ኦሪት ዘሌዋውያን 1
1
ስለሚቃጠል መሥዋዕት
1እግዚአብሔርም ከምስክሩ ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ ሲል ተናገረው፦ 2“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእናንተ ለእግዚአብሔር መባ የሚያቀርብ ሰው ቢኖር መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች ታቀርባላችሁ።
3“መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነት እንዲኖረው በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል። 4ተቀባይነት ይኖረው ዘንድ ስለ እርሱም ያስተሰርይለት ዘንድ እጁን በሚቃጠለው መሥዋዕት ራስ ላይ ይጭናል። 5በሬውንም በእግዚአብሔር ፊት ያርደዋል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን ያቀርባሉ፤ ደሙንም በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። 6የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ይገፍፈዋል፤ በየብልቱም ይቈርጠዋል። 7የካህኑም የአሮን ልጆች በመሠዊያው ላይ እሳት ያነድዳሉ፤ በእሳቱም ላይ ዕንጨት ይረበርባሉ፤ 8የአሮንም ልጆች ካህናቱ የተቈረጡትን ብልቶች፥ ራሱንም፥ ስቡንም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ይረበርቡታል። 9የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባሉ፤ ካህኑም ሁሉን የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቀርበዋል።
10“ነገር ግን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መባ ከበጎች ወይም ከፍየሎች ቢሆን፥ ለሚቃጠል መሥዋዕት ነውር የሌለበትን ተባቱን፥ የፊት እግሮቹንና ራሱን ጨምሮ#“የፊት እግሮቹንና ራሱን ጨምሮ” የሚለው በግእዝና በዕብ. የለም። ያቀርበዋል። 11#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በራሱም ላይ እጁን ይጭናል” የሚል ይጨምራል።በመሠዊያውም አጠገብ በመስዕ በኩል በእግዚአብሔር ፊት ያርዱታል፤ የአሮንም ልጆች ካህናቱ ደሙን በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ይረጩታል። 12በየብልቱም ራሱን፥ ስቡንም ይቈርጡታል፤ ካህናቱም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ይረበርቡታል፤ 13የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥቡታል። ካህኑም ሁሉን በመሠዊያው ላይ ለቍርባን ያቀርበዋል፤ የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
14“ለእግዚአብሔርም የሚያቀርበው ቍርባን የሚቃጠል መሥዋዕት ከዎፎች ቢሆን፥ ቍርባኑን ከዋኖስ ወይም ከርግብ ያቀርባል። 15ካህኑም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል፤ አንገቱንም ይቈርጠዋል፥ በመሠዊያውም ላይ ያኖረዋል። ደሙንም በመሠዊያው አጠገብ ያንጠፈጥፈዋል፤ 16የሆድ ዕቃውንም ከላባዎች ጋር ለይቶ በመሠዊያው አጠገብ በምሥራቅ በኩል በአመዱ ስፍራ ይጥለዋል፤ 17ከክንፎቹም ይሰብረዋል፤ ነገር ግን አይለየውም። ካህኑም በመሠዊያው ላይ በእሳቱ ላይ ባለው በዕንጨቱ ላይ ያኖረዋል፤ መሥዋዕቱ ለእግዚአብሔር በጎ መዓዛ ያለው ቍርባን ነው።
Currently Selected:
ኦሪት ዘሌዋውያን 1: አማ2000
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ