ትንቢተ ኤርምያስ 6
6
የኢየሩሳሌም በጠላት መከበብ
1እናንተ የብንያም ልጆች፥ ክፉ ነገር፥ ታላቅም ጥፋት ከመስዕ ይጐበኛልና ከኢየሩሳሌም ውስጥ ለመሸሽ ጽኑ፤ በቴቁሔ መለከቱን ንፉ፤ በቤትካሪም ላይ ምልክትን አንሡ። 2ቅምጥል የጽዮን ልጅ ሆይ! ውበትሽ ይጐሳቈላል። 3እረኞችና መንጎቻቸው ወደ እርስዋ ይመጣሉ፤ በዙሪያዋም ድንኳኖቻቸውን ይተክሉባታል፤ በእጃቸውም#ዕብ. “በስፍራው” ይላል። መንጋቸውን ያሰማራሉ።
4በእርስዋ ላይ ሰልፍ አዘጋጁ፤ ተነሡ፥ በቀትርም እንውጣ። ቀኑ መሽቶአልና፥ የቀኑም ጥላ አልፎአልና ወዮልን። 5ተነሡ በሌሊትም እንውጣ፤ መሠረቶችዋንም#ዕብ. “አዳራሾችዋን” ይላል። እናፍርስ። 6ኀያል እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ዛፎችዋን ቍረጡ፤ በኢየሩሳሌምም ላይ ኀይልን አፍስሱ#ዕብ. “አፈርን ደልድሉ” ይላል። ይህች ከተማ የሐሰት ከተማ ናት፤ መካከልዋ ሁሉ ግፍ ብቻ ነው። 7#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ጕድጓድ ውኃን እንደሚያቀዘቅዝ እንዲሁ ክፋቷ እርስዋን ያቀዘቅዛታል” ይላል።በጕድጓድ ውኃ እንደሚፈልቅ፥ እንዲሁ ክፋቷ ከእርስዋ ዘንድ ይፈልቃል፤ ግፍና ቅሚያ በእርስዋ ዘንድ ይሰማል፤ ደዌና ቍስልም ሁልጊዜ በፊቷ አለ። 8ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ነፍሴ ከአንቺ እንዳትለይ፥ አንቺንም ባድማና ወና እንዳላደርግሽ፥ ተግሣጽን ተቀበዪ።
የእስራኤል ዐመፀኛነት
9እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሰው ወይንን እንደሚቃርም፥ እንዲሁ ከእስራኤል የቀሩትን ይቃርሙአቸዋል፤ እጅህን እንደ ወይን ለቃሚ ወደ እንቅብ ዘርጋ። 10ይሰሙኝስ ዘንድ ለማን እናገራለሁ? ለማንስ አዳኛለሁ? እነሆ፥ ጆሮአቸው ያልተገረዘች ናት፤ ለመስማትም አይችሉም፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቃል ለስድብ ሆኖባቸዋል፥ ይሰሙት ዘንድ አልፈቀዱምና። 11ስለዚህ ቍጣዬን መላሁባቸው፤ ታገሥሁ፤ ፈጽሜም አላጠፋኋቸውም፤ በሜዳ በሕፃናት ላይ በጐልማሶችም ጉባኤ ላይ መዓቴን በአንድነት አፈስስባቸዋለሁ፤ ባል ከሚስቱ ጋር ሽማግሌውም ከጎበዙ ጋር ይያያዛልና። 12እጄን በዚች ምድር በሚኖሩ ላይ እዘረጋለሁና ቤቶቻቸዉ፥ እርሻዎቻቸውም፥ ሴቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሰጣሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ 13ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ኀጢአትን አድርገዋልና፥ ከሐሳዊ ነቢይ#“ከሐሳዊ ነቢይ” የሚለው በዕብ. የለም። ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ሐሰትን አደረጉ። 14የሕዝቤንም ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን፦ ሰላም ሰላም ይላሉ። 15ርኩስ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፤ ውርደትንም አላወቁም፤ ስለዚህም ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥” ይላል እግዚአብሔር።
16እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፤ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእርስዋም ላይ ሂዱ፤ ለነፍሳችሁም መድኀኒትን ታገኛላችሁ፤” እነርሱ ግን፥ “አንሄድባትም” አሉ። 17እኔም፥ “የመለከቱን ድምፅ አድምጡ” ብዬ ጠባቂዎችን ሾምሁባቸው፤ እነርሱ ግን፥ “አናዳምጥም” አሉ። 18አሕዛብና የመንጋው ጠባቂዎች ሆይ፥ ስለዚህ ስሙ። 19ምድር ሆይ፥ ስሚ! እነሆ ቃሌን ስላልሰሙ፥ ሕጌንም ስለ ጣሉ፥ እኔንም ስለ ናቁ በዚህ ሕዝብ ላይ እንደ ሥራቸው ፍሬ፥ ክፉን ነገር አመጣባቸዋለሁ። 20ስለ ምንስ ከሳባ ዕጣንን፥ ከሩቅም ሀገር ቀረፋን ታቀርቡልኛላችሁ? የሚቃጠለውን መሥዋዕታችሁን አልቀበለውም፤ ቍርባናችሁም ደስ አያሰኘኝም። 21ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ሕዝብ ላይ ደዌን አሳድራለሁ፤ አባቶችና ልጆችም በአንድነት ይታመማሉ፤ ጎረቤትና ባልንጀራም ይጠፋሉ።
ከወደ ሰሜን የሚመጣ ወራሪ
22እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ሕዝብ ከሰሜን ሀገር ይመጣል፤ ታላቅ ሕዝብም#በግእዝ “ወነገሥትሂ ብዙኃን” የሚል አለው። ከምድር ዳርቻ ይነሣል። 23ቀስትንና ጦርን ይይዛሉ፤ ጨካኞች ናቸው፤ ምሕረትም አያደርጉም፤ ድምፃቸው እንደ ባሕር ሞገድ ይተምማል፤ በሰረገላና በፈረሶችም ላይ ይቀመጣሉ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ! እንደ እሳት ያጠፉሻል።#ዕብ. “ለሰልፍ እንደ ተዘጋጀ ሰው እያንዳንዳቸው በአንቺ ላይ ተሰለፉ” ይላል። 24ጩኸታቸውን ሰምተን፥ እጃችን ደክማለች፤ ወላድን ሴት ምጥ እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞናል። 25የጠላት ሰይፍ#ዕብ. “ድንጋጤ” የሚል ቃል ይጨምራል። ከብበዋችኋልና ወደ ሜዳ አትውጡ፤ በመንገድም ላይ አትሂዱ። 26የሕዝቤ ልጅ ሆይ፥ ማቅ ልበሺ፤ በራስሺም ላይ አመድ ነስንሺ፥ አጥፊ በላያችን በድንገት ይመጣብናልና ለተወዳጅ ልጅ#ዕብ. “ለአንድያ ልጅ” ይላል። እንደሚደረግ ልቅሶ መራራ ልቅሶ አልቅሺ።
27በተፈታኝ ሕዝቤ መካከል ፈታኝ አድርጌሃለሁ፤ መንገዳቸውንም በፈተንሁ ጊዜ ታውቀኛለህ። 28እነርሱ ሁሉ እጅግ ደንቆሮዎች ናቸው፤ በጠማማነት ይሄዳሉ፤ ሁሉም እንደ ናስና ብረት የዛጉ ናቸው። 29ወናፉን የሚአናፋው ደከመ፤ እርሳሱም በእሳት ቀለጠ፤ አንጥረኛውም መልሶ በከንቱ ያቀልጠዋል፤ ኀጢአታቸውም አልተወገደም። 30እግዚአብሔር ንቆአቸዋልና የተናቀ ብር ብላችሁ ጥሩአቸው።
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 6: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ