የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 10

10
አሞ​ራ​ው​ያን በእ​ስ​ራ​ኤል እንደ ተሸ​ነፉ
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ#ዕብ. “አዶ​ኒ​ጼ​ዴቅ” ይላል። ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ፥ ፈጽ​ሞም እን​ዳ​ጠ​ፋት፥ በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም ያደ​ረ​ገ​ውን እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረገ፥ የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ሰላም እን​ዳ​ደ​ረጉ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥ 2ገባ​ዖን ከመ​ን​ግ​ሥ​ታት ከተ​ሞች እንደ አን​ዲቱ ታላቅ ከተማ ስለ​ሆ​ነች፥ ከጋ​ይም ስለ በለ​ጠች፥#“ከጋ​ይም ስለ በለ​ጠች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ሰዎ​ች​ዋም ሁሉ ኀያ​ላን ስለ ነበሩ እጅግ ፈራ። 3ስለ​ዚ​ህም የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ወደ ኬብ​ሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የር​ሙት ንጉ​ሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉ​ሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶ​ላም ንጉ​ሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥ 4“ወደ እኔ ኑ፤ ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ጋር ሰላም አድ​ር​ገ​ዋ​ልና ገባ​ዖ​ንን ለመ​ው​ጋት አግ​ዙኝ” አለ። 5አም​ስ​ቱም የኢ​ያ​ቡ​ሴ​ዎን#ዕብ. “አሞ​ራ​ው​ያን” ይላል። ነገ​ሥት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ የኬ​ብ​ሮን ንጉሥ፥ የየ​ር​ሙት ንጉሥ፥ የላ​ኪስ ንጉሥ፥ የአ​ዶ​ላም ንጉሥ፥ ከሠ​ራ​ዊ​ቶ​ቻ​ቸው ሁሉ ጋር ተሰ​ብ​ስ​በው ወጡ፤ ከገ​ባ​ዖ​ንም ጋር ሊጋ​ጠሙ ከበ​ቡ​አት።
6የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ ጌል​ገላ ልከው፥ “ባሪ​ያ​ዎ​ች​ህን ለመ​ር​ዳት እጅ​ህን አት​መ​ልስ፤ በተ​ራ​ራ​ማው ሀገር የሚ​ኖሩ የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ነገ​ሥት ሁሉ ተሰ​ብ​ስ​በ​ው​ብ​ና​ልና ፈጥ​ነህ ወደ እኛ ውጣ፤ አድ​ነ​ንም፤ ርዳ​ንም፤” አሉት። 7ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር የነ​በሩ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ፥ ጽኑ​ዓን ኀያ​ላ​ኑም ሁሉ ከጌ​ል​ጌላ ወጡ። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን፥ “በእ​ጅህ አሳ​ልፌ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለ​ሁና አት​ፍ​ራ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አንድ ሰው በፊ​ትህ የሚ​ተ​ርፍ የለም፤” አለው። 9ኢያ​ሱም ከጌ​ል​ገላ ሌሊ​ቱን ሁሉ ገሥ​ግሦ በድ​ን​ገት ደረ​ሰ​ባ​ቸው። 10እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ራ​ኤል ፊት አስ​ደ​ነ​ገ​ጣ​ቸው፤ በገ​ባ​ዖ​ንም ታላቅ መም​ታት መታ​ቸው። 11ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ፊት እየ​ሸሹ በቤ​ት​ሖ​ሮን ቍል​ቍ​ለት ሲወ​ርዱ፥ ወደ ዓዜ​ቃና ወደ መቄዳ እስ​ኪ​ደ​ርሱ ድረስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ታላ​ላቅ የበ​ረዶ ድን​ጋይ አወ​ረ​ደ​ባ​ቸ​ውና ሞቱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሰ​ይፍ ከገ​ደ​ሉ​አ​ቸው ይልቅ በበ​ረዶ ድን​ጋይ የሞ​ቱት በለጡ።
12ያን ጊዜም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እጅ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እርሱ በገ​ባ​ዖን እነ​ር​ሱን ባጠ​ፋ​በት፥ እነ​ር​ሱም ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት በጠ​ፉ​በት ቀን ኢያሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጋር ተነ​ጋ​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “በገ​ባ​ዖን ላይ ፀሐይ ትቁም፤ በኢ​ሎ​ንም ሸለቆ ጨረቃ፤” 13እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጠላ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን እስ​ኪ​ያ​ጠፋ ድረስ ፀሐ​ይና ጨረቃ በየ​ቦ​ታ​ቸው ቆሙ። ይህም እነሆ በዚህ መጽ​ሐፍ በጊ​ዜው ተጻፈ።#ዕብ. “ይህስ በያ​ሻር መጽ​ሐፍ የተ​ጻፈ አይ​ደ​ለ​ምን” ይላል። ፀሐ​ይም በሰ​ማይ መካ​ከል ቆመች፤ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል አል​ጠ​ለ​ቀ​ችም። 14እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ይዋጋ ነበ​ርና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ውን ቃል የሰ​ማ​በት እን​ደ​ዚያ ያለ ቀን ከዚ​ያም በፊት ከዚ​ያም በኋላ አል​ነ​በ​ረም።
15ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ሰፈ​ራ​ቸው ወደ ጌል​ገላ ተመ​ለሱ።
ኢያሱ አም​ስ​ቱን አሞ​ራ​ው​ያን ነገ​ሥት እንደ ገደለ
16እነ​ዚ​ህም አም​ስት ነገ​ሥት ሸሽ​ተው በመ​ቄዳ ዋሻ ተሸ​ሸጉ። 17ለኢ​ያ​ሱም “አም​ስቱ ነገ​ሥት በመ​ቄዳ ዋሻ ተሸ​ሽ​ገው ተገኙ፤” ብለው ነገ​ሩት። 18ኢያ​ሱም እን​ዲህ አለ፥ “ወደ ዋሻው አፍ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ አን​ከ​ባ​ል​ላ​ችሁ፥ ይጠ​ብ​ቋ​ቸው ዘንድ ሰዎ​ችን በዚያ አኑሩ፤ 19እና​ንተ ግን አት​ዘ​ግዩ፤ ጠላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም እስከ መጨ​ረ​ሻው ተከ​ታ​ት​ላ​ችሁ ያዙ​አ​ቸው፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ቸ​ዋ​ልና ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ይ​ገቡ ከል​ክ​ሉ​አ​ቸው፤” አለ። 20እስ​ኪ​ጠ​ፉም ድረስ ኢያ​ሱና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በታ​ላቅ መም​ታት መም​ታ​ታ​ቸ​ውን በፈ​ጸሙ ጊዜ፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ያመ​ለ​ጡት ወደ ተመ​ሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥ 21ሕዝቡ ሁሉ ኢያሱ ወደ ሰፈ​ረ​በት ወደ መቄዳ በደ​ኅና ተመ​ለሱ፤ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ ምላ​ሱን ማን​ቀ​ሳ​ቀስ የደ​ፈረ ማንም ሰው የለም።
22ኢያ​ሱም፥ “የዋ​ሻ​ውን አፍ ክፈቱ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም አም​ስት ነገ​ሥት ከዋ​ሻው ወደ እኔ አው​ጡ​አ​ቸው” አለ። 23እን​ዲ​ህም አደ​ረጉ፤ አም​ስ​ቱ​ንም ነገ​ሥት፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ንጉሥ፥ የኬ​ብ​ሮ​ን​ንም ንጉሥ፥ የየ​ር​ሙ​ት​ንም ንጉሥ፥ የላ​ኪ​ስ​ንም ንጉሥ፥ የአ​ዶ​ላ​ም​ንም ንጉሥ ከዋ​ሻው ወደ እርሱ አወ​ጡ​አ​ቸው። 24እነ​ዚ​ያ​ንም ነገ​ሥት ወደ ኢያሱ ባመ​ጡ​አ​ቸው ጊዜ ኢያሱ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሰዎች ሁሉ ጠራ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር የሄ​ዱ​ትን የተ​ዋ​ጊ​ዎ​ችን አለ​ቆች “ቅረቡ፤ በእ​ነ​ዚ​ህም ነገ​ሥት አን​ገት ላይ እግ​ራ​ች​ሁን አኑሩ” አላ​ቸው። ቀረ​ቡም በአ​ን​ገ​ታ​ቸ​ውም ላይ እግ​ራ​ቸ​ውን አኖሩ። 25ኢያ​ሱም፥ “በም​ት​ወ​ጉ​አ​ቸው በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ችሁ ሁሉ ላይ እን​ዲሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ር​ጋ​ልና አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግጡ፤ ጽኑ፤ አይ​ዞ​አ​ችሁ” አላ​ቸው። 26ከዚ​ህም በኋላ መት​ተው ገደ​ሉ​አ​ቸው፤ በአ​ም​ስ​ቱም ዛፎች ላይ ሰቀ​ሉ​አ​ቸው፤ እስከ ማታም ደረስ በዛ​ፎቹ ላይ ተሰ​ቅ​ለው ቈዩ። 27ፀሐ​ይም ልት​ገባ በቀ​ረ​በች ጊዜ ኢያሱ አዘዘ፤ ከዛ​ፎ​ችም አወ​ረ​ዱ​አ​ቸው፤ ተሸ​ሽ​ገ​ውም በነ​በ​ሩ​በት ዋሻ ጣሉ​አ​ቸው፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዋ​ሻው አፍ ታላ​ላቅ ድን​ጋይ ተደ​ር​ጎ​አል።
ኢያሱ ሌሎች ከተ​ሞ​ችን እንደ ያዘ
28በዚ​ያም ቀን መቄ​ዳን ያዟት፤ እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋ​ንም በሰ​ይፍ ስለት ገደሉ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽ​መው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ሩም፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረጉ በመ​ቄዳ ንጉሥ አደ​ረጉ።
29ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከመ​ቄዳ ወደ ልብና አለፉ፤ ልብ​ና​ንም ወጉ። 30እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እር​ስ​ዋ​ንና ንጉ​ሥ​ዋን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጠ፤ እር​ስ​ዋ​ንም በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መታ፤ በእ​ር​ስ​ዋም አን​ዱን ስንኳ አላ​ስ​ቀ​ረም፤ በኢ​ያ​ሪ​ኮም ንጉሥ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው በል​ብና ንጉሥ አደ​ረገ።
31ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከል​ብና ወደ ላኪስ አለፉ፤ በዙ​ሪ​ያ​ዋም ሰፈሩ፤ ከበ​ቡ​አ​ትም። 32እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ላኪ​ስን በእ​ስ​ራ​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ቀን ያዙ​አት፤ በል​ብ​ናም እን​ዳ​ደ​ረ​ጉት ሁሉ፥ እር​ስ​ዋን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ​አ​ቸው።
33በዚያ ጊዜም የጋ​ዜር ንጉሥ ኤላም ላኪ​ስን ለመ​ር​ዳት ወጣ፤ ኢያ​ሱም አንድ ስንኳ ሳይ​ቀር በሰ​ይፍ ስለት እር​ሱ​ንና ሕዝ​ቡን መታ፤ የዳ​ነም፥ ያመ​ለ​ጠም የለም።
34ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከላ​ኪስ ወደ አዶ​ላም አለፉ፤ ከበ​ቡ​አ​ትም፤ ወጉ​አ​ትም፤ 35እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በእ​ስ​ር​ኤል እጅ አሳ​ልፎ ሰጣት፤ በዚ​ያም ቀን ያዙ​አት፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አት፤ በላ​ኪ​ስም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ፥ በእ​ር​ስዋ ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
36ኢያ​ሱም ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ከአ​ዶ​ላም ወደ ኬብ​ሮን ወጡ፤ ወጉ​አ​ትም፤ ያዙ​አ​ትም፤ 37እር​ስ​ዋ​ንም፥ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም፥ ከተ​ሞ​ች​ዋ​ንም ሁሉ፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ በሰ​ይፍ ስለት መቱ፤ በአ​ዶ​ላም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው ሁሉ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም ፤ እር​ስ​ዋ​ንም፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ።
38ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ዳቤር ተመ​ለሱ፤ ወጉ​አ​ትም፤ 39እር​ስ​ዋ​ንም፥ ንጉ​ሥ​ዋ​ንም፥ ከተ​ሞ​ች​ዋ​ንም ያዙ፤ በሰ​ይ​ፍም ስለት መቱ​አ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ውስጥ ያሉ​ትን ነፍ​ሳት ሁሉ ፈጽ​መው አጠፉ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ በኬ​ብ​ሮ​ንና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረ​ገው እን​ዲሁ በዳ​ቤ​ርና በን​ጉ​ሥዋ አደ​ረገ።
40እን​ዲ​ሁም ኢያሱ ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ፥ ተራ​ራ​ማ​ውን ሀገር፥ ደቡ​ቡ​ንም፥ ቆላ​ው​ንም፥ ቍል​ቍ​ለ​ቱ​ንም፥ ንጉ​ሦ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሁሉ መታ፤ ማን​ንም አላ​ስ​ቀ​ረም፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘ​ውም ነፍስ ያለ​በ​ትን ሁሉ ፈጽሞ አጠፋ። 41ኢያ​ሱም ከቃ​ዴስ በርኔ እስከ ጋዛ ድረስ፥ የጎ​ሶ​ም​ንም ምድር ሁሉ እስከ ገባ​ዖን ድረስ መታ። 42የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለእ​ስ​ራ​ኤል ስለ ተዋ​ጋ​ላ​ቸው ኢያሱ እነ​ዚ​ህን ነገ​ሥ​ታት ሁሉ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም በአ​ንድ ጊዜ ያዘ። 43ኢያ​ሱም፥ ከእ​ር​ሱም ጋር እስ​ራ​ኤል ሁሉ ወደ ሰፈሩ ወደ ጌል​ገላ ተመ​ለሱ።#ምዕ. 10 ቍጥር 43 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ