ከሁለት ቀንም በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ከዚያ ወጥቶ ወደ ገሊላ ሄደ። ነቢይ በገዛ ሀገሩ እንደማይከብር እርሱ ራሱ ጌታችን ኢየሱስ መሰከረ። ወደ ገሊላም ደግሞ በገባ ጊዜ ገሊላውያን ሁሉ ተቀበሉት፤ እነርሱ ለበዓል ሄደው ስለ ነበር በበዓሉ ቀን በኢየሩሳሌም ያደረገውን ተአምር አይተው ነበርና። ጌታችን ኢየሱስም ውኃውን የወይን ጠጅ ወደ አደረገበት የገሊላ ክፍል ወደምትሆን ወደ ቃና ዳግመኛ ሄደ። በቅፍርናሆም ልጁ የታመመበት የንጉሥ ወገን የሆነ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ ሄደ፤ ሊሞት ቀርቦ ነበርና ወርዶ ልጁን ያድንለት ዘንድ ለመነው፤ ጌታችን ኢየሱስም፥ “ምልክትንና ድንቅ ሥራን ካላያችሁ አታምኑም” አለው። ያም የንጉሥ ወገን የሆነ ሰው፥ “አቤቱ፥ ልጄ ሳይሞት ፈጥነህ ውረድ” አለው። ጌታችን ኢየሱስም፥ “ሂድ፤ ልጅህስ ድኖአል” አለው፤ ያም ሰው፦ ጌታችን ኢየሱስ በነገረው ቃል አምኖ ሄደ። ሲወርድም አገልጋዮቹ ተቀበሉትና፥ “ልጅህስ ድኖአል” ብለው ነገሩት። የዳነባትን ሰዓቷንም ጠየቃቸው፤ “ትናንትና በሰባት ሰዓት ንዳዱ ተወው” አሉት። አባቱም፥ ጌታችን ኢየሱስ፥ “ልጅህ ድኖአል” ባለበት ሰዓት እንደ ሆነች ዐወቀ፤ እርሱም፥ ቤተ ሰቦቹም ሁሉ አመኑ።
የዮሐንስ ወንጌል 4 ያንብቡ
ያዳምጡ የዮሐንስ ወንጌል 4
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: የዮሐንስ ወንጌል 4:43-53
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች