ምሳም ከበሉ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ፦ ስምዖን ጴጥሮስን፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ከእነዚህ ይልቅ ትወደኛለህን?” አለው፤ እርሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “በጎችን ጠብቅ” አለው። ዳግመኛም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ እርሱም፥ “አዎን፥ ጌታዬ ሆይ፥ እኔ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “ጠቦቶችን አሰማራ” አለው። ሦስተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ ጴጥሮስም ሦስት ጊዜ ትወደኛለህን? ስላለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እኔም እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “እንኪያስ ግልገሎችን ጠብቅ” አለው። “እውነት እውነት እልሃለሁ፤ አንተ ጐልማሳ ሳለህ በገዛ እጅህ ወገብህን ታጥቀህ ወደ ወደድኸው ትሄድ ነበር፤ በሸመገልህ ጊዜ ግን እጆችህን ትዘረጋለህ፤ ወገብህንም ሌላ ያስታጥቅሃል፤ ወደማትወደውም ይወስድሃል።” በምን ሞት እግዚአብሔርን ያከብር ዘንድ እንዳለው ሲያመለክት ይህን ተናገረ፤ ይህንም ብሎ ተከተለኝ አለው።
የዮሐንስ ወንጌል 21 ያንብቡ
ያዳምጡ የዮሐንስ ወንጌል 21
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 21:15-19
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች