የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 17

17
ጌታ​ችን ወደ አብ እንደ ጸለየ
1ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ይህን ነገር ተና​ግሮ ዐይ​ኖ​ቹን ወደ ሰማይ አነ​ሣና እን​ዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደር​ሶ​አ​ልና ልጅህ ያከ​ብ​ርህ ዘንድ ልጅ​ህን አክ​ብ​ረው፤ 2ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ። 3ብቻ​ህን እው​ነ​ተኛ አም​ላክ የሆ​ንህ አን​ተን፥ የላ​ክ​ኸ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወት ናት። 4እኔ ልሠ​ራው የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ሥራ ፈጽሜ በም​ድር ላይ አከ​በ​ር​ሁህ። 5አሁ​ንም አባት ሆይ፥ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ከአ​ንተ ጋር በነ​በ​ረኝ ክብር በአ​ንተ ዘንድ አክ​ብ​ረኝ።
6“ከዓ​ለም ለይ​ተህ ለሰ​ጠ​ኸኝ ሰዎች ስም​ህን ገለ​ጥሁ፤ ያንተ ነበሩ፤ እነ​ር​ሱ​ንም ለእኔ ሰጥ​ተ​ኸ​ኛል፤ ቃል​ህ​ንም ጠበቁ። 7የሰ​ጠ​ኸ​ኝም ሁሉ ከአ​ንተ እንደ ሆነ ዛሬ ዐወቁ። 8የሰ​ጠ​ኽ​ኝን ቃል ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና፤ እነ​ር​ሱም ተቀ​ብ​ለው ከአ​ንተ እንደ ወጣሁ በእ​ው​ነት ዐወቁ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ አመኑ። 9እኔ ስለ እነ​ርሱ እለ​ም​ና​ለሁ፤ የም​ለ​ም​ንህ ስለ ዓለም አይ​ደ​ለም፤ ስለ ሰጠ​ኸኝ ነው እንጂ፤ ያንተ ናቸ​ውና። 10የእ​ኔም የሆነ ሁሉ የአ​ንተ ነው፤ የአ​ን​ተም የሆነ የእኔ ነው፤ እኔም በእ​ነ​ርሱ ከብ​ሬ​አ​ለሁ። 11እን​ግ​ዲህ በዓ​ለም አል​ኖ​ርም፤ እነ​ርሱ ግን በዓ​ለም ይኖ​ራሉ፤ እኔም ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ ቅዱስ አባት ሆይ፥ እነ​ዚ​ህን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ በስ​ምህ ጠብ​ቃ​ቸው፤ 12#መዝ. 40፥9፤ ዮሐ. 13፥18። እኔ በዓ​ለም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሳለሁ ግን የሰ​ጠ​ኸ​ኝን በስ​ምህ እጠ​ብ​ቃ​ቸው ነበር፤ ጠበ​ቅ​ኋ​ቸ​ውም፤ የመ​ጽ​ሐ​ፉም ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ከጥ​ፋት ልጅ በቀር ከእ​ነ​ርሱ አንድ ስን​ኳን አል​ጠ​ፋም። 13አሁን ግን ወደ አንተ እመ​ጣ​ለሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ደስ​ታዬ ፍጹም ይሆን ዘንድ ይህን በዓ​ለም እና​ገ​ራ​ለሁ። 14እኔ ቃል​ህን ሰጠ​ኋ​ቸው፤ ዓለም ግን ጠላ​ቸው፤ እኔ ከዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ደ​ለሁ እነ​ርሱ ከዓ​ለም አይ​ደ​ሉ​ምና። 15ከክፉ ነገር እን​ድ​ት​ጠ​ብ​ቃ​ቸው ነው እንጂ ከዓ​ለም እን​ድ​ት​ለ​ያ​ቸው አል​ለ​ም​ንም። 16እኔ ከዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ደ​ለሁ ከዓ​ለም አይ​ደ​ሉ​ምና። 17በእ​ው​ነ​ትህ ቀድ​ሳ​ቸው፤ ቃልህ እው​ነት ነውና። 18አንተ እኔን ወደ ዓለም እንደ ላክ​ኸኝ እኔም እነ​ር​ሱን ወደ ዓለም ላክ​ኋ​ቸው። 19እነ​ር​ሱም በእ​ው​ነት ቅዱ​ሳን ይሆኑ ዘንድ ስለ እነ​ርሱ እኔ ራሴን እቀ​ድ​ሳ​ለሁ።
20“የም​ለ​ም​ን​ህም ስለ እነ​ዚህ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ በቃ​ላ​ቸው ስለ​ሚ​ያ​ም​ኑ​ብ​ኝም ነው እንጂ፤ 21ሁሉም አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አንተ አብ በእኔ እን​ዳ​ለህ፥ እኔም በአ​ንተ እን​ዳ​ለሁ፥ እነ​ር​ሱም እንደ እኛ በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ፥ አን​ተም እንደ ላክ​ኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ። 22እኔም የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ክብር ሰጠ​ኋ​ቸው፤ እኛ አንድ እን​ደ​ሆን እነ​ር​ሱም እንደ እኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ። 23እኔ በእ​ነ​ርሱ እኖ​ራ​ለሁ፤ አን​ተም በእኔ፤ በአ​ንድ ፍጹ​ማን ይሆኑ ዘንድ፤ አን​ተም እንደ ላክ​ኸ​ኝና እንደ ወደ​ድ​ኸኝ#በግ​ሪኩ “... እኔን በወ​ደ​ድ​ኸኝ መጠን እነ​ር​ሱን እንደ ወደ​ድ​ሃ​ቸው ...” ይላል። እኔም እነ​ር​ሱን እንደ ወደ​ድ​ኋ​ቸው። 24አባት ሆይ፥ የሰ​ጠ​ኸኝ እነ​ዚህ እኔ ባለ​ሁ​በት አብ​ረ​ውኝ ይኖሩ ዘን​ድና የሰ​ጠ​ኸ​ኝን ክብ​ሬን ያዩ ዘንድ እወ​ድ​ዳ​ለሁ፤ ዓለም ሳይ​ፈ​ጠር ወድ​ደ​ኸ​ኛ​ልና። 25ጻድቅ አባት ሆይ፥ ዓለም አላ​ወ​ቀ​ህም፤ እኔ ግን ዐወ​ቅ​ሁህ፤ እነ​ዚ​ህም አንተ እንደ ላክ​ኸኝ ዐወቁ። 26እኔን የወ​ደ​ድ​ህ​በት ፍቅር በእ​ነ​ርሱ ይኖር ዘንድ፥ እኔም በእ​ነ​ርሱ እኖር ዘንድ ስም​ህን ነገ​ር​ኋ​ቸው፤ ደግ​ሞም እነ​ግ​ራ​ቸ​ዋ​ለሁ፤”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ