ምም ነገ​ሥ​ታት ከለ​በ​ሱት ከቀዩ ቀሚስ፥ በግ​መ​ሎ​ቻ​ቸ​ውም አን​ገት ከነ​በ​ሩት ሥሉ​ሴ​ዎች ሌላ ሺህ ሰባት መቶ ሰቅለ ወርቅ ነበረ። 27ጌዴ​ዎ​ንም ምስል#ዕብ. እና ግሪክ ሰባ. ሊ. “ኤፉድ” ይላል። አድ​ርጎ ሠራው፤ በከ​ተ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ራታ አኖ​ረው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተከ​ትሎ አመ​ነ​ዘ​ረ​በት፤ ለጌ​ዴ​ዎ​ንና ለቤ​ቱም ወጥ​መድ ሆነ። 28ምድ​ያ​ምም በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተዋ​ረዱ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ዳግ​መኛ አላ​ነ​ሡም፤ በጌ​ዴ​ዎ​ንም ዕድሜ ምድ​ሪቱ አርባ ዓመት ዐረ​ፈች።
የጌ​ዴ​ዎን ሞት
29የኢ​ዮ​አ​ስም ልጅ ይሩ​በ​ኣል ሄዶ በቤቱ ተቀ​መጠ። 30ለጌ​ዴ​ዎ​ንም ብዙ ሚስ​ቶች ነበ​ሩ​ትና ከአ​ብ​ራኩ የወጡ ሰባ ልጆች ነበ​ሩት። 31በሴ​ኬ​ምም የነ​በ​ረ​ችው ዕቅ​ብቱ ወንድ ልጅ ወለ​ደ​ች​ለት፤ ስሙ​ንም አቤ​ሜ​ሌክ ብሎ ጠራው። 32የኢ​ዮ​አ​ስም ልጅ ጌዴ​ዎን በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ሞተ፤ በአ​ብ​ያ​ዜ​ራ​ው​ያ​ንም ከተማ በኤ​ፍ​ራታ በነ​በ​ረ​ችው በአ​ባቱ በኢ​ዮ​አስ መቃ​ብር ተቀ​በረ።
33እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ጌዴ​ዎን ከሞተ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ለሱ፤ በዓ​ሊ​ም​ንም ተከ​ት​ለው አመ​ነ​ዘሩ፤ በዓ​ሊ​ምም አም​ላክ ይሆ​ና​ቸው ዘንድ ከእ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን ገቡ። 34የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዙ​ሪ​ያ​ቸው ከነ​በ​ሩት ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ እጅ ያዳ​ና​ቸ​ውን አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ሰ​ቡ​ትም፤ 35እር​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል በጎ ነገ​ርን ሁሉ እን​ዳ​ደ​ረገ መጠን፥ እነ​ርሱ ይሩ​በ​ኣል ለተ​ባ​ለው ለጌ​ዴ​ዎን ቤት ወረታ አላ​ደ​ረ​ጉም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ