የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 24

24
ኢያሱ በሴሎ ያደ​ረ​ገው የመ​ጨ​ረሻ ንግ​ግር
1ኢያ​ሱም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ነገድ ሁሉ ወደ ሴሎ ሰበ​ሰበ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ሽማ​ግ​ሌ​ዎች፥ አለ​ቆ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ጸሓ​ፊ​ዎ​ቻ​ቸ​ው​ንም፥ ፈራ​ጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም ጠራ​ቸው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት አቆ​ማ​ቸው። 2ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ ሁሉ እን​ዲህ አለ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ‘አባ​ቶ​ቻ​ችሁ፥ የአ​ብ​ር​ሃ​ምና የና​ኮር አባት ታራ፥ አስ​ቀ​ድ​መው በወ​ንዝ ማዶ ተቀ​መጡ፤ ሌሎ​ች​ንም አማ​ል​ክት አመ​ለኩ። 3አባ​ታ​ች​ሁ​ንም አብ​ር​ሃ​ምን ከወ​ንዝ ማዶ ወስጄ በከ​ነ​ዓን ምድር ሁሉ መራ​ሁት፤ ዘሩ​ንም አበ​ዛሁ፤ ይስ​ሐ​ቅ​ንም ሰጠ​ሁት። 4ለይ​ስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዔሳ​ውን ሰጠ​ሁት፤ ለዔ​ሳ​ውም የሴ​ይ​ርን ተራራ ርስት አድ​ርጌ ሰጠ​ሁት፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረ​ቱም፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም መከራ አጸ​ኑ​ባ​ቸው። 5ሙሴ​ንና አሮ​ን​ንም ላክሁ፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ ስላ​ደ​ረ​ጉት ነገር ግብ​ፃ​ው​ያ​ንን ቀሠ​ፍ​ኋ​ቸው፤ 6ከዚ​ያም በኋላ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን ከግ​ብፅ አወ​ጣ​ኋ​ቸው፤ ወደ ባሕ​ሩም ገባ​ችሁ፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁን በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችና በፈ​ረ​ሶች እስከ ኤር​ትራ ባሕር ድረስ ተከ​ተ​ሉ​አ​ቸው። 7ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጮ​ሃ​ችሁ ጊዜ በእ​ና​ን​ተና በግ​ብ​ፃ​ው​ያን መካ​ከል ደመ​ና​ንና ጭጋ​ግን አደ​ረ​ግሁ፤ ባሕ​ሩ​ንም መለ​ስ​ሁ​ባ​ቸው፤ አሰ​ጠ​ማ​ቸ​ውም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በግ​ብፅ ያደ​ረ​ግ​ሁ​ትን አዩ፤ በም​ድረ በዳም ብዙ ጊዜ ተቀ​መ​ጣ​ችሁ። 8በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ተቀ​መ​ጡት ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን ምድ​ርም ወሰ​ድ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ተዋጉ፤ ሙሴም ተዋ​ጋ​ቸው፤ አሳ​ል​ፌም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ምድ​ራ​ቸ​ው​ንም ወረ​ሳ​ችሁ፤ ከፊ​ታ​ች​ሁም አጠ​ፋ​ኋ​ቸው። 9የሞ​ዓ​ብም ንጉሥ የሴ​ፎር ልጅ ባላቅ ተነ​ሥቶ ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጋ፤ እን​ዲ​ረ​ግ​ማ​ች​ሁም የቢ​ዖ​ርን ልጅ በለ​ዓ​ምን ልኮ አስ​ጠ​ራው። 10እኔ ግን ላጠ​ፋ​ችሁ አል​ወ​ደ​ድ​ሁም፤ መባ​ረ​ክ​ንም ባረ​ክ​ኋ​ችሁ፤ ከእ​ጁም አዳ​ን​ኋ​ችሁ፤ 11ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገ​ራ​ችሁ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም መጣ​ችሁ፤ የኢ​ያ​ሪ​ኮም ሰዎች፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊው፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊው፥ ከነ​ዓ​ና​ዊው፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊው፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊው፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው ተዋ​ጉ​አ​ችሁ፥ አሳ​ል​ፌም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ቸው። 12በፊ​ታ​ች​ሁም ተርብ ሰደ​ድሁ፤ በሰ​ይ​ፍ​ህም፥ በቀ​ስ​ት​ህም ሳይ​ሆን ዐሥራ ሁለ​ቱን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ነገ​ሥ​ታት ከፊ​ታ​ችሁ አሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው። 13ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ት​ንም ምድር፥ ያል​ሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውም፤ ካል​ተ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከወ​ይ​ንና ከወ​ይራ በላ​ችሁ።’
14“አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት፤ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነ​ትም አም​ል​ኩት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በወ​ንዝ ማዶ፥ በግ​ብ​ፅም ውስጥ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አም​ልኩ። 15እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታመ​ልኩ ዘንድ ባት​ወ​ድዱ ግን፥ አባ​ቶ​ቻ​ችሁ በወ​ንዝ ማዶ ሳሉ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን አማ​ል​ክት፥ ወይም በም​ድ​ራ​ቸው ያላ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውን የአ​ሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን አማ​ል​ክት ታመ​ልኩ እንደ ሆነ፥ የም​ታ​መ​ል​ኩ​ትን ዛሬ ምረጡ። እኔና ቤቴ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን፤ እርሱ ቅዱስ ነውና።”
16ሕዝ​ቡም መል​ሰው እን​ዲህ አሉ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትተን ሌሎች አማ​ል​ክ​ትን ማም​ለክ ከእኛ ይራቅ፤ 17እኛ​ንና አባ​ቶ​ቻ​ች​ንን ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣን፥ በዐ​ይ​ና​ች​ንም ፊት እነ​ዚ​ያን ታላ​ላቅ ተአ​ም​ራት ያደ​ረገ፥ በሄ​ድ​ን​ባ​ትም መን​ገድ ሁሉ፥ ባለ​ፍ​ን​ባ​ቸ​ውም አሕ​ዛብ ሁሉ መካ​ከል የጠ​በ​ቀን፥ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነውና። 18እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አሕ​ዛ​ብን ሁሉ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም የተ​ቀ​መ​ጡ​ትን አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን ከፊ​ታ​ችን አሳ​ደደ፤ ስለ​ዚህ እርሱ አም​ላ​ካ​ችን ነውና እኛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን።”
19ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “እርሱ ቅዱስ አም​ላክ ነውና፥ እር​ሱም ቀና​ተኛ አም​ላክ ነውና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ማም​ለክ አት​ች​ሉም፤ ብታ​ስ​ቀ​ኑት መተ​ላ​ለ​ፋ​ች​ሁ​ንና ኀጢ​አ​ታ​ች​ሁን ይቅር አይ​ልም። 20እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትታ​ችሁ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ መል​ካ​ምን ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ ፋንታ ተመ​ልሶ ክፉ ነገር ያደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋል፤ ያጠ​ፋ​ች​ሁ​ማል” አላ​ቸው። 21ሕዝ​ቡም ኢያ​ሱን፥ “እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን” አሉት። 22ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “እን​ድ​ታ​መ​ል​ኩት እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ መረ​ጣ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ምስ​ክ​ሮች ነን” አሉ። 23እር​ሱም፥ “አሁን እን​ግ​ዲህ በእ​ና​ንተ ዘንድ ያሉ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት አርቁ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅኑ” አላ​ቸው። 24ሕዝ​ቡም ኢያ​ሱን፥ “አም​ላ​ካ​ች​ንን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን፤ ቃሉ​ንም እን​ሰ​ማ​ለን” አሉት።
25በዚ​ያም ቀን ኢያሱ ከሕ​ዝቡ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ በሴ​ሎም#ዕብ. “በሴ​ኬም” ይላል። በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ድን​ኳን ፊት ሕግ​ንና ፍር​ድን ሰጣ​ቸው። 26ኢያ​ሱም ይህን ቃል ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ መጽ​ሐፍ ጻፈው፤ ኢያ​ሱም ታላ​ቁን ድን​ጋይ ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በነ​በ​ረ​ችው በአ​ሆማ ዛፍ በታች አቆ​ማት። 27ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ ሁሉ፥ “ይህች ድን​ጋይ በእ​ና​ንተ ላይ ምስ​ክር ናት፤ እር​ስዋ፥ ዛሬ እንደ ነገ​ራ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የተ​ባ​ለ​ውን ሁሉ ሰም​ታ​ለ​ችና በኋላ ዘመን አም​ላ​ኬን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ብት​ክ​ዱት ይህች ድን​ጋይ ምስ​ክር ትሆ​ን​ባ​ች​ኋ​ለች” አላ​ቸው። 28ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን አሰ​ና​በተ፤ ሁሉም ወደ​የ​ቦ​ታ​ቸው ገቡ።
የኢ​ያ​ሱና የአ​ል​ዓ​ዛር ሞት
29እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከዚህ ነገር በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ የነዌ ልጅ ኢያሱ ዕድ​ሜው መቶ ዐሥር ዓመት ሲሆ​ነው ሞተ። 30በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር በገ​ዓስ ተራራ በሰ​ሜን ባለ​ችው በር​ስቱ ዳርቻ በተ​ም​ና​ሴራ ቀበ​ሩት። በዚ​ያም ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በገ​ል​ገላ የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶ​ችን እር​ሱን በቀ​በ​ሩ​በት መቃ​ብር ከእ​ርሱ ጋር ቀበሩ፤ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ።#“በዚ​ያም ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች በገ​ል​ገላ የገ​ረ​ዘ​ባ​ቸ​ውን የድ​ን​ጋይ ባል​ጩ​ቶ​ችን እር​ሱን በቀ​በ​ሩ​በት መቃ​ብር ከእ​ርሱ ጋር ቀበሩ እስከ ዛሬም ድረስ በዚያ አሉ” የሚ​ለው በዕብ. የለም። 31ኢያሱ ባለ​በት ዘመን ሁሉ፥ ከኢ​ያ​ሱም በኋላ በነ​በ​ሩት ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ያደ​ረ​ገ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ሁሉ ባወ​ቁት በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ዘመን ሁሉ፥ እስ​ራ​ኤል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ለኩ።
32የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከግ​ብፅ ያወ​ጡ​ትን የዮ​ሴ​ፍን አፅም ያዕ​ቆብ በሰ​ቂማ ከሚ​ኖሩ ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን በመቶ በጎች በገ​ዛው ለዮ​ሴፍ ድርሻ አድ​ርጎ በሰ​ጠው እርሻ በአ​ንዱ ክፍል በሰ​ቂማ ቀበ​ሩት። 33የአ​ሮ​ንም ልጅ ሊቀ ካህ​ናቱ አል​ዓ​ዛር ሞተ፤ በተ​ራ​ራ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ሬም ሀገር ለልጁ ለፊ​ን​ሐስ በተ​ሰ​ጠ​ችው በጊ​ብ​ዓት መሬት ቀበ​ሩት። 34የዚ​ያን ጊዜ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይዘ​ዋት ሄዱ። ፊን​ሐ​ስም እስከ ሞተና በቦ​ታ​ቸው በጊ​ብ​ዓት እስከ ቀበ​ሩት ድረስ በአ​ባቱ በአ​ል​ዓ​ዛር ፋንታ ሊቀ ካህ​ናት ሆነ። 35የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ሁሉ ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና ወደ ቤታ​ቸው ገቡ። ከዚህ በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አስ​ጠ​ራ​ጢ​ን​ንና አስ​ጣ​ሮ​ትን፥ በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም የነ​በ​ሩ​ትን የአ​ሕ​ዛ​ብን አማ​ል​ክት አመ​ለኩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሞ​ዓብ ንጉሥ በኤ​ግ​ሎም እጅ ጣላ​ቸው፤ ዐሥራ ስም​ንት ዓመ​ትም ገዛ​ቸው።#ምዕ. 24 ቍ. 34 እና 35 በዕብ. የለም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ