የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 13

13
ጌታ የደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እግር እንደ አጠበ
1ከፋ​ሲካ በዓል አስ​ቀ​ድሞ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ከዚህ ዓለም ወደ ላከው ወደ አብ ይሄድ ዘንድ ጊዜው እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ በዓ​ለም ያሉ​ትን የወ​ደ​ዳ​ቸ​ውን ወገ​ኖ​ቹን ፈጽሞ ወደ​ዳ​ቸው። 2ራት ሲበ​ሉም አሳ​ልፎ ይሰ​ጠው ዘንድ በስ​ም​ዖን ልጅ በአ​ስ​ቆ​ሮቱ ሰው በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደረ። 3ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ አብ ሁሉን በእጁ እንደ ሰጠው፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ወጣ፥ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ደ​ሚ​ሄድ ባወቀ ጊዜ፥ 4ራት ከሚ​በ​ሉ​በት ተነ​ሥቶ ልብ​ሱን አኖ​ረና ማበሻ ጨርቅ አን​ሥቶ ወገ​ቡን ታጠቀ። 5በኵ​ስ​ኵ​ስ​ቱም ውኃ ቀድቶ የደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱን እግር ያጥብ ጀመር፤ በዚያ በታ​ጠ​ቀው ማበሻ ጨር​ቅም አበሰ። 6ወደ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ደረሰ፤ እር​ሱም፥ “አቤቱ፥ አንተ እግ​ሬን ታጥ​በ​ኛ​ለ​ህን?” አለው። 7ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እኔ የም​ሠ​ራ​ውን አንተ ዛሬ አታ​ው​ቅም፤ ኋላ ግን ታስ​ተ​ው​ለ​ዋ​ለህ” ብሎ መለ​ሰ​ለት። 8ጴጥ​ሮ​ስም፥ “መቼም ቢሆን አንተ እግ​ሬን አታ​ጥ​በ​ኝም” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ እኔ እግ​ር​ህን ካላ​ጠ​ብ​ሁህ ከእኔ ጋር ዕድል ፋንታ የለ​ህም” ብሎ መለ​ሰ​ለት። 9ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም፥ “አቤቱ፥ እን​ኪ​ያስ የም​ታ​ጥ​በኝ እጆ​ች​ንና ራሴ​ንም እንጂ እግ​ሮ​ችን ብቻ አይ​ደ​ለም፤” አለው። 10ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ፈጽሞ የታ​ጠበ ከእ​ግሩ በቀር ሊታ​ጠብ አያ​ስ​ፈ​ል​ገ​ውም፤ ሁለ​ን​ተ​ናው ንጹሕ ነውና፤ እና​ን​ተማ ንጹ​ሓን ናችሁ፤ ነገር ግን ሁላ​ችሁ አይ​ደ​ላ​ች​ሁም” አለው። 11ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጠ​ውን ያውቅ ነበ​ርና ስለ​ዚህ “ሁላ​ችሁ ንጹ​ሓን አይ​ደ​ላ​ች​ሁም” አለ።
ለደቀ መዛ​ሙ​ርቱ የተ​ና​ገ​ረው ቃል
12እግ​ራ​ቸ​ው​ንም ካጠ​ባ​ቸው በኋላ ልብ​ሱን አን​ሥቶ ለበ​ሰና እንደ ገና ከእ​ነ​ርሱ ጋር ተቀ​መጠ፤ እን​ዲ​ህም አላ​ቸው፥ “ያደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ች​ሁን ዐወ​ቃ​ች​ሁን? 13እና​ንተ ‘መም​ህ​ራ​ችን፥ ጌታ​ች​ንም’ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካም ትላ​ላ​ችሁ፤ እኔ እን​ዲሁ ነኝና። 14እን​ግ​ዲህ እኔ መም​ህ​ራ​ች​ሁና ጌታ​ችሁ ስሆን እግ​ራ​ች​ሁን ካጠ​ብ​ኋ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ የባ​ል​ጀ​ሮ​ቻ​ች​ሁን እግር ልታ​ጥቡ ይገ​ባ​ች​ኋል።#በግ​ሪኩ “እርስ በር​ሳ​ችሁ ልት​ተ​ጣ​ጠቡ ይገ​ባ​ች​ኋል” ይላል። 15#ሉቃ. 22፥27። እኔ እንደ አደ​ረ​ግ​ሁ​ላ​ችሁ እና​ን​ተም ልታ​ደ​ርጉ ምሳሌ ሰጥ​ቻ​ች​ኋ​ለ​ሁና። 16#ማቴ. 10፥24፤ ሉቃ. 6፥40፤ ዮሐ. 15፥20። እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከጌ​ታው የሚ​በ​ልጥ አገ​ል​ጋይ የለም፤ ከላ​ከው የሚ​በ​ልጥ መል​እ​ክ​ተ​ኛም የለም። 17ይህ​ንም ዐው​ቃ​ችሁ ብት​ሠሩ ብፁ​ዓን ናችሁ። 18#መዝ. 40፥9። ነገር ግን ይህን የም​ና​ገር ስለ ሁላ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ የመ​ረ​ጥ​ኋ​ቸው እነ​ማን እንደ ሆኑ እኔ አው​ቃ​ለሁ፤ ነገር ግን መጽ​ሐፍ ‘እን​ጀ​ራ​ዬን የሚ​መ​ገብ ተረ​ከ​ዙን በእኔ ላይ አነሣ’ ያለው ይፈ​ጸም ዘንድ ነው። 19በሆ​ነም ጊዜ እኔ እንደ ሆንሁ ታምኑ ዘንድ ከዛሬ ጀምሮ ከመ​ሆኑ አስ​ቀ​ድሞ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ። 20#ማቴ. 10፥40፤ ማር. 9፥37፤ ሉቃ. 9፥48፤ 10፥16። እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ የም​ል​ከ​ውን የሚ​ቀ​በል እኔን ይቀ​በ​ላል፤ እኔ​ንም የሚ​ቀ​በል የላ​ከ​ኝን ይቀ​በ​ላል።”
አሳ​ልፎ የሚ​ሰ​ጠ​ውን ስለ ማመ​ል​ከቱ
21ይህ​ንም ተና​ግሮ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በልቡ አዘነ፤ መሰ​ከረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “እው​ነት እው​ነት እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከእ​ና​ንተ አንዱ አሳ​ልፎ ይሰ​ጠ​ኛል።” 22ደቀ መዛ​ሙ​ር​ቱም ይህን ስለ ማን እንደ ተና​ገረ ተጠ​ራ​ጥ​ረው እርስ በር​ሳ​ቸው ተያዩ፤ 23ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይወ​ደው የነ​በረ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ አንዱ በጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ አጠ​ገብ ተቀ​ምጦ ነበር። 24ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም እር​ሱን ጠቀ​ሰና፥ “ይህን ስለ ማን እንደ ተና​ገረ ጠይ​ቀህ ንገ​ረን” አለው። 25ያም ደቀ መዝ​ሙር በጌ​ታ​ችን ኢየ​ሱስ አጠ​ገብ ቀረብ ብሎ፥ “ጌታ ሆይ፥ እርሱ ማነው?” አለው። 26ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ይህ እኔ እን​ጀራ በወጥ አጥ​ቅሼ የም​ሰ​ጠው ነው” አለው፤ ያን ጊዜም እን​ጀራ በወጥ አጥ​ቅሶ ለስ​ም​ዖን ልጅ ለአ​ስ​ቆ​ሮ​ታ​ዊው ይሁዳ ሰጠው። 27እን​ጀ​ራ​ው​ንም ከተ​ቀ​በለ በኋላ ወዲ​ያ​ውኑ በይ​ሁዳ ልብ ሰይ​ጣን አደ​ረ​በት፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲህ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ፈጥ​ነህ አድ​ርግ” አለው። 28አብ​ረ​ው​ትም በማ​ዕድ የተ​ቀ​መ​ጡት ስለ ምን ይህን እን​ዳ​ለው አላ​ወ​ቁም። 29ሙዳየ ምጽ​ዋቱ በይ​ሁዳ ዘንድ ነበ​ረና፥ ለበ​ዓል የም​ን​ሻ​ውን ወይም ለነ​ዳ​ያን የም​ን​ሰ​ጠ​ውን ግዛ#በግ​ሪኩ “... ለበ​ዓል የም​ን​ሻ​ውን ግዛ ወይም ለነ​ዳ​ያን ስጥ ያለው የመ​ሰ​ላ​ቸው ነበሩ” ይላል። ያለው የመ​ሰ​ላ​ቸው ነበሩ። 30ይሁ​ዳም ያን እን​ጀራ ተቀ​ብሎ ወዲ​ያ​ውኑ ወጣ፥ ሌሊ​ትም ነበር።።
ከራት በኋላ የተ​ነ​ገረ
31ይሁ​ዳም ከወጣ በኋላ ያን​ጊዜ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን የሰው ልጅ ከበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ርሱ ከበረ። 32እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ርሱ ከከ​በረ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ሱን ያከ​ብ​ረ​ዋል፥ ያን​ጊ​ዜም ያከ​ብ​ረ​ዋል። 33#ዮሐ. 7፥34። ልጆች ሆይ፥ ገና ጥቂት ጊዜ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ፤ ትሹ​ኛ​ላ​ችሁ፤ ለአ​ይ​ሁ​ድም እኔ ወደ​ም​ሄ​ድ​በት እና​ንተ መም​ጣት አይ​ቻ​ላ​ች​ሁም እን​ዳ​ል​ኋ​ቸው፥ አሁ​ንም ለእ​ና​ንተ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ።
ስለ አዲስ ትእ​ዛዝ
34 # ዮሐ. 15፥12፤ 17፤ 1ዮሐ. 3፥23፤ 2ዮሐ. 5። “እርስ በር​ሳ​ችሁ ቷደዱ ዘንድ፥ አዲስ ትእ​ዛዝ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ እንደ ወደ​ድ​ኋ​ችሁ እና​ን​ተም እን​ዲሁ እርስ በር​ሳ​ችሁ ተዋ​ደዱ። 35እርስ በር​ሳ​ች​ሁም ብቷ​ደዱ፥ የእኔ ደቀ መዛ​ሙ​ርት እንደ ሆና​ችሁ በዚህ ሁሉ ያው​ቋ​ች​ኋል።”
ጌታ ጴጥ​ሮስ እን​ደ​ሚ​ክድ ስለ መና​ገሩ
36ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ትሄ​ዳ​ለህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ፥ “ወደ​ም​ሄ​ድ​በት አሁን ልት​ከ​ተ​ለኝ አት​ች​ልም፤ ኋላ ግን ትከ​ተ​ለ​ኛ​ለህ” አለው። 37ጴጥ​ሮ​ስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ስለ ምን አሁን ልከ​ተ​ልህ አል​ች​ልም? እኔ ነፍ​ሴ​ንም እንኳ ቢሆን ስለ አንተ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ” አለው። 38ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፤ “ነፍ​ስ​ህን ስለ እኔ አሳ​ል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለ​ህን? እው​ነት እው​ነት እል​ሃ​ለሁ፤ ሦስት ጊዜ እስ​ክ​ት​ክ​ደኝ ዶሮ አይ​ጮ​ህም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ