የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 19

19
አይ​ሁድ ጌታን እንደ ገረ​ፉ​ትና እንደ ተዘ​ባ​በ​ቱ​በት
1ከዚ​ህም በኋላ ጲላ​ጦስ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ይዞ ገረ​ፈው። 2ጭፍ​ሮ​ችም የእ​ሾህ አክ​ሊል ጐን​ጕ​ነው በራሱ ላይ ደፉ​በት፤ የቀይ ሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም አለ​በ​ሱት። 3ወደ እር​ሱም እየ​መጡ፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአ​ንተ ይሁን” ይሉት ነበር፤ በጥ​ፊም ይመ​ቱት ነበር። 4ጲላ​ጦ​ስም እን​ደ​ገና ወደ ውጭ ወጣና፥ “እነሆ፥ በእ​ርሱ ላይ አን​ዲት በደል ስን​ኳን ያገ​ኘ​ሁ​በት እን​ደ​ሌለ ታውቁ ዘንድ ወደ ውጭ አወ​ጣ​ላ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው። 5ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም የእ​ሾህ አክ​ሊል ደፍቶ፥ የቀይ ሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያም ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ፤ ጲላ​ጦ​ስም፥ “እነሆ፥ ሰው​ዬው” አላ​ቸው። 6ሊቃነ ካህ​ና​ትና ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ባዩት ጊዜ፥ “ስቀ​ለው! ስቀ​ለው!” እያሉ ጮሁ፤ ጲላ​ጦ​ስም፥ “እና​ንተ ራሳ​ችሁ ውሰ​ዱና ስቀ​ሉት፤ እኔስ በእ​ርሱ ላይ በደል አላ​ገ​ኘ​ሁ​በ​ትም” አላ​ቸው። 7አይ​ሁ​ድም መል​ሰው፥ “እኛ ሕግ አለን፤ እንደ ሕጋ​ች​ንም ሊሞት ይገ​ባል፤ ራሱን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ አድ​ር​ጎ​አ​ልና” አሉት። 8ጲላ​ጦ​ስም ይህን ነገር ሰምቶ እጅግ ፈራ።
ጲላ​ጦስ ዳግ​መኛ እንደ መረ​መ​ረው
9ደግ​ሞም ወደ ፍርድ አደ​ባ​ባይ ገባና ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን፥ “አንተ ከወ​ዴት ነህ?” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ግን ምንም አል​መ​ለ​ሰ​ለ​ትም። 10ጲላ​ጦ​ስም፥ “ለእ​ኔም አት​ነ​ግ​ረ​ኝ​ምን? ልሰ​ቅ​ልህ ሥል​ጣን እንደ አለኝ፥ ወይም ልፈ​ታህ ሥል​ጣን እን​ዳ​ለኝ፥ አታ​ው​ቅ​ምን?” አለው። 11ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “ከሰ​ማይ ካል​ተ​ሰ​ጠህ በቀር በእኔ ላይ አን​ዳች ሥል​ጣን የለ​ህም፤ ስለ​ዚህ ለአ​ንተ አሳ​ልፎ የሰ​ጠኝ ሰው ታላቅ ኀጢ​ኣት አለ​በት” አለው። 12ስለ​ዚ​ህም ጲላ​ጦስ ሊፈ​ታው ወድዶ ነበር፤ አይ​ሁድ ግን፥ “ይህን ከፈ​ታ​ኸው የቄ​ሣር ወዳጅ አይ​ደ​ለ​ህም፤ ራሱን ንጉሥ የሚ​ያ​ደ​ርግ ሰው ሁሉ በቄ​ሣር ላይ የሚ​ያ​ምፅ ነውና” ብለው ጮሁ።
ጲላ​ጦስ ወደ ሊቶ​ስ​ጥ​ሮስ እንደ አወ​ጣው
13ጲላ​ጦ​ስም ይህን ሰምቶ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን ወደ ውጭ አወ​ጣው፤ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስ​ጥም ገበታ ተብሎ በሚ​ጠ​ራው “ጸፍ​ጸፍ” በሚ​ሉት ቦታ ላይ በወ​ን​በር ተቀ​መጠ። 14የፋ​ሲ​ካም የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበር፤ ጊዜ​ዉም ስድ​ስት ሰዓት ያህል ነበር፤ ጲላ​ጦ​ስም አይ​ሁ​ድን፥ “እነሆ፥ ንጉ​ሣ​ችሁ” አላ​ቸው፤ 15እነ​ርሱ ግን፥ “አስ​ወ​ግ​ደው! ስቀ​ለው!” እያሉ ጮሁ። ጲላ​ጦ​ስም፥ “ንጉ​ሣ​ች​ሁን ልስ​ቀ​ለ​ውን?” አላ​ቸው፤ ሊቃነ ካህ​ና​ቱም፥ “ከቄ​ሣር በቀር ሌላ ንጉሥ የለ​ንም” ብለው መለሱ።
ጌታ​ችን ስለ መሰ​ቀሉ
16ከዚህ በኋላ ሊሰ​ቅ​ሉት አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም ተቀ​ብ​ለው ወሰ​ዱት። 17መስ​ቀ​ሉ​ንም ተሸ​ክሞ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ጎል​ጎታ ወደ ተባ​ለው ቀራ​ንዮ ወደ​ሚ​ባል ቦታ ወጣ። 18በዚ​ያም ሰቀ​ሉት፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አን​ዱን በቀኝ፥ አን​ዱ​ንም በግራ አድ​ር​ገው ሌሎች ሁለት ወን​በ​ዴ​ዎ​ችን ሰቀሉ፤ ኢየ​ሱ​ስ​ንም በመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ሰቀሉ። 19ጲላ​ጦ​ስም ጽሕ​ፈት ጽፎ በመ​ስ​ቀሉ ላይ አኖረ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም፥ “የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ የና​ዝ​ሬቱ ኢየ​ሱስ” የሚል ነበር። 20ከአ​ይ​ሁ​ድም ይህ​ቺን ጽሕ​ፈት ያነ​በ​ብ​ዋት ብዙ​ዎች ነበሩ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን የሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ለከ​ተማ ቅርብ ነበ​ርና፤ ጽሕ​ፈ​ቱም የተ​ጻ​ፈው በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ፥ በሮ​ማ​ይ​ስ​ጥና በግ​ሪክ ነበር። 21ሊቃነ ካህ​ና​ትም ጲላ​ጦ​ስን አሉት፥ “እርሱ ራሱ ‘እኔ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ነኝ’ እን​ዳለ እንጂ የአ​ይ​ሁድ ንጉሥ ብለህ አት​ጻፍ።” 22ጲላ​ጦ​ስም፥ “የጻ​ፍ​ሁ​ትን ጻፍሁ” ብሎ መለ​ሰ​ላ​ቸው።
ልብ​ሱን እንደ ተካ​ፈሉ
23ጭፍ​ሮ​ችም ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስን በሰ​ቀ​ሉት ጊዜ ልብ​ሶ​ቹን ወስ​ደው ከጭ​ፍ​ሮቹ ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አራት ክፍል አድ​ር​ገው መደ​ቡት፤ ቀሚ​ሱ​ንም ወሰዱ፤ ቀሚ​ሱም ከላይ ጀምሮ የተ​ሠራ ሥረ​ወጥ እንጂ የተ​ሰፋ አል​ነ​በ​ረም። 24#መዝ. 21፥18። እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ዕጣ እን​ጣ​ጣ​ልና ለደ​ረሰ ይድ​ረ​ሰው እንጂ አን​ቅ​ደ​ደው ተባ​ባሉ፤” ይህም “ልብ​ሶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ተካ​ፈሉ፤ በቀ​ሚ​ሴም ላይ ዕጣ ተጣ​ጣሉ” ያለው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው፤ ጭፍ​ሮ​ችም እን​ዲሁ አደ​ረጉ።
ጌታ እና​ቱን ለደቀ መዝ​ሙሩ አደራ ስለ መስ​ጠቱ
25በጌ​ታ​ችን በኢ​የ​ሱስ መስ​ቀል አጠ​ገ​ብም እናቱ፥ የእ​ና​ቱም እኅት፥ የቀ​ለ​ዮ​ጳም ሚስት ማር​ያም፥ መግ​ደ​ላ​ዊት ማር​ያ​ምም ቆመው ነበር። 26ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እና​ቱ​ንና የሚ​ወ​ደ​ውን ደቀ መዝ​ሙ​ሩን ቆመው ባያ​ቸው ጊዜ እና​ቱን፥ “አንች ሆይ፥ እነሆ፥ ልጅሽ” አላት። 27ከዚ​ህም በኋላ ደቀ መዝ​ሙ​ሩን፥ “እና​ትህ እነ​ኋት” አለው፤ ከዚ​ያ​ችም ሰዓት ጀምሮ ደቀ መዝ​ሙሩ ተቀ​ብሎ ወደ ቤቱ ወሰ​ዳት።
ስለ ጌታ​ችን ሞት
28 # መዝ. 68፥21፤ 21፥15። ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሁሉ እንደ ተፈ​ጸመ ባየ ጊዜ የመ​ጽ​ሐፉ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ “ተጠ​ማሁ” አለ። 29በዚ​ያም ሆም​ጣጤ የመ​ላ​በት ማሰሮ ነበር፤ እነ​ር​ሱም ሆም​ጣ​ጤ​ውን በሰ​ፍ​ነግ ሞል​ተው በስ​ምዛ ዘንግ ከአፉ አገ​ና​ኝ​ተው ጨመ​ቁት።#“ጨመ​ቁት” የሚ​ለው በግ​ሪኩ የለም። 30ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሆም​ጣ​ጤ​ውን ቀምሶ፥ “ሁሉ ተፈ​ጸመ” አለ፤ ራሱ​ንም አዘ​ን​ብሎ ነፍ​ሱን ሰጠ።
ከመ​ስ​ቀል ስለ መው​ረዱ
31አይ​ሁድ ግን የመ​ዘ​ጋ​ጀት ቀን ነበ​ርና፥ የዚ​ያች ሰን​በ​ትም ቀን ታላቅ ናትና “ሥጋ​ቸው በሰ​ን​በት በመ​ስ​ቀል ላይ አይ​ደር” አሉ፤ ጭን ጭና​ቸ​ው​ንም ሰብ​ረው ያወ​ር​ዷ​ቸው ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ኑት። 32ጭፍ​ሮ​ችም መጥ​ተው ከእ​ርሱ ጋር የተ​ሰ​ቀ​ሉ​ትን የአ​ን​ደ​ኛ​ው​ንና የሁ​ለ​ተ​ኛ​ውን ጭኖች ሰበሩ። 33ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ሄደው ፈጽሞ እንደ ሞተ ባዩ ጊዜ ጭኑን አል​ሰ​በ​ሩም። 34ነገር ግን ከጭ​ፍ​ሮቹ አንዱ የቀኝ#በግ​ሪኩ “ቀኝ” አይ​ልም። ጎኑን በጦር ወጋው፤ ያን​ጊ​ዜም ከእ​ርሱ ደምና ውኃ ወጣ። 35ያየ​ውም መሰ​ከረ፤ ምስ​ክ​ር​ነ​ቱም እው​ነት ነው፤ እር​ሱም እና​ንተ ልታ​ምኑ እው​ነት እን​ደ​ሚ​ና​ገር ያው​ቃል። 36#ዘፀ. 12፥46፤ ዘኍ​. 9፥12፤ መዝ. 33፥20፤ ዘካ. 11፥10፤ ራእ. 1፥7። ይህ ሁሉ የሆ​ነው “ከእ​ርሱ ዐፅ​ሙን አት​ስ​በሩ” ያለው የመ​ጽ​ሐፍ ቃል ይፈ​ጸም ዘንድ ነው። 37ሌላ​ዉም መጽ​ሐፍ ደግሞ“ የወ​ጉ​ትን ያዩ​ታል” ይላል።
ወደ መቃ​ብር ስለ መው​ረዱ
38ከዚ​ህም በኋላ አይ​ሁ​ድን ስለ​ፈራ በስ​ውር የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ደቀ መዝ​ሙር የነ​በ​ረው የአ​ር​ማ​ት​ያስ ሰው ዮሴፍ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ይወ​ስድ ዘንድ ጲላ​ጦ​ስን ለመ​ነው፤ ጲላ​ጦ​ስም ፈቀ​ደ​ለት። እር​ሱም ሄዶ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወሰደ። 39#ዮሐ. 3፥1-2። ቀድሞ በሌ​ሊት ወደ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ሄዶ የነ​በ​ረው ኒቆ​ዲ​ሞ​ስም መጣ፤ ቀብ​ተ​ውም የሚ​ቀ​ብ​ሩ​በ​ትን መቶ ወቄት የከ​ር​ቤና የሬት ቅል​ቅል ሽቶ አመጣ። 40እንደ አይ​ሁድ አገ​ና​ነዝ ሥር​ዐ​ትም የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወስ​ደው ከሽቱ ጋር በበ​ፍታ ገነ​ዙት። 41በዚ​ያም በተ​ሰ​ቀ​ለ​በት ቦታ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ነበር፤ በዚያ የአ​ት​ክ​ልት ስፍራ ውስ​ጥም በው​ስጡ ሰው ያል​ተ​ቀ​በ​ረ​በት አዲስ መቃ​ብር ነበር። 42ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም በዚያ ቀበ​ሩት፤ ለአ​ይ​ሁድ የመ​ሰ​ና​ዳት ቀን ነበ​ርና፤ መቃ​ብ​ሩም ለሰ​ቀ​ሉ​በት ቦታ ቅርብ ነበር።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ