የዮሐንስ ወንጌል 2
2
በቃና ዘገሊላ ስለ ተደረገው ሰርግ
1በሦስተኛውም ቀን የገሊላ ክፍል በምትሆን በቃና ሰርግ ሆነ፤ የጌታችን የኢየሱስ እናትም በዚያ ነበረች። 2ጌታችን ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ ታደሙ።
ስለ እናቱ ምልጃ
3የወይን ጠጃቸውም ባለቀ ጊዜ እናቱ ጌታችን ኢየሱስን፥ “የወይን ጠጅ እኮ የላቸውም” አለችው። 4ጌታችን ኢየሱስም፥ “አንቺ ሆይ ካንቺ ጋር ምን አለኝ? ጊዜዬ ገና አልደረሰም” አላት። 5እናቱም ለአሳላፊዎቹ፥ “የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ” አለቻቸው።
ስለ መጀመሪያው ተአምር
6በዚያም እንደ አይሁድ ልማድ የሚያነጹባቸው ስድስት የድንጋይ ጋኖች ነበሩ፤ ከእነርሱም እያንዳንዱ ሁለት ወይም ሦስት እንስራ ይይዙ ነበር። 7ጌታችን ኢየሱስም፥ “ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው” አላቸው፤ እስከ አፋቸውም እስከ ላይ ሞሉአቸው። 8“አሁንም ቅዱና ወስዳችሁ ለአሳዳሪው ስጡት” አላቸው፤ ወስደውም ሰጡት። 9አሳዳሪውም ያን የወይን ጠጅ የሆነውን ውኃ ቀምሶ አደነቀ፤#“አደነቀ” የሚለው በግሪኩ የለም። ከወዴት እንደ መጣም አላወቀም፤ የቀዱት አሳላፊዎች ግን የወይን ጠጅ የሆነውን ያን ውኃ ያውቁ ነበር። ውኃዉን የሞሉ እነርሱ ነበሩና። 10አሳዳሪውም ሙሽራውን ጠርቶ፥ “ሰው ሁሉ መልካሙን የወይን ጠጅ አስቀድሞ ያጠጣል፤ ከጠገቡ በኋላም ተርታውን ያመጣል፤ አንተ ግን መልካሙን የወይን ጠጅ እስካሁን አቈየህ” አለው። 11ጌታችን ኢየሱስም በቃና ዘገሊላ ያደረገው የተአምራት መጀመሪያ ይህ ነው፤ ክብሩንም ገለጠ፤ ደቀ መዛሙርቱም አመኑበት።
ወደ ኢየሩሳሌም ስለ መውጣቱ
12 #
ማቴ. 4፥13። ከዚህም በኋላ እርሱና እናቱ፥ ወንድሞቹና ደቀ መዛሙርቱም ወደ ቅፍርናሆም ወረዱ፤ በዚያም ብዙ ያይደለ ጥቂት ቀን ተቀመጡ። 13#ዘፀ. 12፥1-27። የአይሁድም የፋሲካቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ። 14በቤተ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን፥ ርግቦችንም የሚሸጡትን፥ ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ። 15የገመድም ጅራፍ አበጀ፤ በጎችንና በሬዎችን፥ ሁሉንም ከቤተ መቅደስ አስወጣ፤ የለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ። 16ርግብ ሻጮችንም፥ “ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ” አላቸው። 17#መዝ. 68፥9። ደቀ መዛሙርቱም፥ “የቤትህ ቅናት በላኝ” የሚል ቃል ተጽፎ እንዳለ ዐሰቡ።
ስለ መሞቱና ስለ መነሣቱ
18አይሁድም መልሰው፥ “ይህን የምታደርግ ምን ምልክት ታሳያለህ?” አሉት። 19#ማቴ. 26፥61፤ 27፥40፤ ማር. 14፥58፤ 15፥29። ጌታችን ኢየሱስም፥ “ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፤ በሦስተኛውም ቀን አነሣዋለሁ” ብሎ መለሰላቸው። 20አይሁድም፥ “ይህ ቤተ መቅደስ በአርባ ስድስት ዓመት ተሠራ፤ አንተስ በሦስት ቀኖች ውስጥ ታነሣዋለህን?” አሉት። 21እርሱ ግን ይህን የተናገረው ቤተ መቅደስ ስለ ተባለ ሰውነቱ ነበር። 22ከሙታን በተነሣ ጊዜም ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ እንደ ነገራቸው ዐሰቡ፤ በመጻሕፍት ቃልና ጌታችን ኢየሱስ በነገራቸውም ነገር አመኑ።
በበዓሉ ውስጥ ብዙዎቹ ስለ ማመናቸው
23ጌታችን ኢየሱስም በፋሲካ በዓል በኢየሩሳሌም ሳለ ብዙ ሰዎች ያደረገውን ተአምራት ባዩ ጊዜ በስሙ አመኑ። 24እርሱ ጌታችን ኢየሱስ ግን አያምናቸውም ነበር፤ ሁሉን እያንዳንዱን ያውቀዋልና። 25የሰውንም ግብሩን ሊነግሩት አይሻም፤ እርሱ በሰው ያለውን ያውቅ ነበርና።
Currently Selected:
የዮሐንስ ወንጌል 2: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ