የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 21:15-17

የዮ​ሐ​ንስ ወን​ጌል 21:15-17 አማ2000

ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ፦ ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስን፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ከእ​ነ​ዚህ ይልቅ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “በጎ​ችን ጠብቅ” አለው። ዳግ​መ​ኛም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ እር​ሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “ጠቦ​ቶ​ችን አሰ​ማራ” አለው። ሦስ​ተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስም​ዖን ሆይ፥ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ጴጥ​ሮ​ስም ሦስት ጊዜ ትወ​ደ​ኛ​ለ​ህን? ስላ​ለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታው​ቃ​ለህ፤ እኔም እን​ደ​ም​ወ​ድህ አንተ ታው​ቃ​ለህ” አለው፤ “እን​ኪ​ያስ ግል​ገ​ሎ​ችን ጠብቅ” አለው።