የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 9

9
የገ​ባ​ዖን ሰዎች ኢያ​ሱን እን​ዳ​ታ​ለ​ሉት
1እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በተ​ራ​ራ​ማው በሜ​ዳ​ውም በታ​ላቁ ባሕር ዳር በሊ​ባ​ኖ​ስም ፊት ለፊት የነ​በሩ ነገ​ሥት ሁሉ፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊዉ፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ከነ​ዓ​ና​ዊ​ዉም፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉም፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊ​ዉም ይህን በሰሙ ጊዜ፥ 2ኢያ​ሱ​ንና እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰ​በ​ሰቡ።
3በገ​ባ​ዖን የሚ​ኖሩ ሰዎች ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር#ዕብ. “ኢያሱ” ይላል። በኢ​ያ​ሪ​ኮና በጋይ ያደ​ረ​ገ​ውን በሰሙ ጊዜ፥ 4እነ​ርሱ ደግሞ ተን​ኰል አድ​ር​ገው መጡ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ስንቅ ያዙ፤ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም#ዕብ. “በአ​ህ​ዮ​ቻ​ቸው” ይላል። ላይ አሮጌ ዓይ​በ​ትና ያረ​ጀና የተ​ቀ​ደደ የተ​ጠ​ቀ​መም የጠጅ ረዋት ተሸ​ከሙ። 5በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም ያደ​ረ​ጉት ጫማ ያረ​ጀና ማዘ​ቢ​ያው የተ​በ​ጣ​ጠሰ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ውም በላ​ያ​ቸው ያረጀ ነበረ፤ ለስ​ን​ቅም የያ​ዙት እን​ጀራ ሁሉ የደ​ረቀ፥ የሻ​ገ​ተና የተ​በ​ላሸ ነበረ። 6ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ጉባኤ ወደ ጌል​ገላ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥ​ተ​ናል፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ” አሉ። 7የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ምና​ል​ባት በመ​ካ​ከ​ላ​ችን የም​ት​ቀ​መጡ እንደ ሆነ እን​ዴ​ትስ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳን እና​ደ​ር​ጋ​ለን?” አሉ​አ​ቸው። 8ኢያ​ሱ​ንም፥ “እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ ነን፤ ከሩቅ ሀገ​ርም ነን”#“ከሩቅ ሀገ​ርም ነን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። አሉት። ኢያ​ሱም፥ “እና​ንተ እነ​ማን ናችሁ? ከወ​ዴ​ትስ መጣ​ችሁ?” አላ​ቸው። 9እነ​ር​ሱም አሉት፥ “በአ​ም​ላ​ክህ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪ​ያ​ዎ​ችህ መጥ​ተ​ናል፤ ዝና​ው​ንም፥ በግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ፥ 10በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶም በነ​በ​ሩት በሁ​ለቱ በአ​ሞ​ሬ​ዎን ነገ​ሥት በሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ በሴ​ዎን፥ በአ​ስ​ታ​ሮ​ትና በኤ​ድ​ራ​ይን በነ​በ​ረው በባ​ሳን ንጉሥ በዐግ ያደ​ረ​ገ​ውን ሁሉ ሰም​ተ​ናል። 11ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ንና የሀ​ገ​ራ​ችን ሰዎች ሁሉ፦ ለመ​ን​ገድ ስንቅ ያዙ፤ ልት​ገ​ና​ኙ​አ​ቸ​ውም ሂዱ፦ እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ቻ​ችሁ ነን፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ በሉ​አ​ቸው አሉን። 12ወደ እና​ንተ ለመ​ም​ጣት በተ​ነ​ሣ​ን​በት ቀን ይህን እን​ጀራ ትኩ​ሱን ለስ​ንቅ ከቤ​ታ​ችን ያዝ​ነው፤ አሁ​ንም እነሆ፥ ደር​ቆ​አል፤ ሻግ​ቶ​አ​ልም። 13እነ​ዚ​ህም የጠጅ ረዋ​ቶች አዲ​ሶች ሳሉ ሞላ​ን​ባ​ቸው፤ እነ​ሆም፥ አር​ጅ​ተው ተቀ​ድ​ደ​ዋል፤ መን​ገ​ዳ​ች​ንም እጅግ ስለ ራቀ​ብን እነ​ዚህ ልብ​ሶ​ቻ​ች​ንና ጫማ​ዎ​ቻ​ችን አር​ጅ​ተ​ዋል።” 14አለ​ቆ​ችም ከስ​ን​ቃ​ቸው ወሰዱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ጠ​የ​ቁም። 15ኢያ​ሱም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሰላም አደ​ረገ፤ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ተ​ዋ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ማሉ​ላ​ቸው።
16ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን ካደ​ረጉ ከሦ​ስት ቀን በኋላ ከቅ​ርብ እን​ደ​ሆ​ኑና በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰሙ። 17የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ተጕ​ዘው በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን#“በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ወደ ከተ​ሞ​ቻ​ቸው ደረሱ፤ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም ገባ​ዖን፥ ከፊራ፥ ብኤ​ሮ​ትና ኢያ​ሪም ነበሩ። 18የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ማሉ​ላ​ቸው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አል​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ውም። ማኅ​በ​ሩም ሁሉ በአ​ለ​ቆቹ ላይ አጕ​ረ​መ​ረሙ። 19አለ​ቆ​ቹም ሁሉ ለማ​ኅ​በሩ ሁሉ፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምለ​ን​ላ​ቸ​ዋል፤ ስለ​ዚ​ህም እን​ነ​ካ​ቸው ዘንድ ምንም አን​ች​ልም። 20ስለ​ማ​ል​ን​ላ​ቸው መሐላ ጥፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብን ይህን አና​ድ​ር​ግ​ባ​ቸው፤ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ተ​ዋ​ቸው፤ እን​ግ​ዛ​ቸ​ውም” አሉ​አ​ቸው። 21አለ​ቆ​ቹም “አዳ​ን​ና​ችሁ፤ ለማ​ኅ​በ​ሩም እን​ጨት ትቈ​ር​ጡና ውኃ ትቀዱ ዘንድ መደ​ብ​ና​ችሁ” አሉ​አ​ቸው። አለ​ቆ​ቹም እን​ዲሁ አዘ​ዙ​አ​ቸው።
22ኢያ​ሱም ጠርቶ፥ “እና​ንተ በመ​ካ​ከ​ላ​ችን የም​ት​ኖሩ ስት​ሆኑ፦ ‘ከእ​ና​ንተ እጅግ የራ​ቅን ነን’ ብላ​ችሁ ለምን አታ​ለ​ላ​ች​ሁን? 23አሁ​ንም የተ​ረ​ገ​ማ​ችሁ ሁኑ፤ ለእ​ኔም፥ ለአ​ም​ላ​ኬም እን​ጨት ቈራጭ፥ ውኃም ቀጂ የሆነ ባሪያ ከእ​ና​ንተ አይ​ጠ​ፋም” አላ​ቸው። 24መል​ሰ​ውም ኢያ​ሱን፥ “እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ#“እኛ ባሪ​ያ​ዎ​ችህ” የሚ​ለው በግ​እ​ዝና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። ምድ​ሪ​ቱን ሁሉ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ፥ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ኖ​ሩ​ትን ሁሉ ከፊ​ታ​ችሁ ያጠፋ ዘንድ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባሪ​ያ​ውን ሙሴን እን​ዳ​ዘዘ በእ​ው​ነት ሰም​ተ​ናል፤ ስለ​ዚ​ህም ከእ​ና​ንተ የተ​ነሣ ስለ ነፍ​ሳ​ችን እጅግ ፈራን፤ ይህ​ንም ነገር አድ​ር​ገ​ናል፤ 25አሁ​ንም እነሆ፥ በእ​ጃ​ችሁ ውስጥ ነን፤ እንደ ወደ​ዳ​ች​ሁና ደስ እን​ደ​ሚ​ላ​ችሁ አድ​ር​ጉ​ብን” አሉት፤#ዕብ. “በእ​ጅህ ውስጥ ነን ለዐ​ይ​ን​ህም መል​ካ​ምና ቅን የመ​ሰ​ለ​ውን ነገር አድ​ር​ግ​ብን አሉት” ይላል። 26ኢያ​ሱም እን​ዲሁ አደ​ረ​ገ​ባ​ቸው፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች እጅ አዳ​ና​ቸው፤ አል​ገ​ደ​ሉ​አ​ቸ​ው​ምም። 27በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ